የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወንበዴው ህወሃት/ትህነግ አገር ለማፍረስ ዓላማ ሲጠቀምባቸው የነበሩት 34 የፋይናንስ ተቋቱን ማገዱን ይፋ አድርጓል።
እንደ ኢቲቪ ዘገባ ከታገዱት የበረኻ ወንበዴዎቹ ድርጅቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፤
ሜጋ ማተሚያ፣
ሱር ኮንስትራክሽን፣
ጉና የንግድ ሥራዎች፣
ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ፣
ትራንስ ኢትዮጵያ፣
መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣
ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣
ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው።
ጎልጉልን ጨምሮ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ወዘተ ለትህነግ የፋይናንስ ምንጭ የሆነው ኤፈርት ወደ ሕዝብ ሃብትነት እንዲመለስ ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል።
ስብሃት ነጋና ቤተሰቡ የተቆጣጠረው ኤፈርት ግብር የማይከፍል፣ የአገር ሃብት ወደፈለገው ፈሰስ የሚያደርግ፣ ኦዲት የማይደረግ፣ በኃላፊነት የማይጠየቅ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ የተቋቋመውን ድርጅት ስብሃት ነጋ ራሴና ጥቂቶች ሆነን ገንዘባችን አዋጥተን የመሠረትነው በማለት በተደጋጋሚ ሲናገር ተደምጧል።
በወንበዴዎቹ ላይ በተከፈተው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሱር ኮንስትራክሽን በርካታ ምሽጎችን በመሥራት ለትህነግ የላቀ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

ተጨማሪ መረጃ
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ያወጣው መረጃ እንዲህ ይነበባል፤
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የዘር ተኮር ጥቃት እና የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው የትህነት/ ህወሃት ሀይል ጋር ግንኙነት በመፍጠር፤ በመመሳጠር እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የተሳተፉ ስለመሆናቸው እና በግብር ስወራ እና የሙስና ወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ስለመሳተፋቸው ምርመራ ለመጀመር የሚያበቃ በቂ ማስረጃ የተገኘባቸውን ከታች ስማቸው የተጠቀሱትን ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በባንክ ያለቸውን ገንዘብ ጨምሮ ከህዳር 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲታገዱ አድርጓል።
ዕግዱ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ድርጅቶቹ ሀብታቸውን ለማሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ በቂ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ ንበረቶቹ ሳይሸሹ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ማቆየት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት ነው።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የመመርመር እና ሀብትን የማስመለስ ስራውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ የታገዱት ንብረቶች እንዳይጎዱ እና እንዳይባክኑ ጠብቆ የሚያቆይ የንብረት አስተዳዳሪ የሚሾም ሲሆን አስተዳዳሪው ስራውን ተቀብሎ ማስተዳደር እስኪጀምር ድረስ የድርጅቶቹ አስተዳዳሪዎች ንበረቱን በሚገባ የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው።
በቀጣይ የምርመራ እና ክስ ሂደቱን ተከታትለን ለህዝቡ የምናሳውቅ ሆኖ የታገዱት ድርጅቶች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት መሆናቸውን እንገልጻለን።
1. ሱር ኮንስትራክሽን
2. ጉና የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
3. ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
4. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
5. ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር
6. ሜጋ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
7. ኤፈርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
8. ኤፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
9. ኤፈርት ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
10. ኢዛና ማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
11. ቬሎሲቲ አፖራልዝ ካምፓኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
12. መሰቦ ቢውልዲንግ ማቴሪያል ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
13. ሳባ ዳይሜንሺናል ስቶን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
14. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ
15. ሼባ ታነሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
16. ኤ.ፒ ኤፍ
17. ሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን
18. እክስፕረስ ትራንዚት ሰርቪስ
19. ደሳለኝ ካትሪናሪ
20. ሼባ ታነሪ ፋክተሪ አክሲዮን ማህበር
21. ህይወት አግሪካልቸር መካናይዜሽን
22. ህይወት እርሻ ሜካናይዜሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
23. አልመዳ ጋርመንት ፋክተሪ
24. መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ
25. ደደቢት ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር
26. አዲስ ፋርማሲቲካልስ ፕሮዳክሽን
27. ትግራይ ዴቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
28. ስታር ፓርማሲቲካልስ ኢፖርተርስ
29. ሳባ እምነበረድ አክሲዮን ማህበር
30. አድዋ ፍሎር ፋክተሪ
31. ትካል እግሪ ምትካል/ ትግራይ/ ት.እ.ም.ት/
32. ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
33. ደሳለኝ የእንስሳ መድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
34. ማይጨው ፓርትክል ቦርድ ፋክተሪ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ከስምምነት መድረሱን አስታወቀየኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር የአገር ሕልውናን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች መስማማታቸውን አስታወቀ። ባለፈው ዓመት ሰላም ሚኒስቴር፣ እርቀ ሰላምContinue Reading
- Gov’t Providing Assistance for over 2.5mln people in Tigray, Benishangul-GumuzThe National Disaster Risk Management Commission (NDRMC) said adequate preparations have been made to assist 2.5 million citizens, including the 700,000 additional needy people affectedContinue Reading
- የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርትበትግራይ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በርሃብ ተጠቃ፣ ሞትም ጀምሯል ሲባል ድንጋጤ ፈጥሯል? በተመሳሳይ ረሃቡ የኖረ፣ ወይስ አዲስ ለሚለው ጉዳይ መልስ የሚሰጡ የሉም። ይልቁኑContinue Reading
- እነ ጃዋር ” በዛሬው ቀጠሮ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁ አይደለንም” ሲሉ የመማከሪያ ጊዜ ጠየቁበተሻሻለው ክስ መሰረት የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጥ ጥያቄ የቀረበላቸው እነ ጃዋር መሐመድና አስራ ስምንት ተጠርጣሪዎች ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በጠየቁት መሰረት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ጠበቆቻቸው Continue Reading