“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ጀግና ያደርጋል እንጂ አይፎክርም ስለሆነም እንዳትፎክሩ” አብይ አሕመድ መቀሌ – ” መቀሌ ዙሪያ እየተዋጋን ነው ” ትህነግ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ” ጀግና ያደርጋል እንጂ አይፎክርም፣ ስለሆነም አትፎክሩ፣ ከገጠምን እናሸንፋለን እናንተ የጦር መሪዎች ይህንን በልባችሁ አኑሩ” ሲሉ ለጦር ከፍተኛ ሹማንትና መኮንኖች መናገራቸው ተጠቆመ። የትህነግ ሃይል መቀሌ ዙሪያ እየተዋጋ መሆኑንን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። ዘገባው ምንጮቹን እንዴትና በመን መልኩ እንዳገኛቸው አላሰፈረም።
ወደ ስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮና ቀደም ብሎ እንዳይመረጡ ሰፊ ዘመቻ የተካሄደባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህንን ያሉት መቀሌ በመገኘት ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።

የመንግስት መገናኛዎች እንዳስነበቡት አብይ አሕመድ መከላከያ በኦፕሬሽኑ  እቅድ መሰረት ጦርነቱን መጠናቀቁን አመክተው  ሰራዊቱ በህግ ማስከበሩ ሂደት ለሰራው ስራም አመስግነዋል።


የአገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ከጠቅላይ ሚ9ኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት፣ ምስል ከጠ/ሚ ፌስ ቡክ

“ሰራዊቱ በጋራና በአንድነትና በጀግንነት የተሰጠውን ስራም መቶ በመቶ አሳክቷል፤በተሰራው ስራ በጣም ደስተኞች ነን የኢትዮጵያ ህዝብም ኮርቶባችኋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር፣ “ወንጀለኞችን የመያዙን ስራ ባጠረ ጊዜ ጨርሰን ወደ ልማት ስራችን መሄድ ያስፈልገናል” በማለት ነገ ዛሬ ሳይባል ትግራይ ዳግም ህይወት እንድትጀምር ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። መመሪያና አቅጣጫም አስቀምጠዋል።

@AbiyAhmedAli Went to Mekelle and met with commanders of the ENDF as well as the Provisional Administration of Tigray. Telecom & electricity currently being restored after repairs; infrastructure works underway & humanitarian relief provided. We will continue apprehending the criminal clique.

“በጦርነት ተፈትነው ያሸነፉ ጀግኖች አፍርተናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ጀግንነታችሁ በውጊያ ብቻ አይደለም፤ በልማቱም እንጂ” ሲሉ በሰራዊቱ ቁመና እንደሚኮሩ ገልጸዋል። በዚሁ የኩራትና የእምነት መንፈስ “ጀግና ያደርጋል እንጂ አይፎክርም ስለሆነም እንዳትፎክሩ፣ከገጠምን እናሸንፋለን እናንተ የጦር መሪዎች ይህንን በልባችሁ አኑሩ”  የሚል ታላቅ ምክረ ሃሳብ በያንዳንዱ ልብ ውስጥ አስቀምጠዋል። “አያይዘውም ወታደር በመሆኔ በጣም ኮርቻለሁ” ሲሉ የሰራዊቱ አካል በመሆናቸው የሚሰማቸውን ክብር ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደርና አግባብ ካላቸው ወገኖች ጋርም ውይይት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል። እርዳታና አስፈላጊ ግብአቶች በስፋት የሚቀርቡበት መንገድ እንዲመቻች፣ እስካሁንም የርዳታ አቅርቦቱን የእለት ደራሽ እገዛው በምን መልክ እየሄደ እንደሆነ
ሮይተርስ ዛሬ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ መግባታቸውን ሲዘግብ የትህነግ ሃይል በመቀሌ ዙሪያ አሁንም እየተዋጋ መሆኑንን አስፍሯል።
Abiy government declared victory over the TPLF after its forces took control of the regional capital, Mekelle, on Nov. 29. The TPLF has said it is continuing to fight from mountains surrounding Mekelle.  አብይ ሕመድ በኖቬምበር 29 መቀሌ መያዟን ሲያበስሩ የትህነግ ሃይሎች መቀሌ ዙሪያ ባሉ ተራሮች ሆነው ውጊያ መቀጠላቸው ዘግቧል። ለምን ዓላማ ይህንን እንደዘገበ ባይታወቅም ዜናውን ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት ጋር አያይዞታል።
በተደጋጋሚ የተዛባና ወገንተኛ ዜና በመስራት የሚታውቀው ሮይተርስ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ የገቡት ትህነግንና መንግስትን ሊያሸማግሉ እንደሆነ ነባር የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል። ሮይተርስ እንዲህ ቢልም በተደጋጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ከጁንታው፣ መከላከያን ካረደው … ጋር ድርድር አይታሰብም” ሲል ለሕዝብ አስረግጠው መናገራቸው የሚታወስ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ
0Shares
0