በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት ከሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስተታወቀ።

“ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ስደተኛና የተፈናቀሉ ናቸው። በአጠቃላይ ህፃናቱን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሥራ ነው” በማለት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ኃላፊ አስታውቀዋል።

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማድረስ ስምምነት ላይ ቢደረስም ድርጅቶቹ በክልሉ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ አልተቻለም እያሉ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የገባበት ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ግጭት በሩካታ ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መሰደዳቸው ይነገራል።

Related stories   የኮቪድ ጽኑ ታማሚዎች ቁጥር መብዛቱ በዲላ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና አስከትሏል

“ለህፃናቱ የሚሰጠው እርዳታ አቅርቦት በዘገየ ቁጥር፣ ምግብ፣ በችጋር ለተጋለጡት ህፃናትን ለማደስ የሚያስፈልጉ አልሚ ምግቦች፣ ህክምና፣ ውሃ፣ ነዳጅና እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች እያጠሩ ወደ ከፋ ሁኔታ ያመራሉ” ብሏል ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ።

አክሎም “አፋጣኝ፣ ዘላቂ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማንንም ባላገለለ መልኩ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለየትኛውም ቤተሰብ በያሉበት እንዲመቻች እንጠይቃለን” ብሏል ድርጅቱ።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

ድርጀቱ አክሎም “ባለስልጣናቱ ለደኅንነታቸው ፈርተው የሚሸሹ ንፁህ ዜጎችን በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ እንዳለበትና ይሄም ዓለም አቀፍ ጥበቃ ፈልገው ድንበር የሚያቋርጡትንም ያካትታል” ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ህወሓት በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት የለም።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራል መንግሥቱና የህወሓት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ ደርሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል።

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገሪቱ መንግሥት ውስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተው ህወሓት ከሦስት ዓመት በፊት በተነሳው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ከማዕከላዊው መንግሥት መራቁ የሚታወስ ነው።

BBC BBC News አማርኛ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *