ለስምንተኛና አስራ ሁለተኛ መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ለአንድ ዓመት ብቻ አስር ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚያወጣው የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎቹን በዲጂታል ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተሰማ። ስልጠና መስጠት ተጀምሯል። ሁዋዌ ታብሌቶቹን በርዳታ እንደሚሰጥ ታወቀ። አንድ ሚሊዮን ታብሌቶች መንገድ ላይ ናቸው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘንድሮ ፈተናን በዲጂታል ለማከናወን መተግበሪያውን አዘጋጅቶ ቸርሷል። ፕሮጀክቱ ገና ይፋ ስላልሆነ አሁን ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩ ጠቅሰው ዜናው ትክክል መሆኑንን አንድ ከፍተና ኤክስፐርት ለዛጎል ገልጸዋል።

Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አስራ ሁለት ሰልጣኞችን በማዘጋጀት ላይ የሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር በዘንድሮው ዓመት ትምህርት የሚከታተሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቅርቡ የታብሌት ባለቤት ይሆናሉ።

ዋና ትኩረቱን የአገሪቱን ትምህርት አሰጣጥ ዲጂታል ለማድረግ አቅዶ የሚሰራው የትምህርት ሚኒስቴር ቀደም ሲል በየዓመቱ ለብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሲያወጣው የነበረውን አስር ሚሊዮን ዶላር ለማቀረት ወስኗል። በዚሁ መሰረት ሁዋዌ ሊሰጥ ቃል ከገባው አምስት ሚሊዮን ታብሌቶች ውስጥ አንድ ሚሊዮኑ በቅርቡ አገር ቤት ይገባሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *