“Our true nationality is mankind.”H.G.

የወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ሳበስር በደስታ ነው… ቀጣዩ ትኩረት ክልሉን መገንባትና ሰብዓዊ እርዳታ ላይ ማተኮር ይሆናል” አብይ አሕመድ

A member of the Amhara Special Forces keeps guard at the 5th Battalion of the Northern Command of the Ethiopian Army in Dansha, Ethiopia, on November 25, 2020. (Photo by EDUARDO SOTERAS / AFP)

“በትግራይ የተጀመረው ወታደራዊው ዘመቻ መጠናቀቁን ሳበስር በደስታ ነው። አሁን ትኩረታችን ክልሉን መልሶ ማቋቋምና ሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ማድረጉ ላይ ነው። በተጓዳኝ የፌደራል ፖሊስ ተግባሩን ያከናውናል” አሉ አብይ አሕመድ። 
” መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ መላው የትግራይ ሕዝብ እንኳን ደስ አላቹህ፤ ሰራዊቱ ዛሬ ከሰዓት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል” የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ

ለስላሳ፣ ታጋሽ፣ ተለማማጭ፣ አቅም የሌለው መንግስት የሚመሩ … በሚል ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲወቀሱ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመከላከያ ሰአራዊት ላይ የግፍ ጭፍጨፋና ዘረፋ ከተካሄደበት ሰዓት ጀምሮ በትር እንዲነሳ ወሰኑ። በውሳኔያቸው መሰረት ዘመቻው ሲጀመር ሚሊሻውን፣ ሰራዊቱን፣ የደጀን ህዝብን አንድ ሆኖ ተነሳ።
በመከላከያ የሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመው ነውር ይፋ ከሆነበት ሰዓት ጀምሮ ቁጣው ድፍን ኢትዮጵያ ላይ ነደደ። አብይ አድብተው ያደራጁት አየር ሃይል አፎቱን አነሳ። በምድር ለምድር እንደ ዋላ የሚተመውን የአገር መከላከያ፣ ሚሊሺያና ልዩ ሃይል እያገዘ በትዕቢት የተነፋውን ሃይል በቀናት ውስጥ አበራዩት።
በወንድሞቹን እህቶቹ ጭፍጨፋ እንደ ግስላ የተቆጣው ሰራዊት ከደጀን ድጋፍና ወኔ ጋር ተዳምሮ በትግራይ ተራሮች ላይ ዘለለ። እርፍት ሳይፈልግ ግፈኞቹ ያስካዱትን ከሃዲና አገልጋይ በአረር እየጠበሰ መቀሌ ገባ።
የመከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል ሲሉ ጄነራል ብርሀኑ ጁላ የድሉን ብስራት አሰሙ። የ72 ሰዓታት ጊዜው ካበቃ በኋላ በሁለት ቀን ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት መቀሌን መቆጣጠሩ ድሉን ፈጣንና በአግባቡ የታቀደ እንደሆነ አስመሰከረ።
የቪኦኤ ዘጋቢ አዳነች ፍስሃዬ “አዋቂዎች ” በማለት በስም ያልጠቀሰቻቸውን አካላት ጠቅሳ የትግራይ ሃይል እጅግ የፈረጠመና ልምድ ያለው በመሆኑ የፌደራል መንግስት ሰራዊት የከፋ እጣ እንደሚገጥመው ዘግባ ነበር። እሷ ብቻ ሳትሆን በርካታ አፍቃሪ ትህነግ የሆኑ በተመሳሳይ የአገር መከላከያ ሰራዊት ዋጋ እንደማይኖረው ሲወተውቱ ነበር።
በሌላ በኩል ከፍተኛ ዝርፊያና ክህደት ተፈጽሞበት የተበተነና ራሱን በመካከል ላይ የነበረ ሰራዊት ዳግም አደራጅቶ፣ እንዲያገግም አድርጎ፣ ሞራሉን ገንብቶ በቀላት ውስጥ ታላቅ ውጤት ያስመዘገበውን ሰራዊት ” መታነው፣ ማርከነው፣ ትጥቁን አስፈትተን በተነው” ብለው የተሳለቁበት ከሃጂዎች ለሃጫቸው ሳይደርቅ አነቃቸው።
በዚህ እልሁ ከተራራ ተራራ እየተወረወረ ብራቁንና አረሩን ሲያነድ የነበረው የአገር መከላከያ ሰራዊት ነጻ ባወጣቸው ከተሞች የሚደረግለት ድጋፍና ልቡን እየጠገነው ድልን በድል እየደረበ ዛሬ አኩሪ ድሉን ጨበጠ።
የመከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ ሲያስታውቁ አገር በደስታ አነባ። ለትግራይ ነጹሃን፣ በተለይም በመቀሌ ከተማ ንጹሃን ሳይጎዱ ዘመቻው መጠናቀቁ ልዩ ደስታን ፈጠረ።
ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በመግለጫቸውም፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትናንትናው እለት የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዴት ከተማዋን መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ላይ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው የድል ዜናውን ሲያበስሩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ” ውሮ ወሸባዬ” አስከተሉ።
አብይ አህመድም ” ዘመቻው መጠናቀቁን ሳበስር በደስታ ነው” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ቀሪው ስራ የትህነግን ቧለማሎች መልቀምና ትግራይን ወደነበረችበት ሰላማዊ ህይወት መመልስ ይጀመራል።
በአሁኑ ወቅትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት በየጎሬው የተደበቁ የጁንታው የህወሓት አባላትን እያሳደደ እና እያደነ ሲሆን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀደም ብለው በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃም “በዚህ ዘመቻችን ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል” ሲሉ የዘመቻውን ረቂቅነት አስታውቀው ነበር።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”
0Shares
0