ሕዳር 6 ቀን 2013 የአገር መከላከያ እንዳስታወቀው ዋጃ፣ጥሙጋና አላማጣ በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እጅ መውደቃቸውን አስታውቋል። ጁናታው አከባቢውን ጥሎ ሲፈረጥጥ ፣ በአላማጣ ከተማ ታስረው የነበሩ 10 ሺህ ዜጎችን ይዞ አፈግፍጓል።
የደቡብ ዕዝ የሰው ሀብትና ሚዲያ ስራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ፀጋዬን  ጠቅሶ ዜናው እንዳመለከው ክፉኛ በትር የደረሰበት የጁንታው
ቡድን በየአውዱ እየፈረጠጠ ነው። መከለከያ የግራካሶ ተራራና አከባቢውን ለመቆጣጠርም እየገሠገሠ ይገኛል።
በራያ ቆቦና አከባቢው ህግን ለማስከበር የተሠማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊታችን ከአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ጋር በመተባባር ዋጃ ፣ ጥሙጋ ፣ አላማጣና አከባቢውን ከጁንታው የህውሀት ቡድን ነፃ አውጥቶ ተቆጣጥሯል ።
በሰራዊቱ ዝግጁነትና በህዝቡ ደጀንነት የተደናገጠው ደም መጣጩ ቡድን ፣ አከባቢውን ጥሎ የፈረጠጠ ቢሆንም ፣ በአላማጣ ከተማ ታስረው የነበሩ 10 ሺህ ዜጎችን ይዞ ማፈግፈጉን የደቡብ ዕዝ የሰው ሀብትና ሚዲያ ስራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል ።
በተጨማሪም ሠራዊቱ የግራካሶ ተራራና አከባቢውን ለመቆጣጠር እየገሠገሠ እንደሚገኝና በምስራቅ አላማጣ ፣ በጨርጨር አከባቢ የተሠማራው ሠራዊትም ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ኮ/ል ደጀኔ ፀጋዬ ገልፀዋል።
እንዲሁም ፅንፈኛው ቡድንን በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር ሠራዊታችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተራመደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ነዋሪዎችም ፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን አካባቢውን ጥሎ በመሸሹ ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
የአማራ ልዩ ሀይል አዛዥ ፣ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን በበኩላቸው ፣ ህብረተሰቡ ሳይጎዳ አካባቢውን ለመቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል።
ንጉሴ ውብሊቀር ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶግራፍ ንጉሴ ውብሊቀር

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ስብሃት ጨምሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች " ጥፋተኛ አይደለንም፣ መከላከያ ሰራዊት ዋሻ ውስጥ ተደብቀን ያዘን" አሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *