“Our true nationality is mankind.”H.G.

የትህነግ የውጭ ክንፍ ትግራይ ሙሉ በሙሉ በመንግስት እጅ መውደቋን አመነ፤ የገንዘብ ማዕቀብ ጥሪ አቀረበ

ትህነግ በውጭ አገር ባሉት ሁለት ከፍተኛ አካሎቹ/ ሃላፊነታቸው ስለማይታወቅ ነው/ አማካይነት ባደረገው ስብሰባ ብልጽግና የሚመራው መንግስት ትግራይን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አምኖ አዲስ ስትራቴጂ መንደፉ ተሰማ። የገንዘብ መዋጮ ሱዳን ለሚገኙ ተፈናቃዮችና ለድምጸ ዋያኔ ዓለም አቀፍ ብቻ እንዲደረግና የክልሉ አስተዳደር ላይ ማዕቀብ እንዲደረግ ተብሏል። ድርጅቱ በግለሰቦች ስም ስላለው ሃብትና የንግድ ተቋማት የተባለ ነገር የለም። የትህነግ ሃብት በድርጅቱ የልዩነትና የመጠራጠር ምንጭ ነው።

“ላለፋት 3 ኣመታት የጥፋት ሃይሉ እንዲወገድ ከፍተኛ ትግል ሳደርግ ቆይቻለሁ፤ አሁን ለልማት እታገላለሁ” በሚል የአካሄድ ለውጥ ማድረጉን ያስታወቀው ዞባ ተምቤን ፔጅ እንዳለው ስብሰባው የተካሄደው ዛሬ ጃንዋሪ 2. ቀን 2021 ነው።

ዞባ “ልዩ ተጠቃሚ” ሲል የጠራቸው የቀድሞ ሹመኞችና የትህነግ ባለ አደራዎች እንዲሁም ካድሬዎች ባሉበት ተገኝተው ንግግር ካሰሙት መካከል በርሃነ ገብረክርስቶስና ፍስሃ ኣስገዶም ይገኙበታል። በንግግራቸውም ትግራይ ሙሉ በሙሉ በብልጽግና መንግስት ቁጥጥር ስር መውደቋን አምነዋል። ሌላ ያሉትን አማራጭ አቅርበዋል።

ከቀናት በፌት አቶ ፍስሃ አስገዶም በትግራይ ጦርነት እየተካሄደ አነደሆነ፣ በቅርቡ ትህነግ ድል እንደሚያስመዘግብ ለቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃዬ ተናግረው ነበር። ሳምንት ሳይሆን፣ የአገር መከለከያ የማረካቸውን፣ እጅ የሰጡትንና የተደመሰሱትን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች፣ እንዲሁም የትግራይ ካቢኔ አባላትን በቁጥጥር ስር ማድረጉን ተከትሎ ነው ሁለቱ ከፍተኛ የትህነግ አካላት በትግራይ መሬት የሚደረገው ትግል እንዳበቃለት ያመኑት።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ይህንኑ ተከትሎ የትሀነግ የፋይናንስ ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶች፣ የትግራይ ልማትና መላው የትእምት ጥላ ስር ያሉ ድርጅቶች ሃብት አሁን ላለው የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት እንዳይውል ጥሪ አቅርበዋል።

ከሁለት ስምንት በፊት መንግስት አግዶ የያዘው የድርጅቶቹ ሃብት የትግራይ ሕዝብ እንደሆነ አስታውቆ ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ መፍቀዱን የትግራይ ብልጽግና ማስታወቁ አይዘነጋም። በዚሁ መነሻ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳይውል የተባለው ሃብት ከአገር ውጭ ያለውን ይሁን አገር ቤት ያለውን በውል መለየት አልተቻለም።

የትህነግ ንብረት በግለሰቦች ስም የሚቀመጥ መሆኑና ለሕዝብም ሆነ ለድርጅቱ አባላት ሚስጢር መሆኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያስነሳ የቆየ ጉዳይ ነው። በአንድ ወቅት ዛሬ ንግግር ያደረጉት ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከትዳር ጓዳቸው ጋር ሲለያዩ ሚስት ከፍተኛ ሃብት በፍርድ ቤት እንድተወሰነላት ሚዲያዎች ይፋ አድርገው ነበር። በወቅቱ ሟቹ መለስ ዜናዊ ገንዘቡ የድርጅት መሆኑንን ጠቅሰው ሊያግባቡ ቢሞክሩም ሚስት አሻፈረኝ ብላ ድርሻዋን መውሰዷ የሚታወስ ነው።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

አቶ ስባሃት ነጋ በአገር ውስጥ ሚዲያ ተጠይቀው “ ኤፈርት ሃብቱ ከአፍሪካ አንደኛ ነው” በማለት የተናገሩለት ኤፈርት በምዕራብ አፍሪካ በማዕድን ኢንቨስትመንት፣ በዱባይ በሪል እስቴትና በገንዘብ ተቋማት፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ሰፋፊ ሃብቶች በውስን ባለስላጣኖች ስምና እነሱ በፈጸሙት ውል የሽርክና ስራ የሚሰራ ተቋም እንደሆነ ቢነገርም የትግራይ ህዝብ አያውቀውም።

በስብሰባው እንደተገለጸው ካሁን በሁዋላ በሱዳን ላሉ ተፈናቃዮችና ለድምጸ ወያኔ ኢንተርናሽናል ብቻ ድጋፍ የደረጋል መባሉን አስመልክቶ አስተያት የጠየቅናቸው አንድ የሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የክልሉ ተወላጅ “ ይህ ማለት ካሁን በሁዋላ ትግራይ ውስጥ የሚደረገው ትግል መሞቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከሱዳን ጋር በተፈናቃይ ስም ሃይል ለማደራጀትና ትግሉን በሚዲያ ለማስጮህ መታቀዱን የሚያመላክት ነው። የማውቃቸው ይህንኑ ሲሉ ሰማቻለሁ። እንደ ትግራይ ተወላጅነቴ አንዳንድ ቅሬታዎች ቢኖሩኝም ካሁን በሁዋላ ጦርነት የሚያዋጣ ነው ብዬ አላምንም” ብለዋል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

“በሌላም በኩል መቆጣጠር ከቻሉ ከትግራይ ሕዝብ ተደብቆ የኖረውን ሃብት እንጂ አገር ቤት ያለውን ሊሆን አይችልም ” ያለው አስተያየት ሰጪ፣ ካሁን በሁዋላ የትጋይን ሕዝብ ማታለል የሚቻል እንደማይመስላቸውና አዲሱ አስተዳደር በርካታ ሚስጢሮችን ይፋ ሲያደርግ ህዝብ እንደሚነሳባቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ሰሞኑንን አንድ የዋሻ እስር ቤት መገኘቱና በርካታ እስረኞችም በዛው እንደነበሩ ተሰምቷል። እንዲህ ያሉ የግፍ ተጋባራትና ይሪኮኖሚ ዝርፊያው በመረጃ ተደግፎ ይፋ ሲሆን ሕዝብ የራሱን ግምት ይወስዳል የሚል እምነት ያለው በበርካቶች ዘንዳ ነው።

ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኳላቸው መንግስት ከሱዳን ጋር ያለውን ጉዳይ ነገ ዛሬ ሳይል መላ ሊለው እንደሚገባ አሳስበዋል።
የስብሰባውን ዝርዝር ዞባ ተንቢን ፒጅ ዓለም ዓቀፍ ቅንጅት ለአወንታዊ ትግራይ OTNAA በቀጣይ ቀናት ውስጥ በሰፊው ለሕዝብ እንደሚያቀርብ ጠቁሟል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0