ሃያ ዠጠኝ በመቶ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ በሴፍትኔት ይተዳደራል። ከ500 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርባት የክልሉ መዲና መቐለና ሌሎች ቦታዎች ንፁህ የሚጠጣ ወሃ የላቸውም። ይሄን ሳታስተካክል፣ የህዝባችን ድምፅ ሳትሆን፣ ህወሓት ጋር ስታጫፍር፣ ስታሽቃብጡ ቆይታቹህ አሁን “ህዝባችን” ስትሉ ትንሽ ሃፍረት የለም?
Image may contain: 3 people, outdoor
የ70 እንደርታ መሬት ሲዘረፍ ወጣቶች አስተባብረን መንግስት ጋር ስንጮህ የት ከርማቹህ ነው ዛሬ የህዝብ ተቆርቋሪ ለመሆን የምትሞክሩት? ያኔ የህዝብ ድምፅ እነ ነብዩ ስሑል ሚካኤል ሲታሰሩ የት ነበራቹህ ዛሬ “ህዝባችን” የምትሉ?
ቤታቸው በውስጥ ለውስጥ ተሽጦ “ከቤታቹህ ውጡ ቤታቹህ አይደለም” ተብለው ሲባረሩ በንዴት እናቶች ሲታነቁ ድምፅ ስንሆናቸው እናንተ የት ነበራቹህ ያኔ?
ለህዝብ ድምፅ ሁነን ስላስጨነቅናቸው በእነ ጌታቸው ረዳ ተጠርቼ “እየሰራሀው ያለሀው ስራ ጥሩ አይደለም ወይ ከኛ ጋር ስራ ወይ ፌስቡክህ አጥፋ” ተብዬ ቀጭን ትእዛዝ ሲሰጠኝ የት ነበርክና ነው ዛሬ “ህዝቤ” ብለህ የምትጮሀው።
Image may contain: 4 people, closeup
የህዝብ ደምፅ ስንሆን ከገበሬው ጎን ስንሆን ብዙ ወጣት መሬት እንዲያገኝ እንዲጠቀም አድርገናል የአይናለም፣ የኩሓ፣ የሰራዋት፣ የደብሪ ወጣት ይመስክር፤ እኛ ግን 70 ካሬም አልወሰድንም እኛ የተረፈን ስድብ ነው ባንዳ ተባልን፣ ከሃዲ ተባልን፣ ሚልዮን ዶላር ከኣብይ ተቀበሉ ተባልን፣ ሃገር ሸያጮች ተባልን፣ ጓደኞቻችን በኛ ሰበብ ታሰሩ፣ ቤተሰቦቻችን በኛ ምክንያት ተሰደቡ እንዲሸማወቀቁም ተደረገ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሰፊው ተከፈተብን።
ያኔ ስታሽቃብጡ እኛ የህዝብ ድምፅ ነበርን ዛሬም ህዝባችን ከቤተሰባዊ አገዛዝ ለማውጣት እየታገልን ነበር በመጨረሻም ድል ተቀዳጀን። ዛሬም ከህዝባችን ጎን ነን።
Image may contain: 2 people
ሁሌም ሊነጋ ሲል ይጨልማል ለውጥ ደሞ ዋጋ ሳይከፈልበት አልጋ ባልጋ ሁኖ አይመጣም። ዛሬ ህዝባችን ተቸግሯል፣ ተጠምቷል ይሄ ሳይከፈል ለውጥ የሚባል አይመጣም።
አንድ ነገር ግን ርግጠኛ ነኝ የነገ የትግራይ ህዝብ መፃኢ እድል ብሩህ ነው ይሄ እስኪሆን እስከመጨረሻ እታገላለሁ።
Image may contain: 1 person, outdoor
ዛሬ ግን ህዝቤ ስትሉ ያሳፍራል ህዝባችን አታቁትም፤ ጩሀታቹህ ለጥቅማቹህ ነው አሳይለም ለማግኛ፣ ጥቅማቹህ ስለተቋረጠ ነው ጭሆታቹህ ህወሓት ስለፈረሰ ህወሓትን ለማዳን ነው እንጂ ለህዝቡ አይደለም ህዝቡ አታቁትም።
ለናንተ ኢጎ፣ ጉራ ሲባል የድሃው ልጅ እንደ ቅጠል ረግፏል እናንተ ግን የተሻለ ሃገር እየኖራቹህ ጀግና እያላቹህ ደሙ አፍልታቹህ ወጣቱን አስጨረሳቹሁት ይሄ ነው የናንተ ህዝባዊነት።
አሁንም ህዝባችን ከቤተሰባዊ የአገዛዝ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተገላግሏል። አሸንፈንም አልፎከርንም ዝም ስንል ግን ዝም አታስብሉም “ህዝባችን” ስትሉ ያለ ህፍረት በህዝባችን ትነግዳላቹሁ፤ በህዝባችን መነገድ ይብቃ እንታገላቹሃለን እርቃናቹህ አውጥተን በህዝብ ፊት እንደምናዋርዳቹህ አልጠራጠርም።
ትላንትም ዛሬም ከህዝባችን ጋር ቁመናል ወደ ከፍታ እንዲጓዝም እንሰራለን !
Amanmichael Mesfin ሊንኩን ስሙ ላይ በመጫን ጽሁፉን ከጸሃፊው ገጽ ላይ ማግነት ይቻላል

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *