በሰሜን ዕዝ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ጠላትነትን በዕምነትም ሆነ በተግባር ካረጋገጠው ወንበዴ ሀይል ጋር ያበሩ አመራሮች አንዳንዶቹ ሠራዊቱ መሣሪያውን አስቀምጦ እንዲመጣ ስብሰባ ጠሩ።
መሪ አባት ነውና አባላቱ ሳይጠራጠሩ አደራሽ ገብተው ተቀመጡ ።
ከውስጥ የደባ ተልዕኮ የተሰጣቸው ከሃዲ አባላት ፣ ባዶ እጃቸውን የተቀመጡ የኢትዮጵያ ብሔርና ብሔረሰቦች ልጆች የሆኑ የሠራዊት አባላት ላይ ገሀዲዎቹ ያልተጠበቀና ድንገተኛ ተኩስ ከፈቱ ።
በሠንደቅ ዓላማችን ፊት ለውዲቷ ሀገራችን ሠላምና ደህንነት አብረው ቃል-ኪዳን በገቡት ጓዶቻችን አባላት ጥይት ተመትተው ከመሞት በላይ ሞቱ።
እነሱ በሳቅና በፌሽታ ታጅበው የራሳቸውን ጓድ አካላቸውን በሳንጃ እየወጉ ሳለ ፣ ከውጭ አድፍጠው ይጠባበቁ የነበሩ የትግራይ ልዩ ሀይል አባላትና ሚሊሻዎች ደርሰውላቸው ዕኩይ ተግባራቸውን ተጋሩ።
የክህደት አድራጎታቸውን ቀጥለውም በህይወት የተረፉትን ከባህልና ወጋችን ፣ ከውትድርና ደንብና ስርአታችን ባፈነገጠ ሁኔታ ፣ የክብር ልብሳቸውን በመግፈፍ በራቁት እያስጓዙ ፣ የተሰውትንም በድናቸውን ራቁት በማድረግ ፣ ከተከበሩበት ታሪክ ፣ ሲሰሩበት ከኖሩበት ግቢ አውጥተው አርቀው ካስቀመጡ በኋላ ፣ የተካደችው የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ልጆች አስከሬን ተጥሎ ከበው ጨፈሩበት።
እንግዲህ ጭፈራው ምንም አይነት ሊሆን ይችላል ፣ ” ብደንጎላ ኮሎኔል ማራኪ ” ሊሆን ይችላል ፣ ” ሳይንሳዊ መብረቅ አውርዲሎ ” ሊሉ ይችላሉ ፤ እነሱ ምን ይሳናቸዋል ?
ይሄንን ሁሉ አዳፋ ታሪክ በቆሸሸ አካሄዳቸው የፃፉት ከሃዲ መሪዎ፣ ች እንደ አባት የሚቆጥሩትን የዓላማ ልጆቹን ክዶ እና ነጥሎ በስብሰባ ሰበብ አስቀምጦ ፣ ቀደም ብሎ ባሰማራቸው የውስጥ ባንዳዎች አማካኝነት አገር ሲጠብቁበት በኖሩት መሣሪያ ረሽነው ፣ አሰቃይተውና አግተው ስለ ሣይንሳዊ መብረቅ ማውራት ከጥንትም ከአባቱ የወረሰው የታሪክ አተላዎች ውሸት ስለመሆኑ ድርሳኑ ከትቦታል።
በአንዳንድ ካምፖች ደግሞ ፣ ሠራዊቱ እንደ ወትሮው በጋራ እራቱን በልቶ ተረኛ ጥበቃ ያልሆኑ አባላት ወደ መኝታቸው አቅንተዋል። ከውስጥ ተልዕኮ የተሰጣቸው ከውጭ የልዩ ገዳይ አባላት ብቻ ሠዓቱን በጉጉት ይጠብቃሉ።
ከውስጥ ተልዕኮ የተቀበሉ አካላት የትላንት ጓዶቻቸውን መኝታ በሚገባ ስለሚያውቁ ሰዓቱ ሲደርስ መኝታቸው ላይ እንዳሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ረሸኗቸው። የውጭውም ገብቶ የቀረውን ጨረሰ።
ይሄ ምንም ዓይነት ቃላት በስያሜ የማይገልፀው ፣ በኢትዮጵያ ላይ በተጠነጠነ ጥላቻ ተፀንሶ ፣ ተወልዶ ፣ ጎርምሶና ጎልምሶ በስተርጅናውም የሴራ ፖለቲካው ያልለቀቀው ጁንታ ክደት የፈፀመባቸው የሠራዊታችን ክፍሎች ውስጥ የሰሜን ዕዝ ክፍሎች ፣ በህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ስር የሚገኘው የውጊያ ድጋፍና የውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ማሰልጠኛ ት/ቤት እንዲሁም በኢፌዴሪ አየር ሃይል የሰሜን አየር ምድብ አመራርና አባላት ናቸው።
አባላቱ በስታፍ ተግባራት ክንውን ላይ ኮምፒውተር ላይ ተደፍተው የሚውሉ ፣ ከእስክርቢቶና ከወረቀት ጋር ተቆራኝተው የሚያድሩ ቅጥር-ግቢው ከሚጠበቅ አነስተኛ የሰው ሃይልና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች ውጭ ሌላ አቅም አልነበረም።
ይሄ የባንዳ ጥርቅም “የውሸት ተራራ አንቀጥቃጭ”ና “ኮሎኔል በድንጋይ እንደማረከ” በውሸት ትርክት ሲሞላን የኖረ ጁንታ ሀይል ግን ፣ ባልጠበቁት ሠዓት የአር ፒ ጂ ፣ የመትረየስና የስናይፐር የአረር ውረጅብኝ ጠላት ብሎ በፈረጁዋቸው በወገኖቻቸው ላይ አርከፈከፉ።
“ከጎኔ አሰለፍኩዋቸው” ፣ “መብረቃዊ ምቴን አሳረፍኩባቸው” ፣ “ማረኳቸው” የሚለን እንግዲህ እኒህን አብረውት እንደ ልጅ ከጉያው የኖሩና ስንት የሆኑለትን የህዝብ ልጆች ነው።
ለእኔ ይሄ ድርጊታቸው ብዙ ነገር ግልፅ አድርጎልኛል። ደርግ አምባገነናዊ ስርዓት ሊሆን ይችላል፡፡ እነሱ ግን “አረመኔያዊ ወንበዴ ፣ ጨካኞችና ኢትዮጵያዊ ስብእና የሌላቸው ከሃዲዎች” በሚል ተጨማሪ የባንዳነት የማዕረግ ስም ይገባቸዋል።
እነዚህ ሰዎች ህዝቡንም ሀገሩንም ከመጥላታቸውም በላይ ፣ እየጠሉ ገዝተውትም እየጠሉትም ግጠው ከጨረሱ በኋላ ፣ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ለመበታተን ከውስጥም ከውጭም ያለ የሌለ አቅማቸውን አሟጠው ለመጠቀም በተዘጋጁበት ወቅት ተቀደሙ እንጂ !
ኢትዮጵያ በታሪኳ በተደጋጋሚ የውጭ ወራሪም ሆነ ለሆዳቸው ብለው ከጠላት ጋር ያበሩ ተባባሪ ባንዳዎች አጋጥመዋታል ፤ እንደነዚህ ከሃዲዎች በውሸት የታሪክ ሙሌት እየሳቁ የገደሉን ፣ ገድለውም በበድናችን ላይ የጨፈሩና ከአውሬ ጋር የበሉን የቀንና የሌሊት ጅቦች አይነት ቢፈለግ የትም አይገኝም።
ያደረጉን ብዙ ነው ፤ የካዱን አንድ ሺህ አንድ ጊዜ ነው።
ሁሉን ቢያወጉት … እንዲሉ ፣ የሀገሬ ቁስል የሚሽረው ከተደበቁበት የሴራ ምሽጋቸው አውጥተንና ከተከበረው የትግራይ ህዝብ ለይተን ለፍትህ ስናቀርባቸው ነውና ፣ አሁን ላይ ሰላማዊ ውይይት ጊዜው ያለፈበት ጁንታዊ ቋንቋ ስለሆነ ከዘመን ጀግኖች ጋር ወደፊት,,,,,,።
“የሆነው ፣ የተደረገው ፣ የተፈፀመው ከተባለው በላይ ገና የሚነገር ነው።”
ሻምበል ፈይሳ ናኔቻ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *