“የተከዜ ግድብ በቦምብ ተደብድቧል” በሚለው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሰጠው መግለጫ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑ ተጠቆመ። ይልቁኑም የሃይል ማመንጫውን ሲጠብቁ በነበሩ የፌደራል ፖሊስ ሃይሎች ላይ ትህነግ እርምጃ ወስዷል ነው የተባለው።
የተከዜ ሀይል ማመንጫ ግድብ በቦምብ ተደብድቧል ተብሎ በህወሓት አመራሮች የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ያታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ነው የገለጸው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ ተከዜ ግድብ እንደ ሌሎቹ ግድቦች በፌደራል መንግስት እንደሚተዳደር አስታውቆ፣  የፅንፈኛው የትህነግ ቡድን ከአምስት ቀን በፊት በስፍራው ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌደራል ፖሊሶች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይፋ አድርጓል። አያይዞም በፌደራል ፖሊሶቹ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ምን ያህሉ ህይወታቸው እንዳለፈ እና እንደቆሰሉ ባይታወቅም አስራ አንድ የሚሆኑ የፌደራል ፖሊሶች የአስራ አራት ሰዓት የእግር ጉዞ በማድረግ ጎንደር ከተማ መግባታቸውን አስታውሷል።
በፌደራል ፖሊስ አባላቱ ላይ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ የፅንፈኛው ህወሓት ቡድን አክቲቪስቶች የተከዜ ግድብን በትህነግ ሃይሎች እጅ መውደቁን በተደጋጋሚ እንደ ድል ሲገልፁ መቆየታቸውን መግለጫው አመልክቷል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ በመግለጫው ማጣሪያ ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦምብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችል መሆኑ የመረጃውን ሀሰተኛነት በቀላሉ የሚያረጋግጥ መሆኑንን ህዝብ ሊረዳው በሚችልበት መንገድ አስረድቷል።
ተፈጥሯዊ ባህሪው ነውና፣ በትህነግ ውስጥ የሚገኘው የጽንፈኞች ቡድን በሀሰት ለማሳመን ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል። ያለው መግለጫው፣
ትህነግ የሀሰት መረጃ የማሠራጨት ዘመቻውን በትጋት መቀጠሉን ሁሉም ሰው እንዲገነዘብም የማሳሰቢያ ጥሪ አቅርቧል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *