ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

መቀሌ ስትያዝ “ጦርነት ላማረው ና በለው” ክፍል አንድ

እድሉ ሊኖር ቢችልም በጦርነቱ ልንሞት እንችላለን የሚል ስጋት ብዙም አልነበረብንም። ከባዱ ስጋታችን በማይካድራ እንደታየው በመቀሌም ሊደገም ይችላል የሚለው ነበር። በዚሁኔታ ሳለን ገና የተፈላው ቡና እንደተቀዳ መቀሌ ተኩስ እንደ ጎርፍ አጥለቀለቃት። የሚተኮስ መሳሪያ ኖሮት ያልተኮሰ አልነበረም። መቀሌ ያሉ መሳሪያዎች ሁሉ ያለማቋረጥ በከተማው በሞላ እየተተኮሱ ነው። በቀላሉ መሳሪያ እንደ ሀይለኛ ዶፍ ዝናብ መቀሌ ላይ ዘነበ። ይህ ተኩስ ያለማቋረጥ ለ 5 ሰዓታት በላይ የዘለቀ ነበር። ተኩሱ የመኪናዎች ጥሩንባ እና የወጣቶች ጭፈራ በአንድ ላይ ቀጥሏል። በየ አደባባዩም ወጣቶች “ጦርነት ላማረው ና በለው” እያሉ ይጨፍራሉ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ይሳደባሉ።

Tajebe Jenber – ታጀበ ጀንበር የባንክ ባለሙያ ምስክርነት

ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት እንደወትሮም ባይሆን መቀሌ በየመንገዱ ሰው ይታይ ነበር። መንግስት የሰጠው የ72 ሰዓት የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ እነ ጌታቸው ረዳ እንደሚያጣጥሉት ሳይሆን የሰው ስጋት ከ አርብ ጀምሮ ከወትሮው መጨመሩ አልቀረም። እኛም በጠዋቱ ቁርሳችንን በልተን እኩለ ቀን አካባቢ ባረፍንበት ፔንሲዮን ቡናችንን አስፈልተን ከመቀሌ ዙሪያ (ምናልባት ከ 15-25 ኬሎሜትር ርቀት ላይ) የሚዘንበውን የመድፍ መዓት በስጋት ውስጥ ሆነን እየሰማን ነው።
በከተማ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት እጅጉን አሳስቦናል ጁንታው የከተማ ውስጡን ጦርነት አጥብቆ የሚፈልገው እንደሆነ እናውቃለን በይፋም ይሄን ሲቀሰቅሱ መክረማቸውን ሰምተናል። በብዙ የረዳችን ቡና የምታፈላልን የፔንሲዮኑ እንግዳ ተቀባይ የሆነችው ሴት ጭንቀታችንን አይታ “አማራ እናንተ ብቻ አይደላችሁም አትፍሩ” ብላ ልታፅናናን ብትሞክርም አባባሏ አስገርሞናልም አስደንግጦናልም። በዚሁ አጋጣሚ ትግሬ ያልሆነ ሁሉ አማራ እንደሚባልም ሰምተናል።

እኛ ካለንበት ፊት ለፊት ያለ ሌላ ፔንሲዮን በጥይት ሲመታም እንዲሁ ተመልክተናል። ህንፃውን በጥይት የመቱት ሆን ብለው አልነበረም መሳሪያ እየተኮሱ ካሉት እድሜያቸው ከ 14 ያላለፈ ህፃናት በቁምጣና በሲሊፐር ክላሽ ይዘወ የወጡ በቂ የአተኳኮስ ክህሎት የሌላቸው ወጣቶችም ስለነበሩ ጭምር ነበር። በዚህ ምክንያት ምናልባት ሌሎች ቦታዎች ላይ የከፋ ጉዳት ደርሶም ሊሆን ይችላል።

እድሉ ሊኖር ቢችልም በጦርነቱ ልንሞት እንችላለን የሚል ስጋት ብዙም አልነበረብንም። ከባዱ ስጋታችን በማይካድራ እንደታየው በመቀሌም ሊደገም ይችላል የሚለው ነበር። በዚሁኔታ ሳለን ገና የተፈላው ቡና እንደተቀዳ መቀሌ ተኩስ እንደ ጎርፍ አጥለቀለቃት። የሚተኮስ መሳሪያ ኖሮት ያልተኮሰ አልነበረም። መቀሌ ያሉ መሳሪያዎች ሁሉ ያለማቋረጥ በከተማው በሞላ እየተተኮሱ ነው። በቀላሉ መሳሪያ እንደ ሀይለኛ ዶፍ ዝናብ መቀሌ ላይ ዘነበ። ይህ ተኩስ ያለማቋረጥ ለ 5 ሰዓታት በላይ የዘለቀ ነበር። ተኩሱ የመኪናዎች ጥሩንባ እና የወጣቶች ጭፈራ በአንድ ላይ ቀጥሏል። በየ አደባባዩም ወጣቶች “ጦርነት ላማረው ና በለው” እያሉ ይጨፍራሉ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ይሳደባሉ።
የተኩስ እሩምታው ያለ እረፍት ሲዘንብ ፎቅ ላይ ከምንሆን መሬት ይሻላል ብለን ሁላችንም ወደ መሬት ወረድን። እኛ ካለንበት ፊት ለፊት ያለ ሌላ ፔንሲዮን በጥይት ሲመታም እንዲሁ ተመልክተናል። ህንፃውን በጥይት የመቱት ሆን ብለው አልነበረም መሳሪያ እየተኮሱ ካሉት እድሜያቸው ከ 14 ያላለፈ ህፃናት በቁምጣና በሲሊፐር ክላሽ ይዘወ የወጡ በቂ የአተኳኮስ ክህሎት የሌላቸው ወጣቶችም ስለነበሩ ጭምር ነበር። በዚህ ምክንያት ምናልባት ሌሎች ቦታዎች ላይ የከፋ ጉዳት ደርሶም ሊሆን ይችላል።
በመቀሌ ቆይታችን ብዙ ዓይን በዝቶብን በጣም በጎ ሰዎች የመኖራቸውን ያህል የሰውም ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየተለወጠ ከዚህ ቀደምም አንድ ጓደኛችን ትግሪኛ መናገር ባለመቻሉ ብቻ ፀጉረ ልውጥ አማራ ናችሁ በሚል አንዲት ሴት ለፖሊስ አመልክታ ሁላችንም ወደ ፖሊስጣቢያ ተወስደንና ተፈትሸን ፖሊሶቹም የእያንዳንዳችንን አድራሻ እና ያለንበት የአልጋ ቁጥር መዝግበው ስለነበር ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያጠቁን የሚመጡ ሰዎች እንዳይኖሩ የሚል ስጋት ስላደረብን የፔንሲዮኑን በር አዘግተን ሁላችንም እንግዳ መቀበያ ክፍል ተቀምጠናል። አንዳንዶቻችን ቢመጡ በየት በኩል ዘለን ማምለጥ እንደምንችል እያሰላሰልን ነው።
እንግዳ ተቀባይዋ በህንፃው ዙሪያ እና ከተማው በሞላ በተኩስ እየተናጠ ምንም ሳይመስላት ግቢ በማፅዳት ስራዋ ላይ ተሰማርታለች። በዚህ መሀል በሩ በሀይል ተንኳኳ ባይከፈት ደስተኞች ነን በሩ ተከፈተ እማማ ናቸው ተበሳጨን በዚህ ሰዓት ለምን ያሳቅቁናል እማማ ካረፍንበት ፔንሲዮን አጠገብ አነስ ያለች ግሮሰሪ አላቸው ከግሮሰሪያቸው በረንዳ ጠፍተው አያውቁም ስንወጣ ሆነ ስንገባ ከበረንዳቸው ተቀምጠው ሰላም እንዳሉን ነው። ከመቀሌ በዓብአላ በኩል ለመውጣት ስንሞክር የዛሬን አያድርገውና ስንቱን ሸሽጌ ከጦር አስመልጬ ልክያለሁ መሰላችሁ ስልክ ጠፋኝ እንጂ እናንተንም እልካችሁ ነበር አዬዬዬ ምን ያደርጋል ይሉናል። ዛሬ በዚህ ቀውጢ ሰዓት ለምን እንደመጡ አናውቅም። ከ እንግዳ ተቀባይዋ ጋር ጥቂት ካወሩ በኋላ ኸረ ውጡ ተኩሱ የደስታ ነው ውጪውን እዩት አይ ማዘር ይቅርብን ብለን መለስናቸው።
እኚህ እናት እኛን ለማጥቃት የሚፈልጉ ሰዎች እስካለንበት ፔንሲዮን ድረስ መጥተው እዚህ የሉም ብለው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ለአንደኛው ጓደኛችን እንደነገሩት ነገሩ ካበቃ በኋላ አጫውቶናል።በቆይታችን ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮች የገጠሙንን ያህል እንዲህ ያሉ ብዙ ደጋግ ሰዎችም ገጥመውናል።
ለደስታ እንዲህ ያለ ተኩስ? እሺ ህዝቡ በዚህ ተኩስ መሀል ሻንጣውን አንጠልጥሎ ለምን ይሰደዳል። አንደኛው ጓደኛችን ፎቅ ላይ ሆኖ አንድ የልዩሀይል አባል ለማምለጥ ሲንደፋደፍ መመልከቱን ነግሮናል ሁኔታው ምንም የደስታ ሊመስለን አልቻለም። ሂዊ የሆነ ሴራ እየወጠነች መሆኑ ገባን። እንግዳ ተቀባይዋ ፈገግ ብላ ይሄ የአቢዩ ተላላኪ የሆነው ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተማርኳል ለዛ ደስታ ነው ተኩሱ ወጥታችሁ እዩ አለችን። አይ ደስታ¡ ጄኔራሉን ሊማርኩት እንደማይችሉ እርግጠኞች ነን ማርከውት ከሆነ እንኳን መንግስት እርምጃውን ይበልጥ ያጠናክራል እንጂ እንደማያፈገፍግ እናውቃለን።
ዜናው እንደ ሁልጊዜው የውሸት በሆን ብለን ተመኘን። የህንፃው ጥበቃ ቻይና የ 72 ሰዓቱ ገደብ ከማለቁ በፊት ወደ ቤተሰቦቹ ይሁን ወደ ጦር ግንባር ስራውን ለቆ ሄዷል። እንግዳ ተቀባይዋም የሪሰፕሽኑን ቁልፍ ሰጥታን በተኩሱ መሀል ወደ ቤቷ ሄዳ እኛ ብቻ ቀርተናል። ከመካከላችን ደግሞ ጠያቂ እንኳን ቢመጣ ትግሪኛ መናገር የሚችል አንድም ሰው የለም።
ማታ 1 ሰዓት አካባቢ አልፎ አልፎ ከሚሰማ ተኩስ በቀር ሁሉም ነገር ፀጥ አለ። ይሄ ማማሟቂያ ነው ዋናው ጦርነት የሚጀመረው ነገ ነው አልን።ሁላችንም መንግስት ዛሬ መቀሌን ምናልባት ተቆጣጥሮ ከሆነ በፍፁም ሊታመን የማይችል ነው አድናቆታችን በቃላት መግለፅ የምንችለው አይሆንም አልን። እርስበርስ ስናወራ ድምፃችንን በጣም ቀንሰን ነው። አይደለምና ዛሬ ሌላም ቀን በመንገድ ስንሄድ ሆነ ምግብ ስንበላ አማሪኛችን ጎልቶ እንዳይሰማና ሊያጠቁን ሊፈልጉ የሚችሉ ሰዎች ቢኖሩ በቀላሉ ሊለዩን እንዳይችሉና ወደዛ እንዳንመራቸውም ጭምር የቻልነውን ያህል እንጠነቀቃለን። ይህ ማለት ግን ሁሉም እንደዛ ነበር ከጥቃት ሊያስመልጡን የሚችሉ ተጋሩዎች አልነበሩም ማለቴ አይደለም።
ልክ 1:30 ሲሆን ቴሌቪዥኑ ሊያሰማ የሚችለውን የመጨረሻው ዝቅተኛ ድምፅ ላይ አድርገን ፋና ዘጠና መስማት ጀመርን። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማ ገባ አሉ የሚል ዜና እየተነገረ ነው። መቀሌ ገባ እንጂ መቀሌን ተቆጣጠረ የሚል ነገር ባለመስማታችን ዜናው ብዙም አላስደነቀንም ነበር ድንገት ሰበር ዜና የሚል ፅሁፍ መጣ በጉጉት ስንጠብቅ ሰበር ዜና ብለው የመጀመሪያውን ዜና ደገሙት በቃ የሆነ ነገርማ አለ ዜናው አልደረሰላቸውም ማለት ነው እያልን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ብቅ ብለው መከላከያ ሰራዊት መቀሌን መቆጣጠሩንና ጁንታውን የመለቃቀም ስራ ብቻ እንደቀረ አበሰሩን። በመከላከያ አስደናቂ ጀግንነት ከተማዋ ምንም ሳትሆን ያለ ምንም ውድመት መቆጣጠር መቻሉ መግለፅ ከምንችለው በላይ ሆነብን።
የመቀሌን ህዝብ ጄኔራል ባጨ ደበሌን ማርከናል በሚል የውሸት ዜና በደስታ አዘልለው ጥሩንባ እያስነፉ መሳሪያ እየተኮሱና እያስተኮሱ ጥግ ጥጉ ላይ ግን ልዩሀይላቸው የቻለው መለዮውን አውልቆ ያልቻለ ከነመለዮው እግሬ አውጭኝ ብሎ ይሮጣል። ህዝቤ በደስታ ሲዋኝና ሲሸልል ዋናዎቹ ጁንታዎች ወደ ሀገረሰላም እየፈረጠጡ ነበር። ከዛን ቀን ጀምሮ መቀሌ ላይ ብዛት ያላቸው የልዩ ሀይል አባላት መለዮአቸውን አውልቀው ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለዋል።
በዚህ ቀንም ሆነ በማግስቱ መከላከያ ምንም እንኳን ጁንታዎቹን ከመቀሌ ቢያባርርም ሰራዊቱ ከተማዋን ማረጋጋትና ህዝቡን ከዘራፊዎች መታደግ ግን አልቻለም ነበር። የተደራጁ የከተማው ወጣቶችና በኋላም እንደሰማነው ጁንታው መሸነፉ አይቀሬ መሆኑን ሲረዳ ከየ እስርቤቱ በነፃ የለቀቃቸው የወንጀል ፍርደኞች ተደራጅተው በተለይ ንግድ ቤቶች ላይ በመኪና ሳይቀር እየጫኑ ከፍተኛ የሆነ ዝርፊያ ፈፅመዋል። ህዝቡም ራሱን ከዝርፊያ ለመከላከል ሌቦች ላይ መተኮስ ጀምሮ የሞቱ ስለመኖራቸው በአይናችን ባናይም ሰምተናል። በጣም የሚያስደንቀው ነገር ሂዊዎች የዘረፉን ኤርትራዊያን ናቸው ከማለታቸው በላይ የራሱ ልጆች ሲዘርፉ እያየ ኤርትራዊያን በአፋር አድርገው ገብተው ዘረፉን የሚሉና የሂዊን ቃል ከአይናቸው በላይ የሚያምኑ በብዛት (ምናልባት ወደ 90% የሚጠጉ) መኖራቸው ነው።
ይቀጥላል…
ፎቶ – የአገር መከላከያ ሰራዊት ወደ መቀሌ ሲቃረብ
Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”