“Our true nationality is mankind.”H.G.

በቤኒሻንጉል ጉዳይ “አማራ ክልል ትዕግስቴ አልቋል” አለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በንጹሃን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እና በደል መሸከም የማይቻልበት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን የአማራ ክልል የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ የአማራና የአገው ህዝብ ተቻችሎና ተመሳስሎ አዳሪ እንጂ ገፊ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ፣ የአገው ፣ የሽናሻ እንዲሁም ንፁሀንና ሀቀኛ የማኮ ፣ በርታና ጉሙዝ ህዝቦች በራሳቸው ዞን ሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ተከብሮ ያለ ስጋት የሚኖሩበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ብለዋል።
በተዛባው የትህነግ የሐሰት ትርክትና በተስፋ ቅሌት ውስጥ የገባው ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ የመሸገው ትንሹ ጁንታና የትህነግ የግልቢያ ፈረስ በአማራ ፣ በአገው ፣ በሽናሻና በሀቀኛና በንፁሀን ማኦ፣ ጉሙዝ ህዝቦች ላይ የሚያደርሰው ግፍና በደል የሚቋጭበት ጊዜው አሁን ነውም ብለዋል።
ኦነግ እና አንዳድ የክልሉ መንግሥት አመራሮች ፣ የጎህዴን ፓርቲ አባላት ከጡት አባታቸው ከትህነግ ጁንታ ትምህርት ይወስዱ ብለን የታገስንበት ትዕግስታችንን ከእቁብ ባለመቁጠር አርሶ ያበላው፣ ከማዕዱ ያካፈለውን ፣ ደካማ የሥራ ባህላቸውን እና ኋላቀር ስልጣኔአቸውን በመቀየር የስልጣኔን በር የከፈተላቸውን ህዝብ ቀዩ የሚል ተቀጽላ ስም በመስጠት ግፍ እየተፈጸመበት መሆኑን አንስተዋል።
የአማራና የአገውን ማኅበረሰብ ተወልዶ ባደገበት ፣ በገዛ ቀየውና ሐገሩ በሽዎች የሚቆጠሩትን በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ በማፈናቀልና ሀብት ንብረታቸውን በመዝረፍ ከፍተኛ በደል እየፈፀሙበት ኖረዋል አሁንም እየፈፀሙበት ይገኛሉ ነው ያሉት።
በእነዚህ ሰው በላ አረመኔ ቡድኖች ምክንያት ከአንድ ቤተሰብ ከ2 እስከ 12 የሚሆኑ ንፁሀን በግፍ ተገድለዋል። ከማህፀን ውስጥ ካለ ህፃን እስከ አዛውንት ያሉ ቤተሰቦቻቸውን የተነጠቁ የአማራ እናቶች፣ አባቶችንና መላውን አማራ አስለቅሰዋል ፤ ጥቁር ማቅም አስለብሰዋል ሲሉ የግፉን ጥግ ተናግረዋል።
በመሆኑም አሁን ህዝባችን እየደረሰበት ያለውን ግፍና በደል መሸከም የምንችልበት ትዕግስታችን አልቆ ፣ተማጽኗችንም አልሰማ ብሎ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ከታሪክ እንኳን የማይማሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ ትንሹ የጁንታ ቡድን የትህነግን ተልዕኮ በመፈጸም የእስካሁኑ አልበቃ ብሏቸው አሁንም ያለሀፍረት በማንኩሽ ጫፍ አልጣሽ ፓርክ አካባቢ እንዲሁም በጉምሩክ ጠረፍ የከማሸ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ፣ የትህነግ ፍርስራሾችና እርዝራዦች ፣ የጎህዴፓን ፓርቲ አባላትና አንዳንድ የክልሉ አመራሮችና የፀጥታ መዋቅሮቻቸው ጭምር ተባብረው በተለምዶ ቀይ ብለው የሚጠሩትን (አማራ፣ አገውና ሽናሻን) አንዳንዴም ሌሎች ንፁሀንና ሀቀኛ የሆኑ ጥቂት የበርታ፣የማኦ፣የጉሙዝ ማህበረሰብ አባላትን የማጥፋትና የማፈናቀል ዘመቻ በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑን መረጃዎች እንደሚያሳዩ ተናግረዋል።
የአማራና የአገው ህዝብ የሚደርስበትን ግፍ ለሀገር አንድነት በሚል በበዛ ትዕግስት ማሳለፋችን እንደፍርሀትና ሐጥያት ተቆጥሮ ያለከልካይ በሽዎች የሚቆጠሩ በግፍ ተገለዋል፥ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ተፈናቅለዋል ፤ ሀብትና ንብረታቸውን በግፈኞች ተዘርፈዋል ነው ያሉት አቶ ግዛቸው።
ግፉን እንደወትሮው ሁሉ አዝነንና መግለጫ አውጥተን የቤንሻንጉል ጉምዝ መንግሥትን ተለማምጠን የምናልፍበት ጊዜ አብቅቷል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ።
በክልሉ ውስጥ የአማራና የአገውን ህዝብ እረፍት ለመንሳት የተሰማሩ ገዳይ ቡድኖች የሚተማመኑበት የትህነግ ቡድን እንዴት አካርካሪውን መትተን ግብአተ መሬቱን እንደፈጸምን አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ሲገባ ፤ በህዝባችን ላይ የሚያደርሱት በደል ከልክ ስላለፈ የመጀመሪያውን የትግል ምዕራፍ በታላቅ ጀብድ ማጠናቀቃችን ይታወሳል።
ቀሪው የቤት ስራችን ምናልባትም የህዝባችን መብት ለማስጠበቅ በቤኒሻንጉል ክልል በተጠለሉት የትህነግና የኦነግ ሸኔ ፍርስራሽ ጁንታዎች ላይ እርምጃ የምንወስድበት ሁለተኛው የትግል ምዕራፍ መሆኑ አይቀሬ እየሆነ መጥቷል ብለዋል።
ችግሩ በተለመደው መንገድ ይፈታል የሚል የሞኝ እይታ የለንም፣ የህዝባችንን በደል ፣ ሞትና እንግልት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚከስምበት ጊዜውና ወቅቱ አሁን ነው ሲሉ አስታወቀዋል ።
የህዝባችን ግፍና በደል ለመካስ በየትኛውም መልኩ የሰው ደም መጣጮች ከያሉበት ጥሻና ምሽግ ታግለን ፣ ለህግ ለማቅረብና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ብለዋል።
የአማራና የአገው ህዝብ ተቻችሎና ተመሳስሎ አዳሪ እንጂ ገፊ አይደለም። አብረውት የሚኖሩ ህዝቦችን ከማዕድ አካፍሎ ፣ ስልጣኔ አስተምሮ ወደ ተሻለ ህይወት እንዲሸጋገሩ ባደረገ ሞት የፈረዳችሁበት ህዝብ ይታገሳል እንጂ ከተነሳ የጀመረውን ሳይጨርስ አይተኛም ነው ያሉት።
በመሆኑም እናንተ የሽናሻና ንፁሀን የሆናችሁ ግድያውን ማፈናቀሉን ንብረት መዘረፉን የማትደግፉ የሌሎች ብሄረሰቦች አባላት የትህነግና የኦነግ ሸኔ ፍርስራሽ ጁንታዎችን በማስወገድና ለህግ በማቅረብ በሚደረገው የህግ ማስከበር የትግል ምዕራፍ አብራችሁን እንድትሰለፉ ጥሪያችን ይድረሳችሁ፣ ከማንኛውም ህግ ከሚያስከብር አካልና ቡድን ጋር ሁሉ በመተባበር ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል በመግለጫቸው።
ለነዚህ ትናንሽ የጁንታው ፍርስራሽ አካላት ለዘመናት የህዝባችን ጠላት ሁኖ የኖረው ትህነግ የጋታቸውን የሐሰት ትርክ አስተንፍሶ ፣ የአማራ፣ የአገውና ሌሎች ንፁሀን ሀቀኛ ህዝቦች በተወለዱበት ቀያቸው ፣ ባደጉበት ሀገርና በራሳቸው ዞን ሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ተከብሮ ያለ ስጋት የሚኖሩበት ጊዜም እሩቅ አይሆንም ሲሉ አስገንዝበዋል።
ዜናው የ (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”
0Shares
0