ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ 40 የቀድሞ የአየር ሃይል፣ የመከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትእዛዝ ወጣ።
በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት የተጠረጠሩ ሜ/ጄ ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ አርባ (40) ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
Image may contain: 3 people, beard and textImage may contain: 6 people, text
 Image may contain: 6 people, textImage may contain: 4 people, beard and text
Image may contain: 1 person, textቀደም ሲል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው በተለያየ የኃላፊነት እርከን ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች በተጨማሪ በሀገር ላይ ጥቃት ለመፈፀም በማቀድ በግንባር የተሰማሩና ጥቅምት 24 /2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተካሄደውን አሳፋሪ የእገታ ተግባር እንደመሩና እንዳስተባበሩ በምርመራ የተደረሰባቸው አርባ (40) የከዱና በጡረታ የተገለሉ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል ብሏል ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ፡፡
መላው የሀገሪቱ ህዝብ በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የህዋሓት የጥፋት ቡድን አባላት አድኖ ለሕግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
መቀሌ ከተማ የገባው የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን በሚያደርገው አሰሳና ኦፕሬሽን የሚገኙ ውጤቶችን እየተከታተለ በመገናኛ ብዙኃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
(አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በቡድን ተደራጅተው የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት ተከሳሾች ከ18 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *