የአገር መከላከያ ሰራዊት ልዩ ኮማንዶ ወርቅ አምባ ላይ ማህለቁን ጥሏል። ወርቅ አምባ ተምቤን የምትገኝ ተራራማ ትንሽ ከተማ ስትሆን የጁንታው አመራሮች ለጊዜው ዋና ምሽጋቸው አድርገው መርጠዋታል። የአገር መከላከያ ሰራዊት አገረ ለላምን ሲቆጣጠር ወደ ወርቅ አምባ የተሽቀነጠረው ቡድን ዛሬ አመሻሽ ላይ እንደተሰማው ከሆነ የመጨረሻው ተቃርቧል።
የደብረፅዮን ጠባቂዎችና የኢትዮጵያ መከላከያ ኮማንዶዎች ፊለፊት ተፋጠው እየተያዩ መሆናቸውንና ከበባው ካሁን በሁዋላ ወደ ሌላ አካባቢ ለማምለጥ የሚያስችል እንዳልሆነ እየተገለጸ ነው። ይህ በሚገለጽበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትግራይን መልሶ ለማቋቋም የመንገድና ተዛማጅ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተጠገኑ መሆናቸውን በቲውተር ገጻቸው ተናግረዋል።
” ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው። ይህ ተግባር ሦስት መልኮች አሉት። ሰብአዊና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የተጎዳውን መሠረተ ልማት መልሶ መገንባት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር። እነዚህ ሥራዎች በስፍራው በተገኙ ቡድኖች አማካኝነት ተጀምረዋል። የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎትም እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች በመደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል። አንድ ሆነን የተቋረጠውን እናስቀጥላለን፣ የፈረሰውን እንገነባለን፣ የነገውንም እናለማለን።”
ወርቅ አምባ፣ ደብረጽዮን ፣ጌታቸው ረዳ፣ አቦይ ስብሀት ፣አባይ ፀሐዬ እንዲሁም ከሰሜን እዝ ከድተው የተቀላቀሉ ጀነራሎች እና የትግራይ ልዩ ሐይል መሪ አብረው እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
ወርቅ አምባ በቆላ ተምቤን የምትገኝ ተራራማና አነስተኛ ከተማ ስትሆን። ከመቀሌ ያፈገፈገው የትህነግ ቡድን በቅድሚያ ወደ ሀገረ ሰላም ቢሸሽም፣ እግር ለግር እየተከተለ የማሰቢያ ሰዓት የነሳቸው የማጥቃት እቅድ ወደ ወርቅ አምባ እንዲሸሹ አስገድዷቸዋል።
ባዶ ስድስት እየተባለ የሚጠራው የህወሓት እሥርቤት የሚገኘውም ከአማራ ክልል አዋሳኝ በቆላ ተምቤን ነው። የመጨረሻው ፍልሚያ ሊሆን የሚችለውም እዚሁ አካባቢ እንደሚሆን ግምት አለ። እንደ አቶ ተመስገን አባባል ከሆነ ደቂቃዎች እየቆጠሩ ነው። ባዶ ስድስት እጅግ በርካታ ሚስጢር ያለበት፣ ግፍ ሞልቶ የፈሰሰበት ስፍራ ብመመሆኑ ጁንታው በመጨረሻ ሰዓት ሚስጥሩ እንዳይወጣበት ሊያወድመው እንደሚችል ከወዲሁ ግምት አለ። ጎልጉል ሰሞኑንን በርካታ የበላይና የመካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሶ ዛሬ ማለዳ ላይ መዘገቡ አይዘነጋም።
የዜናው መነሻ – የአቶ ተመስገን ጥሩነህ  ገጽ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *