“Our true nationality is mankind.”H.G.

የጁንታው መጨረሻ የዘላቂ ሰላም መጀመሪያ ነው!

አገራችን የተለያዩ ወጣ ገባ ታሪኮችን አስተናግዳለች። በአንድ ወቅት ገናና የነበረው ታሪኳ በዓለም ላይ ሁሉ የናኘና ለጥቁር ሕዝቦችም ጭምር ኩራት የሆነ ነው። ለዚህ የአድዋውን ድል ማንሳት ይቻላል።

በአንጻሩ ግን በየዘመኑ ስልጣን ላይ የወጡ ኃይሎች በሚከተሉት የፖለቲካ አካሄድና የግል ፍላጎት የተነሳ የሃገራችን ታሪክ ቀስ በቀስ እየተበላሸ የሄደበት ሁኔታ ተከስቷል። በዚህ የተነሳ ሕዝቡ በመንግስቱ ላይ አመኔታ አጥቶ ኖሯል።

ከዘመናት የሕዝብ ብሶት በኋላ ስልጣን ላይ የወጣው የኢህአዴግ መንግስትም በጥቂት የህወሓት አምባገነኖች ተጠልፎ የሕዝብ ሃብት የጥቂት ጁንታዎች መፈንጪያ ሆኖ ቆይቷል። በዚህ የተነሳም መላው የሃገሪቱ ሕዝብ ይህንን ኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ከጫፍ ጫፍ ተንቀሳቅሷል። እናም ይህ ኃይል በ2010 ዓ.ም ከስልጣን ተነስቶ በምትኩ የለውጥ ፈላጊው ኃይል ወደስልጣን ሊመጣ ችሏል፡፡

ይህ የለውጥ ኃይልም በማይታመን ፍጥነት በሃገሪቱ የነበሩ የተበላሹ አሰራሮችን በማስተካከልና ሃገሪቱን ለዘመናት ወደኋላ ሲጎትቱ የቆዩትን አሰራሮች በማሻሻል አዲስ የእድገትና የዴሞክራሲ በር ለመክፈት ሌት ተቀን መስራቱን ቀጠለ። ይህ ግን ስልጣን ለተነጠቀውና የሃገሪቱን ሃብት አላግባብ በመዝረፍ ያልተገባ የአኗኗር ሥርዓት ውስጥ ለተዘፈቀው የህወሓት የጁንታ ቡድን አባላት የሚዋጥ አልሆነም። የለውጥ ኃይሉ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረበላቸው የእኩል እንሁን ጥያቄም የበታች የሆኑ እስከሚመስላቸው ድረስ እንደንቀት በመመልከት ለውጡን ለማደናቀፍ ገና በጠዋቱ አገርን ወደማተራመስ እና ወደሽብር ተግባር ውስጥ ተዘፈቁ፡፡

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

ይህ የጁንታ ቡድን ታዲያ ጓዙን ጠቅልሎ ወደመቀሌ በመግባት ሕዝቡን በማስፈራራትና በተለያዩ ማደናገሪያዎችና የማታለያ መንገዶች ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥረት አደረገ። በተለይ የሕዝብን ስሜት ለመንካት በተለያዩ መንገዶች በከፈቱት የፕሮፖጋንዳ ስራ ሕዝቡ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ እንዲነጠል የሰራ ሲሆን፤ በዚህም ሌላው ሕዝብ እንዳገለላቸው በማስመሰል ራሱን እንዲነጥልና ከነሱ ጎን እንዲሰለፍ ያልማሱት ጉድጓድ፤ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም፡፡

ከዚያም ከፍ ሲል በሕገወጥ መንገድ አላግባብ ያከማቹትን ገንዘብ ለጥፋት ስራ በማዋል ሃገርን ለማበጣበጥ ተጠቀሙበት። በተለያዩ ክልሎችም ሕዝብና ሕዝብን ለማጋጨት ጥረት አደረጉ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ያሰቡት የሃገር ማፍረስ አደጋ ሊሳካላቸው አልቻለም። በዚህ የተነሳ ተስፋ ወደመቁረጥ በመሄድ በመጨረሻ ለሁለት አስርት አመታት ሲጠብቃቸው በኖረው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ቃታ ሳቡ። ይህ የመጨረሻ ድርጊታቸው ግን የሞታቸው ማፋጠኛ ነበር፡፡

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ምክንያቱም የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ ድሮም ቢሆን በነዚህ ኃይሎች ሲበደል የኖረ ነውና ጁንታው ባልጠበቀው ሁኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እነዚህን ኃይሎች ማስወገድ ለሃገራችን ሰላምም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እውን መሆን አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን በማመን የሕግ ማስከበር ስራውን በእልህና በወኔ ተያያዘው። ጁንታው ይህንን የሕዝብ ኃይል ለማስቆም አንዳችም አቅምም ሆነ ወኔ አልነበረውም። በዚህ የተነሳ መላውን የትግራይ አካባቢዎች ከጁንታው ቡድን ነፃ እያወጣ ሄዶ አሁን የመጨረሻው የሕግ ማስከበር ምዕራፉን በመቀሌ ላይ ማከናወን ጀም ሯል፡፡

ይህ የሰራዊቱ ተግባር እውነትን መሰረት ያደረገ በመሆኑም ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ በጁንታው ታፍኖ በቆየው የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትና ድጋፍ እያገኘ ይገኛል። ለዚህም በአንድ በኩል ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለመከላከያ ሰራዊቱ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች ፤ በሌላ በኩል ደግሞ መከላከያ ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው የትግራይ አካባቢዎች ህብረተሰቡ መከላከያ ሰራዊቱን እየተቀበለ ያለበት የደስታ ስሜት ማሳያዎች ናቸው፡፡

አሁን ለዘመናት ነቀርሳ ሆኖ የቆየው ይህ ጁንታ ኃይል ወደመቃብር የሚወርድበትና ግብዓተ መሬቱ የሚፈጸምበት ጊዜ ተቃርቧል። ቀጣዩ ስራ በችግሩ ሳቢያ ለሰብዓዊ ቀውስ የተዳረጉ ዜጎችን መልሶ ማቋቋምና ወደዘላቂ የልማት መስመር ማስገባት ነው። ለዚህ ደግሞ ለመከላከያ ሰራዊቱ ደጀን የሆነው ሕዝብ ይህንን ተግባር ጎን ለጎን እያካሄደ ይገኛል። በዚህም መሰረት አርቲስቶች የጀመሩት ስራ ተጠቃሽ ነው፡፡

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ትላንት አርቲስቶች “የሀገር ልጅ የማር እጅ” በሚል ለተፈናቀሉ ዜጎች የጀመሩት የድጋፍ ፕሮግራምም ትልቅ ማሳያ ነው። በዚህ ፕሮግራምም መተጋገዝ አገርን እንደሚያቆምና በተለይ በችግርና ጭንቅ ጊዜ የሚደረገው መደጋገፍ ትክክለኛ የአገር ወዳድነት መገለጫ መሆኑን አርቲስቶቹ ይናገራሉ። በመሆኑም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለአገሩ ዜጋ ብሔርና ሌሎች ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው ሊተባበር ይገባል፡፡

ይህ የጁንታ ቡድን ከዚህ ወዲያ የክፉ ታሪክ ማስታወሻ ይሆን እንደሆን እንጂ ተመልሶ ስልጣን ላይ የሚወጣበት እድል ሞቷል። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ግን ነገን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባትና ለውጡን ለማፋጠን እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሰሩ ይገባል። ከትላንት ይልቅ ነገ የተሻለ እድል ነውና በቀጣይ እያንዳንዱ ዜጋ ፊቱን ወደልማትና እድገት ማዞር አለበት፡፡

አዲስ ዘመን ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0