“Our true nationality is mankind.”H.G.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣሊያን ሃገር የተገደለችውን የወ/ት አጊቱ ጉደታ አስክሬን ወደ ሃገር ቤት እንዲመጣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣሊያን ሃገር በግፍ የተገደለችውን የወይዘሪት አጊቱ ጉደታ አስክሬን በትውልድ ቦታዋ በክብር ለማሳረፍ ወደ ሃገር ቤት እንዲመጣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የወይዘሪት አጊቱ ጉደታ አስክሬን ቤተሰቦቿ እና የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ ነን ባሉበት ጊዜ እንደሚመጣ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣሊያን ሃገር በግፍ የተገደለችውን የወይዘሪት አጊቱ ጉደታ አስክሬን በትውልድ ቦታዋ በክብር ለማሳረፍ ወደ ሃገር ቤት እንዲመጣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ጥያቄውንም ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤተሰቦቿ እና የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ ሲሆኑ እንደሚመጣ ነው የገለጸው፡፡
ወይዘሪት አጊቱ ጉደታ በስደት በነበረችበት ጣሊያን ሃገር በስራ ፈጠራ እና በታታሪ ሰራተኝነት እንዲሁም በሴቶች መብት ተሟጋችነት የምትታወቅ ጠንካራ ሴት መሆኗን የገለጹት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለኢትዮጵያ ሴቶች ምሳሌ ነበረች ብለዋል፡፡
በእኩይ ግለሰቦች ሴራ በግፍ የተገደለችው አጊታ የአዲስ አበባ ከተማ ተወላጅ በመሆኗ አስክሬኗ በትውልድ ስፍራዋ ማረፍ አለበት ብለዋል፡፡
በጣሊያን አገር በግፍ የተገደለችውን አጊቱ ጉደታ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ ለቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባስተላለፉት መልዕክት “ምንም እንኳን የእህታችን ህልፈተ ህይወት የሚያሳዝን እና የሚያንገበግብ ቢሆንም በተለያዩ ወጪ ሃገራት በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መደናገጥ ሳይፈጥርባቸው አንድነታቸውን እና ህብረታቸውን ጠብቀው ለአጊቱ ፍትህ ማግኘት መታገል አለባቸው” ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
(ኢ.ፕ.ድ)

0Shares
0