“Our true nationality is mankind.”H.G.

እግርኳስ ፌዴሬሽን በጋዜጠኛ አርአያ ተስፋ ማርያም ላይ ዛተ፣ የጁንታ አባል እንዲያመልጥ ደብዳቤ ጽፎ ጩኸት!!

የዝግጅት ክፍላችን እንዳጣራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ኮ/ል አወል አብዱራሂም ከትግራይ እንዲወጡ ለዩኒሴፍ top urgent request በሚል ደብዳቤ ሲጻፍ ፐሬዚዳንቱ አቶ ኢሳያስ አያውቁም ነበር። ድርጊቱ የጸሃፊው ነው።
ይህ ብቻ አይደለም በድብዳቤው ላይ ኮሎኔል አወል ለስራ ወደ ትግራይ ማምራታቸውንም ይጠቅሳል። ትህነግ የጦርነት እቅዱን ይፋ ከማስጀመሩ በፊት በርካታ ባለሃብቶች ወደ መቀሌ መጠራታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ሳለ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሃፊ በግላቸው የወሰዱት እርምጃ ምን አልባትም ሊጣራ የሚገባው ይሆናል። ማንስ መስካሪ አደረጋቸው? ከልምድ እንደሚታወቀው ጸሐፊዎች የአለቃቸው አንጋቾች ናቸው። ይህ የፌደሬሽኖቻችን ጸሃፊዎች የማለቅለቅ ህይወት ለዓመታት የማይደን በሽታ ሆኖ ሲያስለቅሰ የቆየ እንደነበር ማንም አይክደም። ዛሬም ይህ ተጋባር ላለመኖሩ ማረጋገጫ የለም። ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። ጸሐፊዎች መገለገያ ቁስ ናቸው።
በዚሁ መነሻ አማላጅ ልከው ሲተጋገተጉ ከቆዩ በሁዋላ ጋዜጠኛውን “እከሳለሁ” በሚል የአሽሙር ድሪቶ ለማሸማቀቅ መሞከር ስፖርትን እመራለሁ ከሚል አካል አይጠበቅም። ችግር ካለም እንዲስተካከል በመልክተኛ ሳይሆን በግልጽ መነጋገር እንጂ ወደ ማስፈራሪያ መግባት አግባብ አይሆንም። የፌደሬሽኑ ሊቀመንብር አስቸኳይ ማስተካከያም ሊወስዱ ይገባል።
ጋዜጠኛ አርአያ ህይወቱን ከፍሎ ትህነግን ሲዋጋ የኖረ፣ አሁንም እየተዋጋ ያለ፣ በቀጣይም ብዙ የሚጠበቅበት ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ መሆኑ እየታወቀ በዚህ ደረጃ “ ግለሰብ፣ ሰው፣ የተባለ…” በሚል ሽሙጥ ለመግለጽ መሞከር የስብዕና መላላት ማረጋገጫ እንጂ ሌላ አይሆንም። በግልጽ፣ የሚታወቅ፣ ሙሉ ስምና ሙያ ያለው፣ አድራሻውና ማንነቱ ገሃድ የሆነን አንድ ዜጋ በዚህ ደረጃ መግለጽ በራሱ የፌዴሬሽኑ ጸሃፊ በጋዜጠኛው ስራና ገድል ላይ ቂም እንደያዙ አመላካች ያስመስልባቸዋል።
ይህ ሲባል ስህተት አይሰራም ለማለት ሳይሆን ስህተት እንኳን ቢኖር ተግባብቶ ማስተካከል እንደሚቻል ለማሳየት ነው። አርአያ ደብዳቤውን የተቃወመበት መንገድና ዝንባሌ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ በዚሁ አግባብ የተበላሸ ጉዳይ ካለ ለማሻሻል መወያየት እንደሚቻል ስንጠቁም አርአያ አያጠፋም ወይም ከህግ በላይ ሊሆን ይገባል ለማለት አይደለም። ይሁን ብንልም እሱም እሺ የሚል አይመስለነም።
ይህን ከማድረግ ይልቅ ነገሮች ሲረጋጉ ጠብቆ በአገራዊ ተቋም ስም ማቅራራት ፍጹም ተቀባይነት የለውም። መስታዋት ቤት ያለ ድንጋይ እንደማይወረውር የጸሃፊውም አካሄድ እንዲያ ነውና ባስቸኳይ በህዝብ ተቋም ስም የማይገባ ተጋር ይቁም።
በወቅቱ አርአያ በፌስ ቡክ ገጹ ኡህንን ነበር ያለው።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

“ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተፈላጊውንና በአገራችን ጦርነት አውጆ ትግራይ ለተደበቀው ተፈላጊ ወንጀለኛ ኮ/ል አወል አብዱራሂም ሽፋን ለመስጠት የፃፈው ደብዳቤ አግኝተናል። ለዩኒሲየፍ በተፃፈው ደብዳቤ ኮ/ል አወል ለስራ ወደ ትግራይ እንደሄደ፣ ከነገ ወዲያ ጠቅላላ ጉባኤ ስለሚደረግ የፌዴሬሽኑ ም/ፕ/ት የሆነው ኮ/ል አወል እንዲገኝ ዩኒሲየፍ እንዲያመጣው ማለትም ከለላ ሰጥቶ አዲስ አበባ እንዲያደርሰው ነው ደብዳቤው የሚያትተው። በመጀመሪያ ዩኒሲየፍ ምን አግብቶት ነው ይህን የሚሰራው!? ኮ/ል አወል ንጹህ ቢሆን ለምን እጁን ለመከላከያ ሰራዊት አይሰጥም!? መንግስት በወንጀል ከሚፈልጋቸውና የመያዣ ዝርዝር ካወጣባቸው አንዱ ኮ/ል አወል ነው። ይህ የፌዴሬሽኑ ደባ ትልቅ የአገር ክህደት ወንጀል ነው! መንግስት የፌዴሬሽኑን ሰዎች በአስቸኴይ በቁጥጥር ስር እንዲያውል! ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በግፍ ለምን ከአሰልጣኝነት እንደተባረረ እነግራችኃለሁ። ኮ/ል አወል በቦሌ ለማስወጣት ሴራ የሚጠነስስው ደብዳቤ ይህ ነው”

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል
ታህሳስ 19/2013ዓ.ም አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህዳር 27/2013ዓ.ም 12ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄዱ ይታወሳል፤ ጠቅላላ ጉባዔው ከመካሄዱ በፊት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል። ከነዚህም መካከል ለጉባዔው አባላት ጥሪ እንዲሁም የጉባዔው ሰነዶች በመተዳደሪያ ደንባችን መሰረት ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ተልከዋል።
በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ የስራ አመራር ኮሚቴ ተሟልተው መገኘት ስላለባቸው ለሁሉም አባላት ጥሪ ተላልፏል። በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ኮ/ል አወል አብዱራሂም ጥሪ ከተደረገላቸው አባላት አንዱ ናቸው። መንግስታችን በጁንታው ኃይሎች በትግራይ ክልል እየወሰደ በነበረው የህግ የበላይነትን የማስፈን ዘመቻ ወቅት የትግራይ ክልል ተወካይ የሆኑት የስራ አመራር ኮሚቴ አባል በትግራይ ክልል ይገኙ ነበር። በወቅቱ ትግራይ የነበሩ የተወሰኑ እግር ኳስ ተጫዋቾች በዩኒሴፍ በኩል ወደ አዲስ አበባ መተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ምክትል ፕሬዝዳንቱም በጉባኤ ላይ ተገኝተው የስራ ድርሻ ውን በተመለከተ በጉባዔው ለሚነሱ አስተያየቶች ምላሽ መስጠት ስላለባቸው እንደ ተጫዋቾች ሁሉ ህዳር 14/2013ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ነገር ግን አርአያ ተስፋ ማሪያም የተባለ ግለሰብ በተለያዩ ሚዲያዎች በመቅረብ የፌዴሬሽናችንን በጎ ገጽታ ግንዛቤ አልባ በሆነ አስተያየታቸው በተደጋጋሚ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማድረግ ላይ ናቸው። እንዲሁም የባለስልጣን ልጆች ከብሔራዊ ቡድን ጋር ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል ያሉት አሉባልታ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ እና በማስረጃ ያልተደገፈ ወሬ መሆኑን ለህዝባችን እያሳወቅን፤ ይህ ሂደት እግር ኳሱን እና ፖለቲካውን ካለመረዳት የመጣ ጭፍን ተቋሙን የማጠልሸት እና የእኔ ብቻ አውቃልሃለው የአንድ ወገን አስተያየት ከጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ውጪ ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን ለህዝባችን እየገለጽን፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለማስፈን እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚያደርገውን እርምጃ ሁሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በግንባር ቀደምነት የሚደግፍ መሆኑን እየገለጽን በተቋማችን ላይ የተከፈተብንን የስም ማጥፋት ዘመቻ በህግ አግባብ የምንጠይቅ ይሆናል።
“ክብር ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለመከላከያ ሰራዊታችን!!”

0Shares
0