ማን ነው ክህደት የፈጸመው? የአገር መከላከያ ሰራዊት ወይስ ትህነግ? የሰሜን ዕዝ ሙሉ በሙሉ ትህነግን ተቀላቅሏል ተብሎ የተሰጠው መግለጫ ከየት የመጣ ነበር? ሁሉም ይቅር አራትና አምስት ቀን በውሃ ጥም እየተቃጠለ ራሱን ያተረፈውን ወታደር እንመን? ወይስ ደብረጽዮንን?

ሰለሞን ሃይሉ – ዛሬ አመሻሽ ላይ ደብረጽዮን በምስል ወቅታዊ መግለጫ ለመስጠት ብቅ ሲል ከወትሮው እጅግ የተለየ ነበር። በትህትና ” የተከበራችሁ ውድ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች” በማለት ጀመረ። አስከትሎም ኤርትራና የአገር መከላከያ ተባብረው እንደወረሩዋቸው አመለከተ። ከዚያ መከላከያ ላይ በተፋ መቁረጥ የካድሬ ዝናብ አዘነበ።

ቃል በቃል የሚከተለውን የቃላትና የሃርግ ዱላ አወረደ። በተሰበረ ስሜት ” እንሰዋለን” ካለ በሁዋላ ከመላው አገሪቱ እገሌ ከገሌ ብሄር ሳይባል ሰፊ የደጀን ድጋፍ የሚጎርፍለትን የአገር መከላከያ ሰራዊት ስም በመጥራት ” የኢትዮጵያ ህዝብ መከላከያ ሰራዊት አለኝ እንዳትል” ሲል አስተጋባ።

” ወራዳ፣ ታሪኩን የጨረሰ፣ አገርን ከወራሪ የማይታደግ፣ ትግራይን የወረረ፣ የትግራይ ህዝብን የከዳ፣ ዓላማ ቢስ፣ የአምባ ገነን ዘበኛ፣ ጸረ ህዝብ፣ ራሱን ወደ ደርገ ሰራዊት የቀየረ፣ አኩሪ ታሪኩ ያከተመ፣ ማፈሪያ … ” እያለ አገር የሚመካበትን ሰራዊት አወገዘ።

Related stories   ስብሃት ጨምሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች " ጥፋተኛ አይደለንም፣ መከላከያ ሰራዊት ዋሻ ውስጥ ተደብቀን ያዘን" አሉ

በዚህ አላበቃም ” ባዕዳን ናችህ ” ሲል አራት ነጥብ አስቀመጠ። ” ወራሪዎች ናቹህ እንፋለማችኋለን” በማለት ለፉከራና ማስፈራሪያ በማይመች ገጽታና አንደበት ዛተ። ቀጥሎም ” ከሻዕቢያ ጋር ደርበን ” ብሎ የቀብር ስርዓቱን በአጃቢ ለማሳየት ሞከረ።

ስሜቱ እጅግ እንደተነካና ነፍሱ ወደ አንዳች ጥግ እየጎተትችው እንደሆነ መሸሸግ ያልቻለው የትናንቱ የክልል ፕሬዚዳንት፣ የዛሬው ጁንታ ” መሬት አስመላሽ” ሲል የአገር መከላከያን አዲስ ስም ሰጠው። ሳግ እያነቀው መሬት መዝረፉን በኑዛዜ አፈረጠው። ውስጡ የመሬት ሌባ መሆኑንን አመነች። በእሱ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነ ነበሱ ቃተተች። ምን ይደርግ?

ሲጀመር” የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አድኑን” ብሎ ለምኖ ” የክህደት ክህደት ፈጽማችኋል፣ ልታስመልሱ ያሰባችሁት መሬት ላይ ከሻዕቢያ ጋር ደርበን እንቀብራችኋለን” በማለት እስኪጨርስና እስኪሰናበት ሲታወኝኝ የነበረው እኒያ ለትግራይ ህዝብ እንደ ቤተሰብ፣ ለአገር እንደ ምሶሶ ሆነው ሲያጭዱ፣ አቅመ ደካማ ሲያግዙ፣ አንበጣ ሲከላከሉ፣ ሲያርሱና ሲዘሩ የነበሩ ወገኖቻችን የደረሰባቸውን ባንደበታቸው ሲናገሩ የሰማሁት ነው።

ካድሬነት ጸያፍ ነው። ካድሬ ልብና ህሊና የለውም። ካድሬ ማንነቱ ደረቅ ነው። ካድሬ በድን ነው። ካድሬ የፊቱን እንጂ የኋላውን የማያይ ቅጣፊ ነው። የታረዱት፣ በተኙበት የተረሸኑት፣ በሸፍጥ ግንኙነት ተቋርጦባቸው የተጠበሱት ወገኖቻችንን በገሃድ የነገሩንን ገልብጦ መከለከያችንን ለእኛ ለደጀን ጋሻዎቻቸው ያማል።

Related stories   የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ - ቅንጅት "በተጭበረበረ ተግባር"እንዲሰረዝ ተወስኗል

ድፍረቱ እሱ ከባልደረቦቹ ጋር ሆኖ ሲሴስንና ሲዘርፍ እነሱ የድሜያቸውን ወርቃማ ጊዜ በጉድጓድ ውስጥ እንዳላሳለፉ፣ በባድሜ፣ በጾረናና በዛላንበሳ እንዲሁም በቡሬ ግንባር፣ ከዛም አልፎ ሶማሌ አስከሬናቸውን እያስጎተተ ዶላር እንዳላፈሰባቸው ” ካሃጂዎች” ይላቸዋል። ” ታሪካችሁን ገደል የከተታችሁ ማፈሪያዎች” ይላቸዋል።

ይህንን የምታነቡ አስቡት አንድ እድሜውን በደም አበላ የተጨማለቀ ፣ አገርን ቆዳዋን ገፈው የለበሱ ስግብግቦችን የሚመራ ጁንታ ምስኪን የአገር ምሶሶዎችን ” ታሪክ አልባ ” ሲልና ለሚወዳቸው ህዝብ ሲያማቸው … ሲያልቅ እንዲህ ነው። ሲያር እንዲህ ነው። በር ሲዘጋ እንዲህ ነው። የመጨረሻ ሰዓት ንግግር መቀባጠር ቢሆንም ካድሬ ምን ያህል በቁሙ የበደነ በድን፣ የደነገየ ድንጋይ፣ የሞተ ሙታን እንደሆነ ግንዛቤ ይኖራችኋል ብዬ አምናለሁ።

ህግ ማስከበሩ ይቀጥላ። የመሬትና የተራ ወሮ በላነት አጀንዳ የለም። ኢትዮጵያችን የሁላችንም አገር ናት። አላማው ህግን አስከብሮ በሰላም ተሳስቦ የመኖርና የመላማት ብቻ ነው። ምስኪን የትግራይ ለፍቶ አዳሪዎች ዛሬም ነገም ትናንትም ኢትዮጵያዊ ናቸው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *