መቀሌ በተያዘች ማግስት – ለፌስቡክ አንባቢ እንዲሆን አጥሮ የቀረበ – ታጀበ ጀንበር ። እዛው የነበረ አማኝ።
መቀሌ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጅ መውደቋን ከመገናኛ ብዙሀን ብንሰማም የህወሀት አፈቀላጤዎች ያሳዩት የነበረው መደናገጥና ከፊታቸው ይነበብ የነበረው ሽንፈትና ተስፋ መቁረጥ ብንታዘብም እንዲሁም እነ ድምፂ ወያነ ከዋሻ ውስጥ ሆነውና ኮስሰው የተለመደችዋን ፉከራቸውን እየተጣጣሩም ሲፎክሩ ብንሰማም እውነትም መቀሌ በመከላከያችን ቁጥጥር ስር መሆኗን አምኖ ለመቀበል የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ላይ ሲጎማለል የማየት ጉጉታችን ወሰን አልነበረውም። ሌሎች ሶስት የስራ ባልደረቦቻችን ያረፉት ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዝቅ ብሎ መናኸሪያ አካባቢ ወደ ዳገቱ ጠጋ ያለ አካባቢ ነበርና በአካባቢያቸው የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ተመልክተው እንደሆነ ደውለንላቸው ማየታቸውን ሲነግሩን ልባችን እርፍ እኛም እፎይ አልን።
እንዴት ደወላችሁ ለሚል አንባቢ ጦርነቱ እንደተጀመረ መቀሌም ሆነ አጠቃላይ ትግራይ የስልክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ቢሆንም ስሙን የማልጠቅሰው የመቀሌ ኗሪ የራሳቸውን የቴሌ መገናኛ ይፈጥራሉ ይሰሩታል እንዳለን ከተወሰኑ ቀናት በኋላ መቀሌ ውስጥም ሆነ ከመቀሌ አቅራቢያ ወዳሉ የትግራይ ከተሞች ስልክ መደወልና መቀበል ተችሎ ነበር። ይህ አገልግሎት መቀሌ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ከዋለች ጥቂት ቀናት በኋላ ተቋርጧል።
አንደኛው ከእኛ ጋር አብሮን የነበረ የስራ ባልደረባችን ውጊያው ወደ መቀሌ በተቃረበበት ሰዓት ምን ታይቶት እንደሆነ ባናውቅም እዚህ መሀል ከተማ ከመሆን ወደ ዳር መጠጋት ይሻላል ብሎ አዱሽሁምድሁን ወደተባለና እንደ ድሚፂ ወያኔ፣ ትግራይ ሚዲያ ሀውስ እና የህወሀት ፅ/ቤት የመሳሰሉ ታርጌት የሚደረጉ ተቋማት በአቅራቢያው ወዳሉበት ማረፊያውን ቀይሮ ነበርና መቀሌ በኢትዮጵያ መከላከያ በተያዘችበት ቀንም እዛ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ተኩስ ስለነበር በአካባቢው ከነበሩት ሰዎች ጋር አብሮ ከከተማ ውጪ እስከመሰደድ ደርሶ ማታ ነገሮች ሲረጋጉ እኛ ወዳለንበት ተመልሶ ቢመጣም እኛ ከነበረብን ስጋት አንፃር ቀድመን ቤቱ ለማንም እንዳይከፈት በማለታችንና የሱን ወደኛ መምጣት ባለማወቃችን ጎረቤታችን የሆኑት ባለ ግሮሰሪዋ እማማም ለእኛ ደህንነት ሲሉ ሊያስገቡት ባለመፍቀዳቸው ወደ መጣበት ተመልሶ በማግስቱ ወደኛ ሲመጣ በመንገዱ መከላከያዎችን መመልከቱን ነግሮናል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማየታቸውን ጓደኞቻችን ቢነግሩንም በዓይናችን እስክናያቸው ያለን ጉጉት ወሰን የነበረው አልነበረም።
የተወሰንን የፎቁ ጫፍ ላይ ወጥተን የከተማውን እንቅስቃሴ ቃኘን የሚታይ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረም። ጥቂት ሰዎች አልፎ አልፎ ይንቀሳቀሳሉ በጣም የተወሰኑ ታክሲዎችም እንዲሁ አልፎ አልፎ እልፍ ሲሉ ይታያል እንደ ትላንቱም ባይሆን የተኩስ ድምፅ በአቅራቢያችንም ሆነ ራቅ ብሎ ይሰማል ከዚህ በተረፈ ከተማዋ ፀጥ ብላለች። አንደኛው ባልደረባችን ታድያ የፎቁን ደረጃ ሲወርድ እኛ ካለንበት በቅርብ ርቀት ያለ ያላለቀ ፎቅ ላይ የክልሉን የፖሊስ መለዮ ከነ ኮፊያው ለብሶ ምናልባትም የታጠቀ ሰው ዙሪያውን ሲቃኝ መመልከቱንና ድምፃችንን ከፍ አድርገን እንዳናወራና እንዳንጯጯህ ይነግረናል። ግራ ተጋባን ያየኸው ሰው የፖሊስ ልብስ ለብሷል? አጥብቀን ጠየቅነው አዎ ከነ ኮፊያው። ከደቂቃዎች ዝምታ በኋላ አየሁት ወዳለን ቦታ ብናማትርም ምንም የሚታይ ሰው አልነበረም።
ይህ ቀን ይመጣል ብለን ከጥይት ብናመልጥ በረሀብ እንዳንሞት ነብሳችንን ለማቆየት ብስኩቶች፤ ቸኮሌት፤ውሀ ገዝተን አንዳንዶች ከብስኩትና ቸኮሌት በተጨማሪ ለእለታቸው የሚበቃቸውን ቆሎ ቆጥረው እየቆረጠሙ 😂 ቅዳሜና እሁድን አሳለፍን። በቀጣዮቹ ቀናት ምስጋና ለእንግዳ ተቀባይዋ ሳምሪ ይግባና ምግብ በቀን ሁለቴ እንዲመጣልን አድርጋልናለች። ይሄ ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እራት የበላንበት ቀን በቁጥር ነው። ይህን የምናደርገው የምናማርጠው ምግብ ባይኖርም ቅሉ የሚበላ ምግብ በከተማው ሳይኖር ቀርቶ አልነበረም ጦርነቱ አንድ ወር ይቆይ 6 ወር የምናውቀው ነገር ባለመኖሩ ምክንያትና ባንኮችም ዝግ በመሆናቸው በእጃችን ያለንን ገንዘብ አብቃቅተን የመጠቀም ግዴታ ስለነበረብን እንጂ።
ሳምሪን መከላከያ መቀሌን ስለመቆጣጠሩና በመንገዷ የመከላከያ ሰራዊት ተመልክታ እንደሆነ ስሜቷን ሊጎዳው ስለሚችል ልንጠይቃት ባንፈልግም መከላከያ ሰራዊት መመልከቷንና በመንገድ የሚንቀሳቀሰውን ሰው መታወቂያ እንደሚጠይቁና ስልክ እንደሚፈትሹ እኛም በስልካችን የህወሀትን ነገር ከያዝን እንድናጠፋ (የማንን አርማና ፎቶ በስልካችን ልናኖር እንደምንችል ብታውቅም) ነግራን እኛም ኸረ እኛ በስልካችን ምንም የለም ምንም አያገኙም በቃ ምንም አትስጉ አሁን ደህና ነው እያለች እንደወትሮው ታበረታታናለች።
ይህን ጊዜ የአንድ ሰው ትዝ አለኝ ስሟን አላውቀውም አምና መቀሌ በነበርኩበት ወቅት ካረፍኩበት ፔንሲዮን ፊት ለፊት ትንሽዬ ግሮሰሪ ነበራትና ጉሮሮዬ ሲደርቅ ጎራ እል ነበር ስልክ መለዋወጣችንን አስታውሳለሁ Grocery የሚል ስም ከማህደሬ ፈለኩ ደወልኩላት መቀሌ ተይዟል የሚባለው እውነት ነው? እናንተ አካባቢ ሁኔታው እንዴት ነው? እየሳቀች ምን ሃሃሃሃሃሃ ዐብይ ደብረፂዮንን ሊይዝ ሃሃሃሃሃሃ ኸረ ደብረፂዮንን አይደለም መቀሌን ነው ያልኩሽ እየሳቀች አውቀው እኮ ነው የለቀቁላቸው ኦህ እንደሱ ነው እንዴ ታድያ ሰፈራችሁ እንዴት ነው? መከላከያዎች አሉ እኔ ከቤት አልወጣሁም የወጡ ሰዎች መከላከያዎች መታወቂያና ስልክ እንደሚያዩና የህወሀት አባል የሆነ እንደሚገድሉ ነግረውኛል። ኸረ መከላከያ እንደዛ አያደርግም ውሸት ነው መከላከያ የህዝብ ጠባቂ እንጂ ሰውን የህወሀት አባል ስለሆነ ብቻ አይገድልም ብላትም ልታምነኝ ሳትችል ተለያየን።
አብዛኛው ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ከተማረ እስካልተማረ የህወሀት ፕሮፖጋንዳ እንደ እውነት በመቁጠር መከላከያ ይገድለናል በሚል ስጋት ብቻ ከተማውን ለቆ ወደ ጫካ ለመሸሽ ተገዷል። ቀስ በቀስ ነገሮች እየተረጋጉ ሲመጡ መከላከያ ህዝቡን ሊጠብቅ መጣ ሊሉ ባይችሉም ህዝቡን የሚተናኮል አለመሆኑንና የተባለው ውሸት መሆኑን ሲገነዘቡ የተወሰኑት ትተውት ወደሸሹት ቤታቸው መመለስ መጀመራቸው አልቀረም።
በቦታው አብራችሁኝ የነበራችሁ ሙሉውን ሁነት ማካተት ባለመቻሌ አፉ በሉኝ እያልኩ ሌሎች ገጠመኞቻችን ይቀጥላሉ
 • ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!
  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሃላፊ ሆነው ለስድስት ወራት በሃላፊነት የቆዩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በዛሬው እለት ከስልጣን መነሳታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በምትካቸው ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም የሆኑት ዶ/ር አብራሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። ዶ∕ር አብርሃም በተለያዩ የመንግስትContinue Reading
 • የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤
  በተጨማሪም በውጭ በተለያዩ ሀገራት ሆነው ይህንን ህቡዕ አደረጃጀት ሲያስተባበሩ እንዲሁም የፋይናንስ፣የሃሳብና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ፣ አቶ ተሻለ ከበደ ኢዶ፣ወይዘሮ የሀረርወርቅ ጋሻው፣ አቶ አስፋው ጀቤሳ፣ አቶ መዕረግ፣ አቶ ቢኒያም፣ አቶ ኪሩቤል፣ ወይዘሪት ሊሻን አህመድ፣ ዶ/ር ገነት፣ ወይዘሮ አረጋሽ፣ ኢንጀነር ሊሻን ግዛውና አቶ ሀገሬ አዲስ በወዳጅ ሀገራት ትብበርና  ከኢንተርፖል Continue Reading
 • የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ
  በበዓሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የደረሰችው አባቶቻችን እና እናቶች በከፈሉት መሰዋእትነት ነው ብለዋል። በጊዜው የነበሩት አርበኞቻችን ታላቅ ነበሩ፤ ሀገር መገንባት ከባድ ነው ማፍረስ ግን ቀላል ነው፤ ሁሉም ሀገሩን መጠበቅ አለበት ነው ያሉት። ልጅ ዳንኤል ጆቴ ሰላም በቀላሉ አይገኝም፤ ችግሮች የትም አሉ፤ የኛContinue Reading
 • “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ
  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች በከተማዋ አስተዳደር ስር ባሉ የጤና ተቋማት በሙሉ ነፃ ህክምና እንዲሰጥ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል። የከተማ አስተዳደሩ 80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከነፃ ህክምና አገልግሎቱም በተጨማሪ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የጠየቀው መሬት እንዲሰጠው መወሰኑንም ምክትል ከንቲባዋ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። በበአሉContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *