” ጁንታ” በሚል ስያሜ የሚታወቀው የተገንጣይ ቡድን አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ በኤርትራ የተመረጡ ቦታዎችን በሚሳኤል እናጠቃለን በሚል ያሰራጨውን ዜና ተከትሎ ኤርትራ “ውርድ ከራስ” ስትል ከባድ ምላሽ እንደምትሰጥ ማስጠንቀቋ ተሰማ። ጌታቸው በጎንደር፣ በባህር ዳርና በሌሎች የተመረጡ የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ የሚሳኤል ጥቃት እንደሚሰነዘርም በይፋ ተናግሯል።

በሳምንት ጊዜ ውስጥ አካላዊ ገጽታው እጅግ እያነጋገረ ያለው ጌታቸው ረዳ በወያኔ ቲሌቪዥን ቀርቦ እንዳስታወቀው በባህር ዳርና በጎንደር ኤርፖርት የተፈጸመውን ጥቃት ታላቅ ድል ነው። በዚሁ ማብራሪያው በተመረጡ አካባቢዎች ጥቃቱ እንደሚቀጥል ሲያስረዳ ነበር ኤርትራም የተካተተችው።

ሕግ ከማስከበሩ ስራ ጋር ተያይዞ የጠራና ትክክለኛ መረጃ ለሕዝብ ለመስጠት የተቋቋመው የአስቸኳይ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ እንዳለው ጎንደርና ባህር ዳር ላይ የተተኮሱት ሮኬቶች መጠነኛ ጉዳት ማድረሳቸውን አስታውቋል። የጉዳቱን መጠንና አጠቃላይ ሁኔታውን ማጣራቱ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚያደርግ አመልክቷል። አያይዞም ” ስግብግብ” ሲል የጠራው ጁንታ ቡድን ያሉትን የመጨረሻ መሳሪያዎች ጠጋግኖ ከሞት ማግስት የመጨረሻ ሙከራዉን እያደረገ መሆኑንን የሚያመላክት የትስፋ መሟጠጥ አይነት የጥቃት ሙከራ እንደሆነም ጠቅሷል።

ጌታቸው ረዳ ጭንቀት እንዳለባቸው በሚያሳብቀው መልካቸው በዩቲዩብ ገጽ ቀርበው ” የሚሳኤል” ሲሉ የጠሩትን የመጀመሪያ ጥቃት ለማስፈራሪያነት በመጠቀም ኤርትራንም እንደሚደቁሱ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ምላሽ የተሰነዘረው። በዚሁ ምላሽ ኤርትራ ላይ የርቀት መሳሪያ የመተኮስ ሙከራ ከተደረገ ችግሩ የከፋ እንደሚሆንና ኤርትራ ለክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ተገዳ ጁንታው ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደማታቅማማና ፣ ጥቃቱም የከፋ እንደሚሆን ይፋ አድርጋለች።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

“ጭፍራ ወያኔ አስመራን በሚሳኤል እንደበድባለን እያለ ነው” ይላል ከኤርትራ በኩል የተሰጠው ምላሽ፤ ያስከትልና “እኛም ክብሪት አይደለም የታጠቅነው። የኢትዮጵያ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት እንደገባው ሁሉ እኛም ያለ ጥርጥር እንገባለን” ሲል ያስጠነቅቃል። ለትህነግ የተሰጠው ምላሽ ” ወያኔ ያጥፍቶ መጥፋት አላማውን ካልተወ ከባድ ነገር ይፈጠራል። ጉዳዩም የኤርትራ መንግስት ብቻ ሳይሆን የህዝቡም ይሆናል።” በማለት ድል ለሰፊው ህዝብ በመመኘት ይዘጋዋል። ኤርትራ ለሰጠችው ምላሽ እስካሁን ከጁንታው ወገን የተባለ ነገር የለም።

” የማገናዘብ ችግር እየገደለው ያለና የትግራይ ህዝብን ይዞ ወደ ገደል እየበረረ ነው ” ሲል አብዛኞች የሚተቹት የትህነግ አመራር፣ በአፈ ቀላጤው አማካይነት በቅርቡ ” ወረራውን መክተን ወደ መልሶ ማጥቃት እንዛወራለን” የሚል ምላሽ ቢሰጥም ዛሬ ላይ መንግስት ይፋ እንዳደረገው በራያ በኩል በርካታ ድል መመዝገቡና ጁንታው ያሰለፈው ሃይል መደምሰሱን፣ ይቀተርፈውም መሸሹንና እጅ መስጠቱ ታውቋል።

በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጁንታው ያሰለፈው ቡድን እጁን በ72 ሰዓታት ውስጥ ለመንግስት ሃይል እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውና የትግራይ ሕዝብም መሞቻው ለቀረበው ሃይል ሲል አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል ማሳሰባቸው ይታወሳል። አያይዘውም እጅ ከመስጠት በዘለለ ባለቀና በተቋጨ ጉዳይ ለበለጠ ወንጀል ተባባሪ መሆን ህይወትን ከማሳጣቱ በላይ በህግ እንደሚያስቀጣም አመልክተዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ዛሬ ማለዳ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጣፊ ጁንታው አሁን ለሰራው ብቻ ሳይሆን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያዊያን ላይ ለፈጸመው ጭፍጨፋ ሁሉ የሚጠየቅበት ቀን መቃረቡን አመልክተዋል። አያይዘውም እርቅ በተደጋጋሚ መሞከሩንና ጁናታው አልቀበልም ብሎ የሰላም ገበታ ሲረግጥ መክረሙን አመልክተው ” የሚገባው የሃይል ቋንቋ ብቻ ነው፤ በዛው በለመደውን አበሚገባው ቋንቋ ወደ ህግ እንዲመጣ ይደረጋል። ማንም የህግ ማስከበሩ ጊዜ እንዲወስድ አይፈልግም። በርግጠኛነት ዘመቻው በቅርቡ ይጠናቀቃል” ሲል ተናግረዋል። የቢቢሲ እንግሊዘኛ ፕሮግራም ጠያቂ ” እርግጠኛ ነዎት?” ሲላቸው ” እንዴታ” ብለዋል። በግፍ ለተቸፈጨፉት ሰላማዊ ዜጎች ህይወት ተተያቂው ጁናታው ቡድን መሆኑን አስረግተው ሲናገሩ ” የተረፉት ምስክርነት ሰጥተዋል፤ የህግ ማስከበሩ ሲተናቀቅ ገለልተኞች ይፋ ያደርጉታል” ብለዋል። አያይዘው የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ይህ ጁናታ ትጥቁን ፈቶ እጁን ለህግ እንዲሰጥ ጫና ከማድረግ በዘለለ ሌላውን ነገር ቢተውት የተሻለ እንደሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *