ዛጎል ዜና – በኦሮሚያ ክልል ዘመናዊ የኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት በተዘጋጀ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ። ዘመናዊ ከተማው “ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን ፕሮጀክቱን ዕውን ለማድረግ በተዘጋጀው ጥናት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የፕሮጀክቱ አላማ ሁሉን አቀፍ ዘመናዊ ከተማ መገንባት ነው ተብሏል። ሀሳቡ ባለፈው አመት ለክልሉ የካቢኔ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ነበር። ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግም ዕቅድ እና ጥናቱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበታል።

Related stories   የባይደን አስተዳደር ፖሊሲ አምስተኛው ምሰሶ የኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን ቡድን መወሰንና የ 2021 ምርጫን ማዋደቅ (1ኛ ክፍል 2)

ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በውስጡ ሁሉን የልማት ፍላጎቶች ያካተተ እና ዘመናዊ ከተማ የሚፈጥር ነው መሆኑም ነው የተገለጸው። የባህል ማዕከል እና የቱሪዝም ምርት በዘመናዊ ከተማው ከሚካተቱት መሀል ጥቂቶቹ መሆናቸውን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ገልጿል።

በፕሮጀክቱ የመኖሪያ መንደሮች፥ መዝናኛ ስፍራዎች፥ ኢንዱስትሪ ዞን፥ ሎጅስቲክስ፥ ደረቅ ወደብ፥ መጋዘኖች እና የተለያዩ አገልግሎቶች የተካተቱ ሲሆን በሂደት በ40 አመታት የሚፈጸም መሆኑም ነው የተገለጸው።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

ክልሉ “በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን ማረጋገጥ” የሚያስችሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ እያስገባ ይገኛልም ብሏል ፓርቲው። ፕሮጀክቱ በ23 ሺህ 556 ሄክታር ላይ የሚገነባ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊነት የስራ ዕድል ይፈጥራል።

fana

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *