በህግ ማስከበር ዘመቻው ስማቸው ይፋ እንዳይሆን ሲባል በሚስጢር የተያዙ ከፈተኛ የትህነግ አመራሮችና የታጣቂ መሪ ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጎልጉል ታማኞች አመለከቱ። ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም  አስቀድሞም ከመቀሌ ባለመውጣታቸውና ጁንታው ጥሏቸው የሄደ በመሆኑ ነው መያዛቸው ይፋ እንዲሆን የተደረገው።
“አምባገነናዊ መንግስት ሲፈጠር ተባባሪ አልሆንም” በማለት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ያስታወቁት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ” በቃኝ” ማለታቸው እንደተሰማ በርካታ መረጃዎች መድመጥ ጀምረው ነበር። ወይዘሮዋ እጅ መስጠታቸው ሲሰማ ቀልብ የሳበው ጉዳይ ታዲያ ይኸው ከመሄዳቸው ጋር ተያይዞ ሲደመጥ የነበረውን ጉዳይ ይፋ ያደርጉታል በሚል ነው።
“የወይዘሮ ኬሪያ እጅ መስጠት ምንም ፋይዳ የለውም ግን መቀሌ የከተመውን ቡድን ወቅታዊ ቅርጽና ውሳኔዎች፣ እንዲሁም ዓላማ ከነገሩን መልቀቅ ነው” ሲል አቤል በፊስቡክ እንደጻፈው በርካቶች የሴትየዋን መያዝ ቢያቃልሉትም፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆናቸው ” ጁንታ ናቸው” በሚል ህግ እስኪፈርድ የግለሰቦች ፍርድ እንዲቆይ የሚጠይቁና የሚያራክሱዋቸው እጅግ ብዙ ናቸው።
” የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ፍጥነት መቋቋም አልቻልንም። ተሸንፈናል” ሲሉ ቃለ ምልልስ ማድረጋቸውን እንደሰማ ያስታወቀው ኢሳት ቃለ ምልልሱ መቼ እንደሚለቀቅ ባያውቅም በቅርቡ ይፋ ይሆናል ብሏል። የትህነግ ስራ አስፈጻሚ በመሆናቸው ሙሉ መረጃው በመንግስት መገናኛዎች እስከሚለቀቅ እየጠጠበቀ ነው።
ከአገሪቱ ታላቅ የስልጣን ወንበር በፈቃዳቸው ተሽቀንጥረው ወደ መቀሌ ያመሩት ወ/ሮ ኬሪያ በትህነግ አመራሮች መሰላቸታቸውን አሰቅድመው ይናገሩ ስለነበር ወደ ትግራይ ሄደው ” በቃኝ፣ ትግል ወይም ሞት፣ ዴሞክራሲ ሲቀበር ተሳታፊ ከምሆን ስልጣን ይቅርብኝ፤…” ሲሉ መደመጣቸው በቅርብ ለሚያውቋቸው የድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የመዝናኛ ያህል ነበር።
አንዳንዶች ” ባስቸኳይ ተጠርታ ይህንን ተናገሪ ተብላ ነው” በሚል ወ/ሮ ኬሪያ ያለ እምነታቸው ሲዘላብዱ እንደነበር ሲገልጹ፣ ልክ ” መንግስት ከመስከረም 25 በሁዋላ የለም” በሚል የመቀሌን ወታደራዊ ስለፍ ታምነው እንደተናገሩትና ፊትለፊት እንደገጠሙት ሁሉ እሳቸውም ትህንግ ዳግም ወደ ስልጣን ይመለሳል ሲል አስለተው እንደነበር የሚናገሩ ነበሩ።
ምንም ይባል ምንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ለመንግስት እጅ መስጠታቸውን የመንግስት ልሳኖች ይፋ ሲያደርጉ፣ በዝምታ ታልፎ እንጂ ሌሎችም በስም ያልተጠቀሱ የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊና የፖለቲካ አመራሮች በቁጥትር ስር መዋላቸውን ዛጎሎ አረጋግጣለች።
መንግስት በይፋ እንደገለጸው የተጎጂዎችን መጠን ለመቀነስ ሲባል ወደ አገረ ማሪያም የሸሸው ሃይል ቢተሰቦቻቸውንና ያገቱዋቸውን ንጹሃን ይዘው ለመከላከል ሙከራ ቢያደርጉም መቀሌ ከተያዘችበት ቀን ጀመሮ 360 ዲግሪ የነበረው ከበባ እየጠበበ መጥቶ ዛሬ ውጊያ እየተደረገ ነው። ጥቂት ባለስልጣናት ታማኝ ሃይላቸውን ይዘው ለመከላከል ቢሞክሩም ከሰዓት ወደ ሰዓት የተከበቡበት ቀለበት እየጠበበ መሄዱን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው።
በትናንትናው እለት በኢሳት በኩል ማብራሪያ የሰጡት አንድ ጀነራል ” ጁንታው እጁን በመስጠትና በመደምሰስ መካከል ነው” ሲሉ ነገሩ እያከተመ መሄዱን ገልጸው ነበር። እሳቸው ይህን ካሉ በሁውላ እንደሚሰማው ከሆነ ቀለበቱ ጠቦ የጁንታው መሪዎች የመሸጉበት ጉድጓድ ላንቃው ሊመታ የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ችግሩ ያገቱዋቸው ነጹሃን ዜጎች ጉዳይ ነው።
የመጨረሻውን ኦፕሪሽን እያካሄደ ያለው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከወይዘሮ ኬሪያ በተጨማሪ የያዛቸውን ሃይሎች ይፋ ማድረግ ያልፈለገው ሚስጢር በመጠበቅ ሌሎች እንዳይሸሹ ለመከላከል እንደሆነ ግምት ተሰጥቷል። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በርካታ ሃይሎች መያዛቸውን ታማኝ የመረጃ ሰዎች አረጋግጠዋል።
ከፍተኛ መኮንኖችና የመንግስት ባለስልጣናት እንዳረጋገጡት ሰፊ ቁጥር ያላቸው የሚሊሻና የልዩ ሃይል አባላት እጃቸውን ሰጥተዋል። እየሰጡ ነው። እግር አውጪኝ በማለት ወደ ተከዜ የሸሸው ሃይልም ቢሆን እጅ ከመስጠት የተሻለ አምራጭ የለወም። ይህ በንዲህ እንዳለ የትህነግ አመራሮች ከምሽግ ሆነው የመከላከል ውጊያው በሶስት አቅጣጫ እየተካሄደ መሆኑንን እየገለጹ ናቸው። በዚህም ውጊያ ድል እየቀናቸው መሆኑንንም እየተቀሱ ነው። አካባቢውን የሚያውቁ ጁንታው የተንቤንን ህዝብ ተገን አድርጎ እየተጠቀመ ቢሆንም እንዳሰበው እንዳልተሳካለት እየገለጹ ነው።
ከስር ከስር በጽሁፍ መልዕክት ደረሰኝ በሚል መሪውን ደብረጽዮንን ጠቅሶ የሚዘግበው ሮይተርስ አሁን መጨረሻ ላይ እነሱ ድል እየተቀዳጁ መሆኑንን ጠቁሞ ዘገባውን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ድል ደምድሞታል። በጽሁፉ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የተናገሩትን ቃል በቃል እየጠቀሰ ነገሩ ያከተመ አስመስሎ አቅርቦታል።
በሌላ ዜና ድምጸ ወያኔ ሲገለገልበት የበበረውን ድብቅ ስቱዲዮ የመንግስት ሃይሎች በጥቆማ እንደተቆጣጠሩትና አስፈላጊ የምርመራ ስራ ከሰሩ በሁዋላ ወደ ዋና የማስተላለፊያ ህንጻ ማምራታቸው ታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *