ቀደም ሲል በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል፣አሁን ደግሞ በአገር ክህደት ወንጀል የሚፈለገው የቀድሞ የአገር ደህንነት ዋና ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ ወንድም እርምጃ እንደተወሰደበት ተሰማ። ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ ግን እጅ ሰጥተዋል።አቶ ዳኔል አሰፋ ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከመሰማቱ በስተቀር ተጨማሪ መረጃ ይፋ አልሆነም። በመንግስት አካላትም ዜናው አልተገለጸም።የትህነግ አክቲቪስቶችም ሆኑ ደጋፊዎች ዜናውን አላስተባበሉም።

ከተንቤን መረጃ የሰጡን እንዳሉት አቶ ዳኔል ከኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ ጋር አንድ ላይ፣ አንድ ቤት ውስጥ ራሳቸውን ሸሽገው ነበር። ጥቆማ የሰጡትም በቅርብ መረጃ የነበራቸው ወገኖች ሲሆኑ በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ተጠይቀው ነበር።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

በአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ የነበሩት ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በፍቃደኝነት እጅ በመስጠታቸው በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አብሯቸው የነበሩት የጌታቸው አስፋ ወንድም አቶ ዳንኤል አሰፋ እጅ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸው መረጃ የሰጡን አመልክተዋል።

ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በትራንስፖርት ዘርፍ የአዲስ አበባ ምክትል ከንትባ በመሆን ከተሾሙ ከአንድ አመት ተኩል በኃላ በህወሓት አባልነታቸው ስለቀጠሉ ከስልጣናቸው ተነስተው ነበር። ከዛም ወደ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ጋር በይፋ መስራት ጀምረዋል። ዜናው ይህ እስከታተመ ድረስ በመንግስት በኩል በይፋ አልተጠቆመም። ይሁን እንጂ ናትናኤል በመባል የሚታወቀው የፌስ ቡክ መረጃ አቀባይ ይህንኑ ዜና በሰበር ቀድሞ አረፋፋዱ ላይ አውጇል። ናትናኤል ከግንባር የሚወጡ ዜናዎችን አስቀድሞ በመዘገብና ፍንጭ በመስጠት የሚታወቅ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *