ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ልደቱ ብርቱካን ሚደቅሳን “ ቅንጅት ውስጥ ሆነን ለምናውቃት” ሲሉ በተላላኪነት ፈረጁ፤ “ግንቦት ሰባትም ያዛቸዋል” አሉ

ዛጎል ዜና – አቶ ለደቱ አያሌው የቀድሞ የቅንጅት ከፍተኛ አመራርና የአንድነት ሊቀመንበር የነበሩት ብርቱካን ሚደቅሳን ስም ጥቀሰው አበሻቀጡ። ወደ ሃላፊነት ሲመጡ ጀምሮ ሲጠብቁት እንደነበረው ስራቸውን በ “ተላላኪነት” የሚያከናውኑ እንደሆነ አድርገው ለርዕዮት ሚዲያ ተናገሩ።
ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ብዙም አስተያየት የመስጠት ፍላጎት እንዳልነበራቸው በንግግራቸው መካከል የጠቀሱት አቶ ልደቱ፣ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ያመለጣቸውን የኢትዮጵያን ሁኔታ ለመረዳት “ ቴዲ ምን አለ” በሚል የተያቂያቸውን ሚዲያ ለግንዛቤ ግብአትነት እንደተጠቀሙበት አመልክተዋል።

“ የተካሄደው ጦርነት በእያንዳዳችን አዕምሮ ውስጥ ነው” ሲል የህግ ማስከበር የተባለውን ጦርነት የገለጸው የሚዲያው ባለቤና ጠያቂ አቶ ልደቱ ስለምርጫ ቦርድ ሃላፊ ብርቱካን ሚደቅሳ ሲጠይቅ የተጠቀመው ቃል “ በግለሰብ ማንነት ላይ የሚያብረቀርቅ” ሲል ነበር።
ከቀድሞ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ፕሮፌሰር በቃና ጋር እያወዳደረ በርቱካን ሚደቅሳን የዘለፉት አቶ ልደቱ “ በተለይ ብርቱካንን በቅንጅት ውስጥ አብረን ስንሰራ ለምናውቃት” ሲሉ ነበር ያለ ከልካይ አልባ ዘለፋቸውን የጀመሩት። ወ/ት ብርቱካን በቅንጅት አመራርነታቸው ምን እንደሰሩና ለዛሬው ትችት ማስደገፊያ የሚሆን ማስረጃ ግን አላቀረቡም። ጠያቂውም አልጠየቃቸውም።
ደጋግመው “ ቅንጅት እያለች ለማንውቃት” በማለት ው/ት ብርቱካን በምርጫ ቦርድ ሃላፊነታቸው ምን ሊወስኑ እንደሚችሉ አስቀድመው ያውቁ እንደነበር አቶ ልደቱ አያሌው ሲደሰኩሩ አሁንም “ እንደው ለመሆኑ በቅንጅት ጊዜ ምን ክህደት ፈጸሙ፣ ወይም ምን በደል ህዝብና ድርጅታቸው ላይ አከናወኑ?” የሚል ማብራሪያ እንዲቀርብ አልተደረገም።
አቶ ልደቱ በቅንጅት ወቅት እሳቸው እንከን አልባ፣ ታማኝ፣ ለዓላማ ሟች ወዘተ ሆነው በእሳት መፈተናቸውን አገርና ዓለም በአደባባይ ያየውን የወ/ት ብርቱካንን ጀግንነት ሲያጠለሹ ተሰምተዋል።
ለማነጻጸር የቀድሞውን የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና አጣቅሰው፣ “ እሳቸውን የሚያዛቸው ህወሃት ብቻ ነው” አሉ። ወ/ር ብርቱካንን ግን አዜማና መንግስት እንደሚያዛቸው ሲገልጹ፣ አሁንም “ እንዴት? በምን መስፈርት? …” አልተባሉም።
ወ/ት ብርቱካን እንዲሾሙ ያደረገው የቀድሞው ግንቦት ሰባት፣ የአሁኑ ኢዜማ እንደሆነ ማስረጃ ሳያጣቅሱ ያቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው “ በቅንጅት ወቅት ብርቱካን ሚደቅሳን ለሚያውቁ” ብለው ጀምረው አዜማ ለምርጫ ቦርድ ሃላፊነት እንዳሾማቸው የጠቀሱት ፓርቲያቸው መሰረዙ “ታሪካዊ አመጣጥና ዳራ ” እንዳለው ለማሳየት ነው።

Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

“የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲወገዱና ከህዝብ እንዲነጠሉ በጥምረት ተናበው ከሚሰሩት መንደር ተሳታፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ልደቱ አያሌውና ይህንኑ አጀንዳ በግንባር ከሚያራምዱት ሚዲያዎች መካከል አንዱ የሆነው ርዕዮት ልዩነት የላቸውም” ሲል አስተያየቱን የሰጠው የአምቦ ነዋሪ ገመቹ አያና “ ብርቱካንን ትግስቱ በታዛዥነትና በባንዳነት የሚጠረጥርበት ዘመን ላይ ደረስን። ይህን ለመስማት መብቃታችን መላክም ነው” ሲል በተራው ተሳልቋል።
አቶ ልደቱ ህግ ተቀይሮም ቢሆን ምርጫ መደረግ እንደሌለበት ባደባባይ ሲከራከሩ ቆይተው በድንገት የሽግግር መንግስት ጠያቂ መሆናቸው፣ ለዚሁም የሚበጅ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀታቸው ከትህነግ እቅድና ውጥን ጋር እንደሚመሳሰል በርካታ አስተያየት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። በእስር ጊዜያቸው ትህነግ ከቅንጅት አባላት ለይቶ ለሳቸውን ብቻ ህይወታቸውን መጠበቂያ ሽጉጥ እንደሰጣቸው ለፍርድ ቤት መናገራቸው አይዘነጋም። አቶ ልደቱ በስተመጨረሻ ፓርላማ ሲገቡ፣ ብርቱካን ሚደቅሳ ግን ወህኒ ወርደዋል።
የትህነግ ከፍተኛ አመራሮች ወ/ት ብርቱካንን ግትር፣ የማይደለሉ፣ ጠንካራ ሲሉ የሚገልጿቸው ሲሆን በአደባባይ የፍርድ ውሳኔያቸው መለስ ዜናዊን አሳፍረው ስዬ አብረሃምን ነጻ ያወጡ “ የችሎት አንበሳ” በሚል የተሞካሹ ነበሩ። ለምርጫ ቦርድ ሶሾሙ “ ምርጫ ቦርድን መንግስት እንዳሻው ያሽከረክረዋል ማለት ብርቱካንን አለማወቅ ነው” በሚል ዶክተር ዳናቸው አደባባይ ምስክር የሰጡዋቸውና ሟቹ ቀንዲል ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “ ምትክ አልባ” ሲሉ የብርቱካን ሚደቅሳን የህሊና ጸዳል በአጭር ቃል መግለጻቸውም የሚዘነጋ አይደለም።
ጠያቂው “ ሳያላምጥ የሚውጥ” ሲል ብርቱካን ሚደቅሳን የሚወዷቸውን ሳይለይ ሕዝብን ለመግለጽ የሞከረ ሲሆን “ ይኼ ኦሮሚያ የሚባል አገር” ሲልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተወከሉበትን ክልል በማይገባው አጠራር ሲያስተዋውቅ በቃለ ምልልሱ ተሰምቷል።

Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ

ሁሉም ከተባለ በሁዋላ ማሳረጊያ የሆነው “ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ካልተቋቋመ አገሪቷ ሶስት ቦታ ትከፈላለች” የሚለው የልደቱ አያሌው ትንታኔና ድምዳሜ ነው። አቶ ልደቱ አያሌው ክትህነግና ትህነግ ካሰባሰባቸው ጋር በመሆን የሽግግር መንግስት ሲጠይቁ መስማት የተለመደ ሆኗል።
ፓርቲያቸው ኢዴፓ ሆን ተብሎ እንዲፈርስ መደረጉን ያወሱት ልደቱ አያሌውና የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ይልቃል ጌትነት “ ፓርቲያቸው ፈቃድ ቢያገኝ ለብልጽግና ምን ያህል ስጋት እንደሚሆን ብታስረዱ” በሚል ባለመጠየቃቸው ስለፓርቲያቸው ግዝፈትና ጥልቀት ሲያብራሩ አልተሰሙም። ቢሮና ገንዘባቸው ከኢዜማ ጋር በተቀላቀለ ድርጅት ስም ለእነ ዶክተር ብርሃኑ መሰጠጡን ሲናገሩም እሳቸው “ሃብታችን፣ ገንዘባችብ ተዘርፎ ” ላሉት አሁንም መጠኑ ለግንዛቤ በሚል ስንት እንደሆነ አልተጠየቀም።

Related stories   ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ