“Our true nationality is mankind.”H.G.

ለትህነግ የ”እንወሃድ” ጥያቄ የጃዋር መሐመድ ቅድመ ሁኔታ

ጃዋር መሐመድ ስሌት ላይ ጥገኛ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። በርቀት የሚያውቁት ይህንን ቢሉም ቅርብ የሆኑት ግን ስሌቱ መርህ ላይ የተመሰረት ሳይሆን ያሰበበት ለመድረስ የሚሰላ ተለዋዋጭ ሂሳብ እንደሆነ ነው የሚናገሩት።
ደጀኔ ጉተማ እንደሚያቆላምጠው “ ተንታኝ፣ ተመራማሪና አክቲቪስት …” ሳይሆን ጃዋር ጥሩ የሚዲያ ባለሙያ እንደሆነ የሚጠሉት ሳይቀር የሚቀበሉ ሃቅ ነው። ራሱ ጃዋርም ቢሆን ይህንኑ እውነታ እንደሚቀበለው ጥርጥር የለውም። አክቲቪስት ሆኖ ሲሰራም ቢሳካለትም እንደ ሚዲያ ባለሟልነቱ ግን አይሆንም።
ቀደም ባሉት ዓመታት ከአቶ መለስ ጋር ግንኙነት እንደነብረው፣ ከኦህዴድም ጋር አብሮ ሲሰራ ቆይቶ በግጥምጥሞሽ የገነነው ጃዋር፣ ከለውጡ በሁዋላ ጠቅልሎ አዲስ አበባ ከገባ በሁዋላ “ሁለት መንግስት አለ” እስኪል ራሱን መንግስት አድርጎ ለንፅፅር ሲያቀርብ “ስቷል” ወይም “ እየሳተ ነው” የሚል ምክርና ትችት ሲሰነዘር መስሚያ አልነበረውም። እንግዲህ ከዚህ በሁዋላ ነበር “ ጃዋር እንደ ትህነግ ምላስ እንጂ ጆሮ የለውም” በሚል መወቀጥ የጀመረው። እንደዚህ ከሚሉት መካከል ከኦህዴድ ጋር ግንኙነቱን እንዳያበላሽ፣ አቶ ለማንም ጎትቶ በማውጣት እንደማይጠቀም መክረውት እንደነበር ተረድተናል።
ሁለት እብዶች
የሰከኑ ፖለቲከኞች በጎንዮሽ ሲያወሩ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሁለት ታላላቅ እብዶች እንዳሉ ይናገራሉ። እነዚህ እብዶች የተባሉት ደግሞ ጃዋር መሀመድና ዛሬ ጉድጓድ ለጉድጓድ የሚሹለከለኩት የትህነግ አመራሮች ናቸው።
ጃዋር ከአቅሙ በላይ ራሱን ሰቅሎ ፓርላማውን አረቢያን መጂሊስ ላይ፣ መገናኛውን ቤቱ፣ ሚዲያውን ደጁ ተክሎ ራሱን እንደ ንጉስ ሰየመ። በዛው ስሜት ንግስናውን ህጋዊ ለማድረግ ጊዜ አነሰውና የትግሉን ዙር እጅግ አክርሮ ሁሉንም አፈራረሰው። ይህን አካሄዱን ነው “ እብደት” ሲሉ ባጭሩ የሚጠቅሱት።
የትህነግ አመራሮች ደግሞ ከላይ ሻዕቢያን የሚያክል ጠላት፣ ከጎን ጠላት አድርገው ፈርጀው የሚያደሙት አማራ፣ ከመካከል የፌደራል መንግስትን የሚያክል ጠላት ፈጥረው ጦርነት ውስጥ መግባታቸው ትልቁ የዘመኑ እብደታቸው እንደሆነ እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ። የጃዋርና የትህነግ ሰዎች እብደት የሚለያየው ጃዋር በመጣደፍ የፈጸመው እብደት ሲሆን የትህነግ እብደት ግን የተፈጥሮን ለውጥ ያለመቀበል፣ እርጅናን ያለማመን፣ ከዛም በላይ በሃሰት የፈጠሩትን የማታለያ ትርክት የማመንና እውነት አድርጎ የመቀበል ቂልነት ወይም የአንጎል ጨዋነት ነው።
የእብዶቹ የውህደት ሃሳብና የጃዋር ቅድመ ሁኔታ
ጃዋር ከጅምሩ ዶክተር አብይን ጠልቶ ስለነበር ከትህነግ “ እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” ሃሳብ ጋር ስምምነት ለመድረስ መነጋገር አይጠበቅባቸውም ነበር። ትህነግ በዲጂታል ወያኔ አማካይነትና በማህበራዊ ሚዲያና በግል የቴሌቪዥን ስርጭቱ፣ ጃዋር ባደራጃቸው ሚዲያዎችና ኔትዎርኮች አብይ አህመድን ሲደበድቡ እንደው ዝም ብሎ ግጥምጥም አልነበረም።
የትህነግና የጃዋር ግንኙነት ትህነግ መቀሌ ከገባ በሁዋላ በስትራቴጂ ተደግፎ ይመራ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ነግረውናል። ግንኙነታቸው አብጦና ጥንክሮ በፓርቲ ደረጃ የመዋሃድ ደረጃ ደርሶ ነበር።
ከአዲስ አበባ ትግራይ በቀለምና ጥናት ሰበብ ሲጎነጎን ለነብረው ግንኙነት ቀዳሚው የመጫዋቻ መድረክ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሲሆን፣ ዩኒቨርስቲውን ታኮ በርካታ የፖለቲካ ድር ሲደራ ነበር። በበርካታ ጉዳዮች ላይ መግባባት ቢፈጠርም ጃዋር አንድ ትልቅ ጉዳይ አነሳ።
ትህነግ ላነሳው የውህደት ጥያቄ ጃዋር ቅድሚያ ያነሳው ቅድመ ሁኔታ “ ጌታቸው አሰፋን አንሱ፣ ደብረጽዮንን አውርዱ፣ ጌታቸው ረዳንና ወ/ት ኪሪያን ወደ ሃላፊነት ከፍ አድርጉ” የሚል ነበር።ይህ ለትህነግ የቀደመውን ዘመን ያስታወሰ ሆነ።
ድሮ የዛሬን አያድርገውና ትህነግ አባዱላን አንሳ፣ አለማየሁን አቶምሳን ተካ፣ ጁነዲንን አውርድ… እያለ ያዝ እንደነበር ጃዋርም ዛሬ በቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው ጉዳይ ትህነግ ቤት ቁጭት ፈጠረ። እነ ጌታቸው አሰፋ ተንተከተኩ። እንደ ደብረጽዮን አመማቸው። ጃዋርን ዛቱበት። ግን ጊዜው ስላልሆነ በህቡዕ ለመስራት ወስነው እነ ሕዝቄልና በቀለ ላይ ታች እያሉ “መንግስት የለም” ብለው እስካወጁበት ቀን ድረስ ተጓዙ።
የምሁራን ንዴትና የጃዋር ቅድመ ሁኔታ ማረጋገጫዎች
ትህነግ ለጃዋር ጥያቄ በኦፊሳል ምላሽ ባይሰጥም፣ በኦፊሳል “አገር አውቆ፣ ጸሃይ ሞቆ በፓርቲ ደረጃ እንወሃድ” የሚለው ጥያቄ ወደ ጎን ተብሎ የህቡዕ የሚመስል ነገር ግን ገሃድ የሚታይ የትግል መስተጋብር ፈጥረው የአብይ አሕመድን መንግስት አወራጩት።
የዶክተር መረራ ኦፌኮ ለትህነግ አዲሱ ኦህዴድ እንዲሆን ታስቦ ትህነግን እንዲዋሃድ ውስጥ ውስጡን በካሳና በአበል ስም ብዙ የፈሰሰበት ድርድር ውሃ ሲበላው ቅድሚያ ያኮረፉት መንግዱን ሲያመቻቹ የነበሩት የዩኒቨርስቲው ሰዎች ነበሩ።
ለዚህም ይመስላል ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል መቀሌ ተገኝተው ከምሁራን ጋር ሲወያዩ “ እንኳ ደህና መጡ፤ ሌሎችም ሊመጡ ይገባል፤ ግን አንዳንዶች እገሌ ይሾም፣ እገሌ ይውረድ እያሉ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸው ነውር ነው …” እያሉ ብስጭታቸውን ሲናገሩ ተሰምቶ ነበር። በወቅቱ ጉዳዩ ለበርካቶች ተራ ጥያቄ ቢመስልም ብዙ የተከሰከሰበት ውህደት መክሸፉ የፈጠረው ስሜት መሆኑንን ይህን መረጃ ያካፈሉን አጫውተውናል።
ራሱ ጃዋር መሐመድም ቢሆን የአቶ ጌታቸውን ዳግም በትህነግ የስራ አስፈጻሚ ውስጥ መመረጥ ሲሰማ በኦኤምኤን በኩል እሳት ጎርሶ ትችቱን ሰንዝሯል። ጃዋር ትህነግ የማይሻሻል፣ ያረጀና ራሱን በወጉ ማየት የማይችል ፓርቲ መሆኑንን አጠንክሮ በመግለጽ ነበር የወቀሳቸው። በዛም አላበቃም። የሚቴኩ ጀነራል ተላልፎ እንደተሰጠ ሁሉ ጌታቸው አሰፋን አሳልፎ መስጠት የግባቸዋል ሲል በህግ አግባብ ሁሉ ሞግቷቸዋል። ጃዋር ይህን ቢልም ግንኙነቱ ሳይቋረጥ በመናበበ የዶክተር አብይን አስተዳደረ በፕሮፓጋንዳ አዝሎ፣ በመስከረም ለመዘረር የተነደፈውን ውጥን ግን ወደ ጎን አልገፋውም።
እናም “ጃዋር ብልጥ ፖለቲከኛ አይደለም” የሚሉት ወገኖች እንደሚሉት “ ጃዋርም ሆነ ኦፌኮ የፖለቲካ ሞት የሞቱት ከትህነግ ጋር ዳግም ግኝኙነት የጀመሩ ዕለት ነው” ባይ ናቸው።እነ ሃጫሉ፣ ፈይሳና በርካታ ታላላቅ ሰዎች እነ ጃዋርን “ ደህና ሰንብቱ” ያሉዋቸው በዚሁ ሳቢያ ነበር። አምቦ የእነ ደራራ ከፈኒ ሃዘን የጠበሳቸው ይህንን ጉዞ ሲሰሙ መረራንም “ የራስህ ጉዳይ” ብለዋቸዋል። ክሽፈቱ የመጣው በብልጽግና ሰዎች ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በእነ ጃዋር ቀሽም ፖለቲካ ነው። ቄሮ ንብረትነቱና አፈጣጠሩንም በውል ያለመረዳት ይመስላል። ይህ ሁሉ ተዳምሮ ዛሬ ጭጭ ሆኗል።
ትህነግ ከመስከረም 25 በሁዋላ መንግስት እንደሌለ ኤጀንቶቹን እነ … አስተባብራ ዘመቻዋን ስታቀጣጥል በዋናነት ሁለት ነገር ገምግማ ነበር። አንደኛው “ የዶክተር አብይ ስም በሚገባ ደረጃ ተበላሽቷል፣ ከሕዝብ ተነጥሏል፤ አሁን ደጋፊ የለውም፤ እዚህ ላይ ስኬታማ ስራ ተሰርቷል” የሚል ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ “ አብይ ጃዋርን ቢነካ ድፍን ኦሮሚያ በዓመጽ ስለሚቀጣጠል አብይ ዋጋ የለውም” የሚል ነው። በእነዚህ ሁለት ግምገማዎች መነሻ ከምስከረም 25 በሁዋላ መንግስት እንደማይኖር አውጆ ብልጽግናን በረዶ ማድረግ ይቻላል ብለው ሲነሱ፣ ብዜቱ በዜሮ የሆነው ቀደም ሲል ትህነግ ስለተጠጋቸው “ የፖለቲካ ሞት” ያሳወጀባቸው አጋሮቹ ወቅታዊ አቋም ለመመርመር የሚያስችል ጤና ስላልነብረው ነበር። በሌላ ቋንቋ “ አብደው” ነበር!!

0Shares
0