“Our true nationality is mankind.”H.G.

የትህነግ የውጪ አገር ከፍተኛ ድጋፍ ሰጪዎችና ሎቢስቶች ጌታቸው አሰፋን እየወነጀሉ ነው !

ጌታቸው አሰፋ አካሄዱ ያልተመቻቸው መለስ ዜናዊ ሞት ቀደማቸው እንጂ ከሃላፊነቱ ሊያነሱት ወስነው እንደነበር የቅርብ አዋቂዎች ይገልጻሉ። የመቀሌው ተወላጅ እንደተፈራው መለስ እንዳረፉ ህወሃትን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቆጣጠረው። የትህነግ ምክትል የነበረው አባይ ወልዱ አስቀድሞም ሲሾም መለስን የሚገዳደል ሰው እንዳይኖር በሚል የተቀመጠ ነበርና ትህነግን በመላስ ሞገስ መምራት ቀርቶ ጥሩ ተመሪ እንኳን መሆን ሳይችል ተሰናበት። በዚሁ ሳቢያ አንጋፋዎቹ የየራሳቸው ቡድን ሰርተው የየራሳቸውን ጡንቻ ሲያፈረጥሙ ድርጅቱ ተናደ። ማዕከላዊነት ራቀው። ፈሪና ተፈሪ ጠፋ። ሳይታወቅ እየወላለቁ ሄዱ። በዛው መጠን ኦህዴድና ብአዴን አድብተው ከህዝብ አመጽ ጋር ሆነው ቁልቁል ነዷቸው።


በብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞና ቅሬታ ይሰነዘር እንደነበር የተሰማው የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ይፋ ከሆነ በሁውላ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አገሪቱ በነውጥና ግጭት እየነፈረች ባሳለፈቻቸው ሁለት ዓመታት በፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን ከሕዝብ ዘንድም ክፉኛ ተቃውሞ ሲሰነዘርባቸው ነበር የከረመው።

በአንጻሩ ትህነግ ወደ መቀሌ ሲያፈገፍግ የጸጥታ መዋቅሩን ስለላውንና የግንኙነት መስመሩን ነቃቅሎ ይዞ በመሄዱ መንግስት እንደ አዲስ ሁሉንም የመጀመር ጣጣ ውስጥ በመግባቱ ለውጡ በተፈለገው መንገድ ሊሄድ እንዳልቻለ የገባቸው እጅግ ጥቂት ሃይሎች ነበሩ።

ዛጎል እንደሰማችው የቀድሞው የአገር ደህንነት ዋና ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማስወገድ ወጥመድ ዘርግቶ ሴል እንዳደራጀ ለውጡን በግንባር ቀደምትነት ከሚደግፉ አገራት መካክለ አንዷ የሆነችው አሜሪካ መረጃ ደርሷት አትርፋቸዋለች። መረጃው የደረሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መሃላቸው ሳይደርቅ እንዲወገዱ የተቋቋመውን ሴል ለማክሸፍ በሁለት መስመር ደብዳቤ ጌታቸው አሰፋን ከሃላፊነቱ ሲያነሱ ሰላይ ነውና ወጥመዱ እንድተነቃበት የገባውና ” ባህር ዳር ነኝ” ብሎ የያዘውን ይዞ መቀሌ ገባ።

መቀሌ ሆኖ ያደራጀውን ሴል በማንቀሳቀስ የሰኔ አስራ ስድስቱ የግድያ ሙከራ ተደረገ። ከዛም ይፋ ባይሆንም አብይ አህመድን ነጥሎ ማጥፋት ላይ ያተኮረ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። እሳቸው ራሳቸው ለፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ ” ያልተሞከረ ሙከራ የለም። ግን ጠባቂው አያንቀላፋም” ብለው ከሙከራዎቹ ጥቂቶቹን ሲናገሩ ፓርላማው አልቅሷል።

Related stories   በአቡነ ማቲያስ መልዕክት ሳቢያ - ሲኖዶስ በመቆጣቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ የተግሳጽና የማስተካከያ መግለጫ ሊሰጥ ነው

እሱ ብቻ አይደለም ታዋቂ ሚዲያዎችም ዘ ጋርዲያን ያለውን ተከትለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድንገት እንደሚገደሉ እየተቀባበሉ ዜና አድርገው ሰርተው ነበር። ” ትብትቡ ሃይለኛ ነው” ሲሉ የገለጹት የ27 ዓመቱ የትህነግ መዋቅር አኩራፊዎች፣ የሰጉና በሙስና የተጨማለቁ አንድ ላይ ሆነው በከፍተኛ በጀት እዛም እዚህም ሃይል እያደራጁ አገሪቱ ሰማታና አይታ የማታውቀው አይነት ግፍ ተፈጸመ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ያልገባቸው ” መንግስት ለፈስፋሳ ነው” በሚል  ሲዘለዝሉት ጥቅላይ ሚኒስትሩ ቀውሱን በማለዘብና ማስታገሻ በማድረግ ዋና ትኩረታቸው የነበረው የደህነንቱን፣ የፖሊስንና የመከላከያውን ሃይል ዳግም መስራትና የሪፐብሊካን ሰራዊት ማደራጀት ላይ ነበር። ከሌሎች አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በተጨማሪ የአገሪቱን የጸጥታ ሃይልና አቅም ሲያደራጅ መቆየታቸው ዛሬ ላይ ትክክል እንደሆነ አብዛኞች እየመሰከሩ ቢሆንም በትህነግ ደጋፊዎችና የውጭ የዲፕሎማሲ ክንፍ ዘንዳ ድንጋጤ ፈጥሯል።

በትግራይና ኤርትራ ድንበር ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ምሽግ ውስጥ ህይወቱን የሚገፋውን ሰራዊትና ትጥቁን በከፊል ወደ ሌላ ግንባር ለማንቀሳቀስ የተለያዩ ሙከራዎች ቢደረጉም አልተሳካም። ትህነግ አፍ አውጥቶ ከልክሏል። መንገድ ገድቦ በገሃድም ባይሆን አግቶ ቆይቷል። ይህ ሲሆን ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በከፍተኛ ሚስጢር ሁለት ክፍለ ጦር አዲስ ሃይል አስመረቁ። ይህ አዲስ ሰራዊት እጅግ ዘማንዊ ውጊያ ስልት የተካነና ቀደም ሲል ከሚታወቀው ውጪ የዘመነ ትጥቅ መታጠቁ ለትህነግ ራስ ምታት ሆነ።

ከዚሁ ጎን ለጎን አየር ሃይል ወደ ዲጂታል ተዋጊነት ማደጉ፣ እጅግ ዘመናዊ ሰው አልባ ድሮንና ጀቶች ታጠቀ። ሸፍጥ እንዳይፈጸምበት ውስን ሰዎች ብቻ የሚቆጣጠሩት ታላቅ ተቋም ሆነ። የአየር ወለድና የኮማንዶው ሰራዊትም ብዛቱና ጥራቱ አድጎ ተዋቀረ። ትህነግ የጦርነቱን አቅጣጫ በማስፋት ሃይል በታትና ወደ አራት ኪሎ ለመግባት አቅዳ ነበርና ኦሮሚያ ሰፊ ሰራዊት እንድታሰለጥን ተደረገ። አማራ ክልል ቀድሞ ከነበረው በላይ አቶ ተመስገን ወደ አመራር ሲመጡ በጥራትም በብዛትም ሰፊ ሃይል ተገነባ። ይህ ሁሉ ሲሆን ትህነግ ለትግራይ ህዝብና ለኢትዮጵያ ታማኝ ሆኖ የኖረውን ሰራዊት ለመብላት ውስጥ ውስጡ እየሸረሸረ ነበር።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ትህነግ አገሪቱ ላይ በየክልሉ የተለኮሰውን እሳት በመቆስቆስ “ከመስከረም 25 በሁዋላ መንግስት የለም” በሚለው ሂሳብ ከኦሮሚያ፣ ከወላይታ እንዲሁም ከአንዳንድ ፓርቲዎችና ከቀድሞው የጸጥታ መዋቅሩ ጋር ስር ሰዶ የአብይን መንግስት ሊያስወግድ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ የዘመቻ መሪ ሆነ።

በኦሮሞና በአማራ ስም የተደራጁ የፌስቡክ አርበኞች ዘመቻውን ያራግቡ ያዙ። የአብይ መንገስት ሁሉን ችሎ ውስጡን እያደራጀና በግሩ እየቆመ ስለነበር ይህንን ውጥን ገለበጠ። የኦሮሚያ ባለ ሃይል ነን የሚሉትም የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ወደ ማረፊያ ወረዱ። ይህንን አስፈንጣሪ ተጭነው ያንብቡ ተምሳሳይ ሃሳብ ስላለው ለመረጃነት ይረዳዎታል። ወይም የመስከረም 25 ድራማ እንዴት እንደተቋጨ አጠቃላይ ሰዕል የሰጣል። የአንድነት ሃይሎች ካዱኝ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አዳዲስ ሰራዊት አዘምነው ማሰልጠናቸው ጊዜ ከሄደ ችግር ስለሚፈጥር ትህነግ የሰሜን ዕዝን ትጥቅ ጠቅልላ መውሰድ እንዳለባት ጌታቸው አሰፋ ወሰነ። ዘጎል ከትህነግ ቅርብ ሰዎች እንደሰማቸው ሃሳቡ ሙሉ በሙሉ ባያስደስትም የትህነግ አመራሮች መቃወም ስለማይችሉ ተቀበሉት።

ጌታቸው አሰፋ አካሄዱ ያልተመቻቸው መለስ ዜናዊ ሞት ቀደማቸው እንጂ ከሃላፊነቱ ሊያነሱት ወስነው እንደነበር የቅርብ አዋቂዎች ይገልጻሉ። የመቀሌው ተወላጅ እንደተፈራው መለስ እንዳረፉ ህወሃትን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቆጣጠረው። የትህነግ ምክትል የነበረው አባይ ወልዱ አስቀድሞም ሲሾም መለስን የሚገዳደል ሰው እንዳይኖር በሚል የተቀመጠ ነበርና ትህነግን በመላስ ሞገስ መምራት ቀርቶ ጥሩ ተመሪ እንኳን መሆን ሳይችል ተሰናበት። በዚሁ ሳቢያ አንጋፋዎቹ የየራሳቸው ቡድን ሰርተው የየራሳቸውን ጡንቻ ሲያፈረጥሙ ድርጅቱ ተናደ። ማዕከላዊነት ራቀው። ፈሪና ተፈሪ ጠፋ። ሳይታወቅ እየወላለቁ ሄዱ። በዛው መጠን ኦህዴድና ብአዴን አድብተው ከህዝብ አመጽ ጋር ሆነው ቁልቁል ነዷቸው።

ወደ ዋናው ሃሳብ ስመለስ ጌታቸው የአገሪቱ የድህንነት ተቋም መሪ እንደመሆኑ ብቻውን በስቶ ወጣና ከለውጡ በሁዋላ ነገሰ። ሁሉንም አግቶ ያሻውን ያደርግ ጀመር። መንግስት በይፋ ተፈላጊ በሚል የእስር ማዘዣ ያወጣበት ጌታቸው ከአገር ወጥቶ ለመኖርም ችግር ስለሚያጋጥመው የአብይ መንግስትን ለመናድ ጉድጓድ ሲምስ ቆይቶ መከለካይ ሰራዊት ትጥቁ እንዲዘረፍ፣ እንዲደመሰስ አምኖ አሳመነ።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

እንግዲህ ይህንን ውሳኔ ነው በውጭ አገር የሚኖሩና በአሜሪካና በታላላቅ አገሮች ቁልፍ ፖለቲከኞችንና ተጽዕኖ ፈጣሪ ጡረተኛ ፖለቲከኞችን ይዘው ሲነቀሳቀሱ የነበሩትን ያበሳጫቸው። እርግጥ ” ጦርነት ለትግራዋይ ባህላዊ ጨዋታ ነው” የሚል እምነትና ሰፊ ጦር መገንባቱ ተዳምሮ እንዲህ በአጭር ጊዜ መሰባበር ይፈጠራል የሚል እምነት ባይኖራቸውም፣ ጦርነቱ አሁን መጀመር አልነበረበትም በሚል ክፉኛ ንትርክ ውስጥ ገብተው እርስ በርስ እየተነታረኩ መሆኑን ለእነዚሁ ወገኖች ቅርብ የሆነ ለዛጎል አስታውቋል።

ምክንያታቸው ዲሞክራቶች ከበረሃ ትግል ጀመሮ አራት ኪሎ እስኪገቡ ድረስ የረዷቸው በመሆኑ፣ ይህንን ታሪክ ለማደስ ለባይደን ምርጫ ዘመቻ ትህነግ አሜሪካ ባሉት ከፍተኛ አጋሮቹ አማካይነት በምርጫው ዘመቻ ከፈተኛ አስተዋጾ አድርገው ሲሳተፉ ነበር። ከዝመቻው ጎን ለጎን ትህነግ ዳግም በምስራቅ አፍሪቃ ሰላም ማስከበር የሚችል ብቸኛው ድርጅት እንደሆነ የማሳመን ስራም እየተሰራ ነበር።

“የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት እንኳን ምስራቅ አፍሪቃን ሊያረጋጋ የሚመራትንም አገር ሰላም ማስጠበቅ አልቻለም” በሚል ዘመቻ ላይ ተጠምደው የነበሩትና ከፍተኛ ሃብት የከሰከሱት የትህነግ የውጪው አገር ታጋዮች ” ባይደን ወደ ስልጣን እስኪመጡ መጠበቅ ነበረባቸው። እኛ ምን እየሰራን እንደሆነ እያወቁ እንዴት ተጣድፈው ወደ እርምጃ ይገባሉ” የሚል መቃወሚያ እያነሱ ነው።

በዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና በላቸው መዋቅር፣ በማህበራዊ ሚዲያ ጭፍራዎቻቸውና በቴዎድሮስ አድሃኖም አማካይነት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስትን ለማሳጣት እጅግ በርካታ ሴራዎችን ሲያስፈጽሙ የነበሩት የትህነግ ሰዎች፣ በተለይም ጌታቸው አሰፋ የገንዘብ ኖት እንዲቀየር ሲደረግ የሰሜን እዝን መሳሪያ ዘርፎ ወደ ሃይል እርምጃ ለመዞር እንደወሰነ የመረጃው ሰዎች ያስረዳሉ።

እያንዳንዷ የርስዎ እርዳታ ከትንሿ ሳንቲም ጀምሮ የጠነክረናል። ዛጎልን ይርዱ 


Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0