የህወሃት ጁንታ ታሪክ ይቅር የማይለው የሀገር ክህደት እንደፈጸመባቸው በደባርቅ በኩል ወደ አማራ ክልል የገቡ የሰሜን እዝ አባላት ገለጹ። የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 600 የእዙ አባላትን በመቀበል የምግብ የመኝታና የህክምና አገልግሎት በመስጠት የወገን አለኝታነቱን እያሳየ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሰሜን እዝ የ7ኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር አባል ሀምሳ አለቃ ገዛኸኝ በቀለ ”ባላሰብነውና ባልጠበቅነው መንገድ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አሰቃቂ ግድያና አፈና ፈጽሞብናል” ብለዋል፡፡

የተፈጸመው ጥቃት የሰራዊቱን አባላት በብሄር ማንነት ለመለያየት በመሞከር ጭምር እንደሆነ የገለጹት ሃምሳ አለቃ ገዛኸኝ “ከግድያና ከመቁሰል የተረፍነውን ለ10 ቀናት በማጎሪያ ካምፕ በቀን አንድ ደረቅ ዳቦ እየተሰጠን ሰብአዊነት የጎደለው እንግልት ደርሶብናል” ሲሉ ተናግረዋል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

በሰሜን እዝ አባላት ላይ የደረሰብን ግፍና መከራ ከኢትዮጵያዊነት እሴቶቻችን ያፈነገጠና በረሃብ አለንጋ ጭምር እንድንቀጣ ያደረገ ነው” በማለት የተናገረው ደግሞ ሻለቃ ባሻ ግርማ ወንድማገኝ ነው፡፡ እጅግ አሰቃቂ በሆነ አያያዝ ለአስር ተከታታይ ቀናት በእስር በቆዩባቸው ጊዚያት በቀን አንድ ደረቅ ዳቦ እየተሰጠው መቆየቱን ተናግሮ በሌሊት በመኪና አጓጉዘው ተከዜ ድንበር ላይ በረሃ ላይ ጥለዋቸው እንደሄዱ ተናግሯል፡፡

ከአራት ቀን የእግር ጉዞ በኋላ በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ በህይወት ተርፈው መድረሳቸውን ተናግሮ በርካታ ጓደኞቹ በርሃብና በውሃ ጥም እንዲሁም ገደል ገብተው ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

የትግራይ ልዩ ሃይል ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍና በደል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል በሆንነው ላይ ፈጽሞብናል ያለው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባል  ሃምሳ አለቃ ሰለሞን ነጋሽ ነው፡፡

“ረሃብና ውሃ ጥም ተቋቁመን ከተከዜ ተነስተን ከሦስት ቀናት የእግር ጉዞ በኋላ ሰሜን ጎንደር ስንገባ ህዝቡ ባደረገልን አቀባበል እጅግ ተደስተናል የሞራል ስብራታችንም ታድሷል ሲል” ተናግሯል፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ጀጃው ደማሙ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከሦስት ሺ 600 በላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላትን በመቀበል የምግብ፣ የመኝታና የህክምና ድጋፍ ጭምር እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Related stories   ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

በተለይ ከፍተኛ እንግልት የደረሰባቸውን የሰራዊቱን አባላት ከደባርቅ ሆስፒታል ጋር በመቀናጀት አምቡላንስ መድቦ የህክምና ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ህግ በማስከበር ለተሰማራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንቅ ድጋፎችን ማድረጉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ENA – Reported

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *