“Our true nationality is mankind.”H.G.

” ኢትዮጵያ በእናንተ እጅ ናት፤ ከድል በሁዋላ ጓዳዊ ፍቅራችሁን፣ መከባበራችሁን፣ አንድነታችሁን ጠብቁ” አብይ አህመድ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመቀሌ ቆይታቸው ከሀገር መከለከያ ሰራዊት አመራሮች ጋርም በድሉ ዙሪያ ውይይት
አድርገዋል፤ በዚሁ ወቅት የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ባይደግሙትም ዘወትር ” ኢትዮጵያ ያላችው በመከላከያ ሰራዊት ልቡናና አዕምሮ ውስጥ ነው” ይሉ ነበር። ይህንኑ አጠናከረው ከመቀሌ ተመልሰዋል።
👉 ጠላት በርከት ያሉ የእኛን መኮንኖች ይዞ ስለቆየ እነሱን ይዞ ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ ስለሆነም ማታ ማታ በምናደርገው ኦፕሬሸን በርከት ያለ ሰው በሚኖርበት ሰአት ይህ ሀይል የእኛ ሃይል ሊሆን ይችላል በሚል ያቆየናቸው ሚሳየሎችና ቦንቦች ዛሬ ያኮሩኛል። ያንን ተጠቅመን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመካከላችን ያሉትን መኮንኖች አናያቸውም ነበር፤
👉 ይህ ኢትዮጵያን የመታደግ ኢትዮጵያን የማኩራት ብቃት፤ ተልዕኮን በአጭር ጊዜ የመፈጸም ብቃት የተቋማችን የሁልጊዜ አርማ መሆን አለበት፤
👉 በተደጋጋሚ እንዳልኩት የመከላከያ ሰራዊት የብልጽግና ሰራዊት አይደለም፤ የአብይ ሰራዊት አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መከታና ኩራት የሆነ ወታደር ነው፤
👉 እኛ የምንፈልገው ፕሮፌሽናል ጠንካራ አርሚ እንድትሆኑ እንጂ ለአንድ ፓርቲ የሚገዛ እንድትሆኑ አንፈልግም፤
👉 ኢትዮጵያ ከብልጽግናም ከፓርቲም በላይ ናት፤ ትልቋን አገር የመታደግ ሃላፊነት ተጥሎባችኋል፤
👉 ፖለቲካው የተበላሸ ነው፤ የማያውቀውን የደም ስር እና ሀረግ እየፈለገ የሚቧደን ነው፤ እናንተ ግን ጀግኖች ብቻ ሳትሆኑ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፤
👉 ጦርነቱን ስንጀምር በጣም ብዙ ሰዎች በአጠረ ጊዜም ብቻ ሳይሆን ማሸነፍም ይከብዳል የሚል ግምግማና ግምት ይናገሩ ነበር፤ ይሄ አልሆነም፤
👉 እኛን የሚዋጉን ሰዎች ዘመናዊ ጦርነት አያውቁም፤ የጦርነት ሳይንስ አያውቁም፤ የሚያውቁት የሽምቅ ውጊያ ነው፤ እሱ የሽፍቶች ውጊያ ነው፤ እሱ በሰው ሃይልና በተተኳሽ ቁጥር ማሸነፍ የምናረጋግጠብት ውጊያ ነው፤
👉 የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ስንት ሺህ ወጣት እንዳስከፈለን ስንት ጊዜ እንደወሰደ እናውቀዋልን፤ ይሄ የአሁኑ ኦፕሬሽን ደግሞ በምን ያህል ባነሰ የሰው ሃይልና መስዋዕትነት ለድል እንደበቃን ታውቃላችሁ፤
👉 ከሁመራ መቀሌ በእግር መጓዝ ማለት ብዙዎች አዲስ አባበ ሆነው ዝም ብሎ ጀግና እንደሚሉት አይደለም፤ በዚህ መልክዐ ምድር በዚህ ሙቀት ስንቅና ትጥቅ ተሸክሞ ይሄንን ያህል ጉዞ መጓዝ የማንም አገር ወታደር አይደግመውም፤
👉 ይሄንን ጀግንነት ወንጀለኞችን በመያዝ መድገም ያስፈልጋል፤ ወታደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መቶ በመቶ አሳክቷል፤ የሚቀረው ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ነው እሱንም በፍጥነት ማከናወን ያስፈልጋል፤
👉 ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የትግራይ ህዝብ ሃላፊነት አለበት፤ የተደበቁትን ሰዎች፣ ከመኪና ወርደው እግረኛ የሆኑትን ሰዎች በመያዝ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለትግራይ አስተዳደር ማስረከብ አለበት፤ ያ ካልሆነ ወታደሩ አገር የመጠገን ጊዜውን ወንጀለኛ በማደን ስለሚያሳልፍ የሚጎዳው ራሱ ህዝቡ ነው፤
👉 ከኢትዮጵያ መንግስት ልማት ድጋፍ መጠየቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ወንጀለኞችን አሳልፈው መስጠት ደግሞ ግዴታ ነው፤ ይህ ስምምነት ካለ ነው ስራችንን በአጭር ጊዜ በማከናወን ወደልማት የምንገባው፤
በርካታ ወንጀለኞችን እንደተያዙ፤ የተቀሩትም የት እንዳሉ መረጃው አለኝ፤
👉 የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝቦች ኩራት መሆኑን፤ በዚህ ቀጣና የሚነሳ ማንኛውንም አደጋ በሚፈለገው ልክ ለመመከት የሚያስችል ብቃት ያለው ጦር መሆኑን በድጋሜ አረጋግጧል፤
👉 የጁንታው ሃይል በቁጥር ከ80 ሺህ በላይ ይገመታል፤ አዳዲስ መሳሪያዎችን ታጥቋል፤ ከፍተኛ የተተኳሽ ዲፖዎች ነበሩት፤ ኮማንዶ ሜካናይዝድ ሮኬት መተኮስ የሚችሉም ሰዎችነበሩት፤ እኛ ግን መቀሌ እስከገባንበት ቀን ድረስ ሮኬት አልተኮስንም በእኛና በጁንታው መካከል ያለው ልዩነት ይሄ ነው፤ እኛ ያልተኮስነው ህዝባችን እዚህ እንዳለ ስለምናውቅ ነው፤
👉 እኛ ሮኬት የተጠቀምነው ጁንታው መቀሌን ለቆ በረሀ ለበረሃ ለማምለጥ ሲሞክር ነው፤ ይሄ የእውነት ይሄ የፍትሃዊነት ልዩነታችን አሸናፊ አድርጎናል፤
ኢፕድ እንደዘገበው ፤ ፎቶ ክሬዲት ኢፕድ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት
0Shares
0