“Our true nationality is mankind.”H.G.

መቀሌ ወደ ተስፋዋ!! ሠራተኞች ወደሥራ ተመለሱ፤ በረራ ተጀመረ፤ የትግራይ ተወላጆች ዓይናቸውን ሲገልጹ ” አፍረናል” እያሉ ነው

በመቀሌ ቤተሰብ ያላት የጀርመን ነዋሪ ከወር በላይ ቆይታ ቤሰቦቿን በስልክ ማግነቷን ስትናገር ከንደበቷ የቀደመው ” አፍረናል፤ አፍሬያለሁ” የሚለው ቃል ነበር። በመቀሌ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ከቤተሰቦቿ መረዳቷን፣ የሚወራው እጅግ የተጋነነ እንደሆነ ያመለከትቸው የጀርመን ነዋሪ ደግማ ደጋግማ የምታነሳው ስለ ሃፍረት ነው።

ስሟ በግል ምክንያት እንዳይጠቀስ የጠየቀችው ይሕች የትግራይ ተወላጅ ” አንድ ወር እንኳን ሕዝብ የሚመገበው የለውም” ስትል የሃፍረቷን መነሻ ትጀመራለች። ” ይሁን የሚበላ ለአንድ ወር ይጥፋ፣ እንዴት ውሃ ይጠፋል” ስትል ትጠይቃለች። ” ሲንገረን የነበረው እኮ ራሳችንን የምንችል መንግስት እንደምንሆን ነበር” የምትለው የጀርመን ነዋሪ ” ያ ሁሉ የዲፋክቶ ቀረርቶ አንድ ብርጭቆ ውሃ ሳይኖር ነበር” ስትል ሃዘኗን ገልጻለች።

ከበርካታ አብረዋት ከሚኖሩና በርቀት ከምትገናኛቸው የአገሯ ልጆች ጋር መነጋገሪያቸው ” እነዚህ ሰዎች ምን ሲሰሩ ኖሮ፣ እንዴት ቢንቁን ነው እንዲህ ባዶ ቤት ታቅፈው፣ አንድ ወር ህዝብ የሚበላው ሳይኖረው፣ የጉድጓድ ውሃ እንኳን ሳይቆፍሩ 27 ዓመት የኖሩት” በሚል ጣይቄ የታጀበ እንደሆነ አመልክታለች።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

” አንዷ ጓደኛዬ ይህንን ሁሉ ጉድ ይዘው ነው እንዴ ሲጨፍሩ የነበሩት?” ብላ ክፉኛ መሳደቧን አመልክታ ሳታስበው አለቀሰች። ይህን ምስኪን ሕዝብ ሰርቶና ለፍቶ እንኳን እንዳይኖር ጠላት ዙሪያውን አበጁለት። አናከሱት። ዙሪያውን በቂምና በበደል ስሜት አስንሱበት” ስትል የትህነግን አንጋፋ መሪዎች ረገመች። አክላም ” ያልተማሩት ይታለሉ፣ የተማሩት ምን ሆነው ነው ይህ ሁሉ ጉድ አስቀድሞ ያልታያቸው” ስትል ጠየቀች። አሁን ሲጠየቁ ምን ምላሽ እንደሚሰጡ ስታስበው እንደሚያማት ገለጸች።

ብልጽግናን እስከወዲያኛው እንደምትጠላው ያስታወቅቸው ይህቺው የጀርመን ነዋሪ ፣ ምንም እንኳን ፓርቲውን ብትጠላውም የውሃ ጉድጓድ አፈረሰ፣ ድልድይ ሰበረ፣ መብራትብ አጋየ፣ ስልክ ቆረጠ ወይም ባንክ ዘረፈ ብላ እንደማትወቅስ ተናግራለች። በበቂ መረጃ የትግራይን ባንኮች ማን እንደዘረፈና መሰረተ ለማቶችን ማን እንዳፈራረሰ እንደምታውቅም አመልክታለች። ለተከሰተው ረሃብና ጥማት ተተያቂዎቹም ራሳቸው እንደሆኑ ጠቁማለች። በሌላ ዜና በትግራይ የገንዘብ ችግር መኖሩን፣ መድሃኒትና የሚጠጣ ውሃ እንዲሁም የምግብ አቅርቦት ሽግር እንዳለ ከፍራው የሚወጡ ዜናዎች ይጠቁማሉ። ሕጻናት ለጉዳት የተዳረጉበት ሁኔታ ስለመኖሩም እየትሰማ ነው።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የርዳታ እህል፣ መድሃኒት፣ የመጠጥ ውሃ በስፋት እየቀረበ ሲሆን ሰራዊቱ ከእለት ምግቡ እየቀነሰ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነና ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መንግስትና ይክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር እያስታወቀ ነው።

ሰራተኞች ወደ ስራ ተመለሱ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መቀሌ ከሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ተወያየ። ሠራተኞቹ ከትናንት ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል። በውይይቱ የተሳተፉት ሠራተኞች በሕግ ማስከበር ሂደቱ ከአንድ ወር በላይ በቤታቸው መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ሠራተኛ የሕዝብ አገልጋይ እንጂ የፖለቲካ ዓላማ አራማጅ እንዳልሆነ የተናገሩት ሠራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በመቀሌ የሰፈነው ሠላም ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን እንደሚያስችላቸውም ተናግረዋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞችን ወደ ስራ ለመመለስ ጥሪ ማቅረቡን አስታውሰዋል፡፡

በጥሪው መሰረት ሠራተኞቹ ከትናንትና ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸው የተመለሱ ሲሆን በተለመደው አግባብ ሕዝቡን ለማገልገል ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል፡፡

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ በይፋ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ በትግራይ ክልል በህወሃት ጁንታ ላይ ይወሰድ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በረራውን አቋርጦ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ የህግ ማስከበሩ ከተጠናቀቀ በኋላ በዛሬው እለት ምሽት ከአዲስ አበባ መንገደኞችን ጭኖ የመጀመሪያ በረራውን በማድረግ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤር ፖርት ደርሷል።

በኤርፖርት ለደረሱት መንገደኞችም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባል ጀነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀልና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አስተባባሪ አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚአብሔር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መቀሌ የደረሰው አውሮፕላን ሌሎች መንገደኞችን አሳፍሮ ምሽቱን ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ታውቋል።

የኤርፖርቱ ሰራተኞችም በሙሉ በስራ ገበታቸው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ በቀጣይ አየር መንገዱ በቀን ሁለት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ይቀጥላል ተብሏል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0