“Our true nationality is mankind.”H.G.

የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና  የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሞምባሳ – ናይሮቢ -አዲስ አበባ – ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚደንት ኡኹሩ ኬንያታ በሞያሌ የሚገኘውን የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ዛሬ ጎብኝተዋል። የፍተሻ ጣቢያው መመረቅ በሞያሌ ድንበር የነበረውን ልዩ ልዩ እክል አስቀርቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ያሳልጣል ተብሎ ይታመናል።
በተጨማሪም፣ ሁለቱ መሪዎች የሀዋሳ-ሞያሌ 500 ኪ.ሜ አስፋልት መንገድን አስመርቀዋል። በኢትዮጵያ በኩል የተጠናቀቀው ይህ መንገድ ከኬፕ ታውን እስከ ካይሮ የሚዘረጋው የአፍሪካ አሕጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል ነው። ከጋራ ፍተሻ ጣቢያው የድህረ መሠረተ ልማት ግንባታ ሙዐለ ነዋይ ፍሰት ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያ እና የኬንያን የንግድ ትስስር ለማጠናከር የታለመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞያሌ የጋራ  የፍተሻ ጣቢያ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የሞንባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው እና የ500 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሃዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ የሁለቱን ሀገራት ብሎም ቀጠናው በተለያዩ ዘርፎች በማስተሳሰር በኩል የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የተመረቀው መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጭ የተደረገበት ሲሆን ወጪው በአፍሪካ ልማት ባንክ የረጅም ጊዜ የብድር ድጋፍ የተሸፈነ መሆኑ ታውቋል።

መንገዱ በመስመሩ ለሚገኙ ከተሞች የእርሻ እና የኢንደስትሪ ዞኖች እና የቱሪስት መዳረሻወች በዘመናዊ መንገድ ከማስተሳሰሩ ባለፈ የኢትዮጲያ እና የኬኒያ መንግስት የሁለትዬሽ የንግድ ልውውጥ ግንኙነትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0