በአካባቢው ሰፍሮ የነበረው የመከላከያ ሃይል በተነደፈለት እቅድ መሰረት እንዴት ተናቦ እንደሚያጠቃ ልምምድ ሲስያደርግ ቆይቶ አካባቢውን ነጻ ለማውጣት ትዕዛዝ ሲጠባበቅ ነበር። በቴሌቪዥን መግለጫ የሰጡት አዋዲዎችና የካርታ ጠቋሚ ” ሞራላችንና እልሃችን ከልክ በላይ ነው። ይህን ጁንታ እንደመሠዋለን። የምንጠብቀው ት ዕዛዝ ብቻ ነው”  በማለት ተናግረው ነበር።

እንዳሉት ተግባሩ አልቆየም። መመሪያው እንደተላለፈ  ዋጋ ከፍለው፣ በአየር ሃይል ድጋፍ ሰጪነት፣ በከባድ መሳሪያ አጃቢነት ጥቂት መስዋዕትነት በመክፈል ራያንና አካባቢውን ነጻ አውጥተዋል።

የጁንታው አፈ ቀላጤ ” የሮኬት ጥቃቱ ይቀጥላል” በማለት ትንታኔ ሲሰጡ ” ከጥቃቱ በሁዋላ አሁን ውጊያው ጋብ ብሏል” ብለው ነበር። እንዲሁም ” ወደ ማጥቃት እንዛወራለን” ሲሉ ተደምጠው ነበር።

እሳቸው ይህን ባሉ ሰዓታት ውስጥ የመከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሃይል፣ እንዲሁም ደጀኑ ህዝብ በሚያደርገው ደጋፍ የሚታገዘው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለወራት የተማሰውን ምሽግ ተረማምደውበታል። ዛጎል እንደሰማችው ጁንታው ያሰለፋቸው ሃይሎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ተደምሰሰዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

” እጅግ ያሳዝናል” ሲሉ ምስክሩ እንደነገሩን እግር አውጪኝ ብሎ የሚሸሸው ሃይል በጁንታው ሃይል ” እለምን ትሸሻለህ” በሚል ቅጣት ተቀብላሏል። መከላከያ ሰራዊት የሰነዘረው ጥቃት ከባድ ስለነበር፣ ከተለያየ አቅጣጫና፣ በአየር የተደገፈ ስለነበር መቋቋም ያቃታቸው የጁንታው ምስኪን ሚሊሻና ልዩ ሃይል እጅ ለመስጠት ተገደዋል።

ነጻ በወጡት መንደሮችና አካባቢዎች መከላከያ አቀባበል ተደርጎለታል። ፋና እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎችምበ ፅንፈኛው የሕወሓት ቡድን ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ጭቆናበደል ሲደርስባቸው እንደነበር ገልፀዋል።

አሁን  ላይ በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት ከትህነግ ከሐዲ ቡድን ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸውን እየገለጹ ነው። የትግራይ ህዝብ የዘራፊውን ትህነግ ቡድን ሐገርን የማፍረስ ተግባር በመቃወም ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለባቸውም መናገራቸውን ሲል የአማራ ክልል ማስ ሚዲያ ዘግቧል። ከጁንታው ሃይል በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ምን አልባትም ሰሞኑንን በቁጥጥር ስር ውላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጀመረችው ሁመራ ነዋሪዎች አስተያየት እንደሰጡት ተብሎ እንደቀረበው አይነት መግለጫ ማምሻውን እንደሚቀርብ ይገመታል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *