የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናል መባሉን ተከትሎ በተወሰደ የማጥቃት ርምጃ የትህነግ ሃይል መደምሰሱ፣ መማረኩና በርካታ ቁሳዊ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለፀ። የአገር መከላከያ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን እጁ አስገብቶ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡
በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል። ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው።
በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አክሱም በመገሥገሥ ላይ ይገኛል።
በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ከመማረካቸውም በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየገሠገሠ ሲሆን የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በይፋዊ ገፁ አመላክቷል።
በሌላ ዜና ትህነግ ወደ መቀሌ የሚያስኬዱ አራት ድልድዮችን ማፈራረሱን መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡ የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው ጁንታ፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቀሌ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮችን ያፈረሰው እየደረሰበት ያለውን ጥቃት ለማባረድና ፍጥነት ለመቀነስ ነው፡፡
የተማመነባቸው ከባድ ምሽጎቹ ፈራርሰው፣ በሽሬ መንገድ የደረሰበት ሽንፈት ያንገበገበው ጁንታ፣ በሽሬና በአኩስም መካከል የሚገኘውን አስፓልት በግሬደር ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታል።
የሕወሐት ጁንታው እስከዛሬ ከፈጸማቸው ወንጀሎች በተጨማሪ ባወደማቸው መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ይጠይቅባቸዋል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ግብረ ሀይል አስታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ኤታማዦርሹሙ ሱዳን ከተደገሰላት የጦርነት ወጥመድ ይልቅ ለዕርቅ ቁርጠኛ እንድትሆን መከሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *