በቅርቡ የፌዴራል መንግስት በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ ማቅረብ ተግባር መሆኑን በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ገለፁ፡፡ በቅርቡ የፌዴራል መንግስት በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ የወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃን በተመለከተ በጀርመን ዶቸ ወሌ ቱ ዘ ፖይንት ፕሮግራም ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ በተመለከተ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን እንዳሉት ከዚህ በፊት በመንግስት የቀረቡ የሰላም አማራጮችን መለስ ብሎ ማየት እንደሚያስፈልግ አንስተው በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ይለው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ አክለውም እየተካሀየደ ያለውን ህግ ማስከበር ተግባር ጦርነት ለማለት ሁለት ሉዓላዊ ሀገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚያደርጉት ውጊያ ሲሆን መሆንን አንስተው ÷ይህ ግን መንግስት ያቀረበውን የይቅርታና የእርቀ ሰላም አማራጭ ካለመቀበል ባለፈ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ወንጀለኞችን በማደን ለህግ ለማቅረብ ያለመ ዘመቻ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

በውይይት ላይ የተሳተፉት አቶ አስፋወሰን አስራቴ በበኩላቸው መንግስት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ጥረቶችን ማድረጉን እንደሚያውቁ ገልጸውል፡፡

አምባሳደር ሙሉ በህወሃት ጁንታ ቡድን አንዳንድ የግንኙነት መስመሮች ቢቋረጡም በማይካድራ በሚኖሩ የሌሎች ብሔር ተወላጆችና በመከላከያ ሰራዊት ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደጨፈጨፈ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማወቁ ሰላማዊ ሰውች ላይ ስለነበረው ሁኔታ ለማወቅ ያስችል እንደነበር አስረድተዋል፡፡

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

አንምባሳደር ሙሉ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሁንም በሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን በቀጣናውና በአፍሪካ አህጉር ሰላም እንዲሰፍን እየሰሩ መሆኑንም ከዶቸ ወሌ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገሪቱ ሁሉን አቀፍ ለውጥ እንዲመጣ ሲሰሩ የነበረውንና በአንጻሩ ህወሃት ለውጡ እውን እንዳይሆን በርካታ የጥፋት ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር አቶ አስፋወሰን አስራቴ አብራርተዋል፡፡

አቶ አስፋወሰን በውይይቱ ላይ እንዳሉት በዶክተር አቢይ የመደመር አስተሳሰብ የትግራይ ህዝብ ታሪክ ለኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ ወሳኝ መሆኑን እንደተቀመተ አንስተው÷ ነገር ግን በጁንታው የተሳሳተ አመለካከት የተበላሹ አሰራሮች የሚስተካከሉ መሆኑን አንስተው፤ ላለፉት 30 ዓመታት በህወሃት መሪነት ወቅት ከሀገሪቱ ውሳኔ ሰጭነት ሳይሳተፉ የነበሩ ህዝቦችን ወደ ሙሉ ተሳታፊነት ማምጣት መቻሉ እውነተኛ የፌዴራሊዝም ስርዓትን ለመተግበር የሚያስችል አስተሳሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም በቅርቡ የሀገሪቱ 10ኛ ክልል ሆኖ የተመሰረተው የሲዳማ ክልል ዋቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

በመጨረሻም አምባሳደር ሙሉ የዚህ ወንጀለኛ ቡድን መጠለያ ድርጅት ስያሜ እስካሁን ነጻ አውጭ ድርጅት ነኝ የሚል ሲሆን ማንን ከማን ነጻ እንደሚያወጣ የማይታወቅ ይልቁንም በትግራይ ህዝብ ስም ሲነግድና ለወንጀል መፈጸሚያ መሳሪያ አድርጎ ሲጠቀምበት ለበርካታ ዓመታት መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ለዚህም ባለፉት 2 እና ከዛ በላይ አመታት በሀገሪቱ የተፈጠሩ ችግሮችን በማቀድ߹ በማስተባበር߹ በቁሳቁስና በገንዘብ ሲደግፍ እንደቆየ አመላክተዋል፡፡

(ኢዜአ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *