የሴኮቱሬ የልጁ ባለቤት አብነት ኃይሉሸዋ በሚኖርበት መኖሪያ የተገኘው ሁለት የእጅ ቦምብ፣ 17 የእጅ ሽጉጥ እና ሌሎች መሳሪያዎች ሴኮቱሬ በመኝታ ቤቱ ያስቀመጠው እንጂ የኔ አይደለም ሲል ተከራከረ።ተጠርጣሪው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቧል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምርመርራ አባልም በተጠርጣሪው ላይ የሰራቸውን የምርመራ ስራዎችን ለችሎቱ ገልጻል።ተጠርጣሪው ሀገርን በመካድ በሀገሪቱ ላይ ጥቃትና አመጽ እንዲንቀሳቀስ ከሚሰሩ የህወሓት የጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር ተልዕኮ ተቀብሎ ሲሰራ እንደነበር መረጃ ሰብስቤያለው ሲል መርማሪ ፖሊስ ለችሎት አስረድቷል።
በዚህ መሰረትም “በርካታ የምርመራ ስራዎችን አከናውኛያለሁ፤ ተጠርጣሪው በሚኖርበት መኖሪያ ቤትም ብርበራ አድርጌ ሁለት የእጅ ቦምብ፣ 17 ሽጉጥ 30 ፍሬ የክላሽ ጥይት እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች አግኝቻለሁ” ሲል ነው የገለጸው።እንዲሁም ያገኛቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ለቴክኒክ ምርመራ መላኩንና ለቀሪ ምርመራ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪው “ሴኮቱሬ የባለቤቱ አባት ነው፤ እኔ የምኖርበት ቤት ቀደም ሲል በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ለሌላ ተሰጥቶ የነበረና በተዘጋው የሴኮቱሬ መኝታ ቤት ውስጥ ነው ቦምቡና መሳሪያዎቹ የተገኙት፤ እኔን የሚመለከቱ አይደሉም” ሲል ተከራክሯል።ጉዳዩን የተከታተለው ችሎትም ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ ሰባት ቀናት የፈቀደ ሲሆን፥ በችሎቱ ሌሎች ጉዳዮችንም ተመልክቷል።
Via FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በቡድን ተደራጅተው የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት ተከሳሾች ከ18 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *