በትግራይ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በአየር ኃይል ሄሊኮፕተሮች እየተጫኑ ወደየቤተሰቦቻቸው እየተጓዙ ነው። አየር ኃይል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለተለያየ የስራ ጉዳዮች በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰራተኞችን ወደየአካባቢያቸው የማመላለስ ስራ መጀመሩን አሳወቀ።
አየር ኃይል ወደመጡበት አካባቢያቸው እየመለሳቸው ከሚገኙት ውስጥ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የሄዱ ፣ በአካባቢው የደረሱና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ይገኙበታል። አየር ኃይል ከሽሬ አውሮፕላን ማረፊያ ነው ተማሪዎችን የማመላለስ ስራ የጀመረው።
ተማሪዎቹ የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርግላቸው እንደነበር ተናግረዋል። ሰራዊቱ ላለፉት ቀናት ለተማሪዎች ምግብና መጠጥ፣ መጠለያ ሲያቀርብ እንደነበር ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሄዱ ተማሪዎችን ወደየቤተሰቦቻቸው የመመለሱን ስራ እንደሚቀጥል አሳውቋል።
Via EBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *