“ትህነግ በይፋ ለኤርትራን የጦርነት ግብዣ አቀረበ”

በበረሃም ሆነ በሃያ ሰባት ዓመት የስልታን ጊዜው ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” ትህነግ በሚል ስያሜ የሚጠራውና በስተመጨረሻ መንግስት ” ጁንታ” ያለው ቡድን አስመራን በሶስት ተወንጫፊ ሮኬት መደብደቡ ታወቀ። የኤርትራ መንግስት “ለኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር ስንል እናታገሳለን” ሲል ከጥቃቱ በሁዋላ መግለጫ መስጠቱን ኤርትራን ፕሬስ የተሰኘው ድረ ገጽ ገለጸ።

ጌታቸው ረዳ ኤርትራን የመምታት እቅድ እንዳለ በይፋ መግለጹን ተከትሎ እንደተሰማው አስመራ ዛሬ ማምሻውን በከባድ መሳሪያ ጥቃት ደርሶባታል። የጉዳቱ መጠን አልተገለጸም። ጥቃቱን ተከትሎ ኤርትራ “ለኢትዮጵያ ክብር ሲባል ለተቃጣብኝ የጥቃት ሙከራ መልስ አልሰጥም” ማለቷን የዘገበው ድረገጽ፣” ኤርትራ ጉዳት አልደረሰብኝም ብላለች። ይህ የተከበበና የሞተ ቡድን ላይ አልተኩስም። ይልቁንስ ከኢትዮጵያ ጋር የወደፊት መልካም ነገራችን ይበልጣል። ይህ እየሞተ ያለ ቡድን ስለሆነ ለአብይ ሌላ ስራ አልሆንም ብላለች” Eritrean Press አመልክቷል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ትህነግ ጥቃቱን የሰነዘረው ኤርትራን ለጦርነት በመጋበዝ ተወረርኩ በሚል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለቅሶ ለማሰማትና ጣልቃ እንዲገባ እንደሆነ ድረገጹ ጠቁሟል። አያይዞም የትህነግ አካሄድ ኋላ ቀር ቢሆንም ኤርትራ ካሁን በሁዋላ ራሷን ከአሸባሪ ሃይሎች የመከላከልና ሉዓላዊነቷን የማስጠበቅ ሁለንተናዊ መብት እንዳላት አመላክቷል። ሲያጠቃልልም ” ኤርትራ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪውን ትህነግ እንደሚያወግዙት ትጠብቃለች” ብሏል።

ስለጥቃቱ ከትህነግ በኩል እስካሁን ዝርዝር ያልተሰጠ ሲሆን ደብረጽዮን ማምሻውን በቀጥታ ስርጭት “ኤርትራ ወራናለች” ብሏል። አያይዞም ከበባው በወልደያ በኩልም ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክቷል። ይሁን እንጂ ራያ በመከላከያ ቁጥትር ስር ስለመሆኗ ያለው ነገር የለም። በዚሁ መግለጫው ” ተመጣጣኝ አጻፋዊ እርምጃ እንወስዳለን” ሲል ተደምጧል። የተከዜ ሃይል ማመንጫም ተደበደበ በተባለ ቀናት ውስጥ ጥገና ተደርጎለት ስራ መጀመሩን አመልክቷል። ዳግም ከተመታ ግን “አይማረኝ ” አይነት ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

የተከዜን ሃይል ማመንጫ አስመልክቶ መንግስት ድብደባ እንዳልፈጸመ፣ ሃይላ ማመንጫው ቢመታ የውሃ ማጥለቅለቅ እንደሚከሰትና ጉዳት እንደሚያስከትል፤ በቀላሉ ሊጠገን እንደማይችል፣ ወሬው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የተፈበረከ ስለመሆኑ ማስተባበያ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *