መላው የትግራይ ህዝብ ነባር ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን በመጠቀም አገር በማተራመስ ላይ ያለውን ፅንፈኛውን የህወሓት ቡድን በሰላም እጁን እንዲሰጥ ጫና ማሳደር እንደሚገባው የቀድሞው የቅንጅት አመራርና ፖለቲከኛ ዶክተር ኃይሉ አርዓያ አስታወቁ፡፡
ዶክተር ኃይሉ አርዓያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን ላለፉት 27 ዓመታት ህዝብ ሲበድልና ሲያንገላታ መቆየቱ አልበቃ ብሎ ከሰሞኑ ደግሞ ሀገርን በመጠበቅ ላይ ባለ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙ የቡድኑን ከሃዲነት የሚያሳይ ነው፡፡ ጥቃቱ የትግራይ ህዝብ ከኖረበት መልካም እሴት አኳያም ተፃፃሪ የሆነ እኩይ ተግባር በመሆኑ ይህንን ኃይል በገሃድ ወጥቶ ሊያወግዘው ይገባል፡፡
ህወሓት አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅበት ሁኔታ ተቻችሎ የኖረውን ህዝብ በብሔር በመከፈፋል እርስበርስ እንዲባላና እንዲገዳደል በማድረግ ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱን አመልክተው ፣ይህ ጽንፈኛ ሃይል ባለፉት 27 ዓመታት አሰፈንኩ ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም ከወረቀት ያልዘለለ ፤ በተጨባጭ ህዝቡን ተጠቃሚ ያላደረገና አገሪቱን ወደለየለት አዘቅት ውስጥ የጨመረ መሆኑን አመልክተዋል።
ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለእሱና እሱን ለሚከተሉ ብቻ ተለክቶ የተሰፋ እንጂ ህዝቡ የዚህ ዴሞክራሲያዊ መብት ተጠቃሚ እንዳልነበር የጠቆሙት ዶክተር ሃይሉ ፣ ለአብነትም የራያና አካባቢው ህዝብ ያለውዴታው በእነሱ ጨቋኝ አገዛዝ ውስጥ እንዲወድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ይህ ህዝብ ይተዳደር የነበረው ከአድዋ በመጡ እንደራሴዎች ብቻ እንዲሆን መደረጉ በአገሩ ባይተዋር ሆኖ እንዲኖር ያደረጉት መሆኑን ገልጸዋል።
ጥቂት የማይባለው የአካባቢው ተወላጅ ጭቆናውን በመሸሽ ከአገር የተሰደደበት ሁኔታ መኖሩን አስታውሰው፤ ሥርዓቱን የተቃወሙ ወጣቶች ለእስራትና ለእንግልት ሲዳረጉ መኖራቸውን አመልክተዋል።
«የመከላከያ ሰራዊታችንም ሆነ መንግሥታችን በዚህ ኃይል ላይ እየወሰደ ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ የምደግፈውና መቀጠል ያለበት ነው» ያሉት ዶክተር ኃይሉ፤ እርምጃው የአገርን ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ ያለመ በመሆኑ ፅንፈኛው አካል እጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ መላው ህዝብ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በተለይም የትግራይ ክልል ህዝብ የዚህ ኃይል የጭቆና ቀንበር በዋነኝነት ያረፈበት እንደመሆኑ ከባህሉ ከወጉ ውጭ በመሆን ህዝብ ለማስጨረስ የወጣውን ኃይል በገሃድ መቃወምና ለህግ ራሱን አሳልፎ እንዲሰጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
«እውነተኛ ጀግና በሃቅ የሚያምን፤ ለሃቅ የሚሞት፤ ሲሳሳትም ስህተቱን አምኖ ከስህተቱ የሚመለስ ነው» ያሉት ዶክተር ኃይሉ፤ አገር በማተራመስ ላይ ያሉት እነዚህ የህወሓት አባላት ጀግና የህዝብ ልጅ ነን ብለው የሚያምኑ ከሆኑ ጊዜው ሳይረፍድባቸውና ብዙ ህዝብ ከማስጨረሳቸው በፊት ራሳቸውን ለህግ አሳልፈው ሊሰጡ እንደሚገባም መክረዋል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው።
የእስካሁኑ ግትርነታቸው በተለይም የትግራይን ህዝብ በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ ከመሆኑም ባሻገር የአገርንም ህልውና አደጋ ውስጥ የሚጥል በመሆኑ በአፋጣኝ ማሳሪያቸውን መጣል እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል።
ምንጭ አዲስ ዘመን
 • ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!
  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሃላፊ ሆነው ለስድስት ወራት በሃላፊነት የቆዩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በዛሬው እለት ከስልጣን መነሳታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በምትካቸው ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም የሆኑት ዶ/ር አብራሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። ዶ∕ር አብርሃም በተለያዩ የመንግስትContinue Reading
 • እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።
  ከመንደር ወጥተናል።ሀገርን መርጠናል።ልካችን ሳንመርጥ የተወለድንበት ብሔራዊ ማንነታችን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ስንል ለህዝቦቿ ደህንነት እና የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ክብር ወዶ እና ፈቅዶ የመሞት ቁርጠኝነት የሚያላብስ ማንነት ነው። የእኛ ምርጫ በጊዜ ወቅት የሚገደብ፣ በውስጥና ውጭ አካል የሚታዘብ አጨቃጫቂና አከራካሪ አይደለም።በውርስ የሚተላለፍ ነው። የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ሀገራዊ አስተዋፅኦ የምንለከው በአባት አያቶቻችን ከአእምሮ በላይContinue Reading
 • አውሮፓ ህብረት – ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ
  “የአውሮፓ ህብረት ምርጫ የማይታዘበው በበጀት እጥረት መሆኑንን ገልጾልናል” ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ህብረቱ ወዲያውኑ ” በበጀት እጥረት ምክንያት ሳይሆን የቀረነው ስላልተጋበዝን ነው” ሲል ድምጹን አሰማ። ምላሽ ሰጠ። ጉዳዩ ከዚያ በላይ አልሄደም። ነገሩ ህወሃት የሚባለው አገዛዝ ቀደም ሲል የገባው ኮንትራት ነበርና ብዙም አስገራሚ እንዳልነበር በወቅቱ ብዙ ተብሎ እንደነበርContinue Reading
 • የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤
  በተጨማሪም በውጭ በተለያዩ ሀገራት ሆነው ይህንን ህቡዕ አደረጃጀት ሲያስተባበሩ እንዲሁም የፋይናንስ፣የሃሳብና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ፣ አቶ ተሻለ ከበደ ኢዶ፣ወይዘሮ የሀረርወርቅ ጋሻው፣ አቶ አስፋው ጀቤሳ፣ አቶ መዕረግ፣ አቶ ቢኒያም፣ አቶ ኪሩቤል፣ ወይዘሪት ሊሻን አህመድ፣ ዶ/ር ገነት፣ ወይዘሮ አረጋሽ፣ ኢንጀነር ሊሻን ግዛውና አቶ ሀገሬ አዲስ በወዳጅ ሀገራት ትብበርና  ከኢንተርፖል Continue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *