(ኢዜአ) በባዕከር፣ በሁመራና በቃፍታ አካባቢዎች የሚሊሻ ዋና አስተባባሪ በነበረበት ወቅት በንጹሃን ላይ ግፍ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ በሽሬ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የብረት ለበስ አዛዥ ሻምበል አማኑኤል በለጠ ለኢዜአ እንደተናገሩት እንኳአየነው መሰለ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው ተፈናቃይ በመምሰል በሽሬ ከተማ ሲንቀሳቀስ ነው።

ግለሰቡ በባዕከር፣ ሁመራና ቃፍቲያ አካባቢ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የፀጥታ ዘርፍ አስተባባሪ በመሆን የጁንታው የጥፋት ተልዕኮ ሲያስፈጽም መቆየቱንም ነው የገለጹት።

የህወሃት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አራት ቀናት ቀደም ብሎ  “ሰራዊቱ በወለጋና በትግራይ ክልል ጭፍጨፋ እያካሄደ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ  በማሰራጨት የጥፋት ቅስቀሳ ሲያካሂድ እንደነበርም ተናግረዋል።

የጁንታውን ሚሊሻዎች በማስተባበር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ ረገድም ጉልህ ሚና እንደነበረውም ጠቁመዋል።

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

በክፍለጦሩ የሁለተኛ ብርጌድ አባል ሃምሳ አለቃ ምህረት ደምሌ በበኩላቸው ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም ስልጣኑን በመጠቀም በተለይ አማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭቆና ሲፈፅም መቆየቱን ተናግረዋል።

“የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ መለያን ለብሳችኋል እንዲሁም ‘የእገሌን’ ሙዚቃ አዳምጣችኋል” በሚል ምክንያት በንጹሃን ላይ የሰባዊ መብት ጥሰት በመፈጸም የሚፈለግ ተጠርጣሪ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በአካባቢው የተለያዩ የፍተሻ ጣቢያዎችን በማቋቋም የሀገር መከላከያ ሰራዊት መደበኛ እንቅስቃሴን  ሲያስተጓጉል መቆየቱንም ጠቅሰዋል።

ሻምበል አማኑኤል እና ሃምሳ አለቃ ምህረት  ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በቀጣይ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ  በሚደረገው ጥረት ላይ የተለመደ ትብበሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

መንግስት በጽንፈኛው የህወሃት ጁንታ ሲያከናውን የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ አጠናቆ ወንጀለኞችን የማደንና ማህበረሰቡን መልሶ የማቋቋም ምዕራፍን እየተገበረ እንደሚገኝ ይታወቃል።

Related stories   " አሜሪካ ስለ ዴሞክራሲ፣ ጸጥታና ደህንነት የማውራት ሞራል የላትም፤ የአገራችን ሚዲያዎች ያሳዝናል"

(ኢዜአ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *