– ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹ የቀረጹትን ሰነድ በበጎ እንደምትመለከተው ገልጻለች፤

– የሱዳን ወገን ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጎ እንደሚመለከተው ገልጿል፤

– የግብጽ ወገን ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው አስታውቋል

ስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ተካሂዷል። ሚኒስትሮቹ የሕዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ያደረጉ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ በማተኮር ምክክር ተደርጓል፡፡

በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹ የቀረጹትን ሰነድ በበጎ እንደምትመለከተው እና በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብዓት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን ገልጣለች፡፡ የሱዳን ወገን በበኩሉ ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጎ እንደሚመለከተው እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ላይ ቢጋር በማጽደቅ ድርድሩን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡

የግብጽ ወገን ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው ገልጧል፡፡ የሕዳሴው ግድብ ሙሌት እና ዓመታዊ አስተዳደርን የሚመለከተው ሰነድ ላይ የሚደረገው ድርድር በአመዛኙ መግባባት የተደረሰበት ቢሆንም፣ ወደፊት በዓባይ ተፋሰስ ላይ በሚገነቡ የውሃ ልማት ሥራዎች ጋር የሚኖረው ቁርኝት ዋነኛ የልዩነት ሃሳብ ነው፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍጆታ የሌለው የኃይል ማመንጫ ግድብ እንደመሆኑ በግድቡ ላይ የሚደረሰው ስምምነት ይህንኑ ከግምት ያስገባ እና የተሟላ የውሃ ስምምነት በሌለበት እና ኢፍትሃዊ አጠቃቀም በሰፈነበት ተፋሰስ የኢትዮጵያን የመጠቀም መብት የሚያቅብ እንዲሆን ኢትዮጵያ አትፈቅድም፡፡

Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ

ይህን መሰረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ አሞላል እና ዓመታዊ አስተደዳር የሚመለከተውን ደንብ በጋራ ስምምነት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ናት፡፡ በዚህም መሰረት የስምምነት አማራጮችን ለግብጽ እና ሱዳን ወገን ያቀረበች ሲሆን የሃገራቱ ምላሽ ቀና እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋል፡፡ በቀጣይ የሃገራቱ ባለሙያዎች በውሃ ሚኒስትሮች አመራር ስር ስብሰባቸውን በመቀጠል ስምምነት የተደረሰባቸውን እና የልዩነት ሃሳቦችን በመለየት በቀጣይ ዕሁድ ጥር 01 ቀን 2013 ለሚካሄደው የስድስት ሚኒስትሮች ስብሰባ ውጤቱን ያቀርባሉ፡፡

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ የተካሄደውን የሶስትዮሽ ውይይት አስመልክቶየውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ የተካሄደውን የሶስትዮሽ ውይይት አስመልክቶ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል።

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነመረብ ስብሰባ አካሂደዋል።

ስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምከር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ተካሂዷል።

ሚኒስትሮቹ የሕዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ያደረጉ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ በማተኮር ምክክርተደርጓል፡፡

በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹ የቀረጹትን ሰነድ በበጎ እንደምትመለከተው እና በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብዓት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች፡፡

የሱዳንወገን በበኩሉ ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጎ እንደሚመለከተው እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ላይ ቢጋር በማጽደቅ ድርድሩን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡

የግብጽ ወገን ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው ገልጿል፡፡

የሕዳሴው ግድብ ሙሌት እና ዓመታዊ አስተዳደርን የሚመለከተው ሰነድ ላይ የሚደረገው ድርድር በአመዛኙ መግባባት የተደረሰበት ቢሆንም፣ ወደፊት በዓባይ ተፋሰስ ላይ በሚገነቡ የውኃ ልማት ሥራዎች ጋር የሚኖረው ቁርኝት ዋነኛ የልዩነት ሃሳብ ነው፡፡

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ፍጆታ የሌለው የኀይል ማመንጫ ግድብ እንደመሆኑ በግድቡ ላይ የሚደረሰው ስምምነት ይህንኑ ከግምት ያስገባ እና የተሟላ የውኃ ስምምነት በሌለበት እና ኢፍትሐዊ አጠቃቀም በሰፈነበት ተፋሰስ የኢትዮጵያን የመጠቀም መብት የሚያቅብ እንዲሆን ኢትዮጵያ አትፈቅድም::

READ ALSO “የኢትዮጵያ አንድ ሀገር ሆኖ መቀጠል ለአሜሪካ ጉዳት እንጂ ጥቅም ስለሌለው ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት” ኪሲንጀር ለሲአይኤ ያቀረበው ሪፖርት
ይህን መሰረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ አሞላል እና ዓመታዊ አስተደዳር የሚመለከተውን ደንብ በጋራ ስምምነት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ናት፡፡

በዚህም መሰረት የስምምነት አማራጮችን ለግብጽ እና ሱዳን ወገን ያቀረበች ሲሆን የሀገራቱ ምላሽ ቀና እንደሚሆን ተስፋ
ይደረጋል፡፡

በቀጣይ የሀገራቱ ባለሙያዎች በውኃ ሚኒስትሮች አመራር ስር ስብሰባቸውን በመቀጠል ስምምነት የተደረሰባቸውን እና የልዩነት ሃሳቦችን በመለየት በቀጣይ ዕሁድ ጥር 01/2013 ለሚካሄደው የስድስት ሚኒስትሮች ስብሰባ ውጤቱን ያቀርባሉ፡፡

(ኢ.ፕ.ድ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *