ዛጎል ዜና – ልደቱ አያሌው እስር ቤት ከገቡ በሁዋላ በፍተሻ ሽጉጦች ሲገኙባቸው ” የህወሃት የስለላ ቡድን ራሴን መጠበቂያ የሰጠኝ ነው” ሲሉ ራሳቸውን ለመከላከል የሰጡት መልስ ቀደም ሲል ሲከሰሱበት ለነበረው ” የሁለት ቢላ ጨዋታ” መስታዋት በመሆኑ በርካቶች እሳቸውን በትህነግ ኤጀንትነት መፈረጃቸው ትክክል እንደነበር ምስክር የሆነ ክስተት ሆኖ ነበር።

በ1998 ዓመተ ምህረት ማስፈራሪያዎች ይደርስባቸው ስለነበር በወቅቱ የነበረው መንግስት “ችግሩ ሲያልፍ ትመልሳለህ “ብሎ እንደሰጣቸው ማመናቸው መነጋገሪያ ሆኖ ሳያበቃ፣ በዚሁ ጉዳይ በቀጣይ አፍንጫቸውን ተይዘው ማብራሪያ እንዲሰጡ ይደረጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ አቶ ልደቱ ከእስር ሲፈቱ ልባቸውን ተሽሏቸው ቃለ ምልልስ የጀመሩት ወ/ት ብርቱካንን በማናናቅና ሆነ።ብርቱካንን ” ባንዳ” እንደነበሩ አስመስለው የቅንጅት ወቅት እውቂያቸውን ዋቢ አድርገው ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ ሲፈርጇቸው በድንገት አዳልጧቸው ሌላ ሰፈር ውስጥ ተገኙ።

የቅንጅት አመራሮች በሙሉ ወህኒ ሲወርዱ ፓርላማ አድማቂ ሆነው የነበሩት አቶ ልደቱ የትግል ባልደረቦቻቸው እስር ቤት ሲወርዱ እሳቸው ከደህንነት ራስ መጠበቂያ ሽጉጥ እንደተሰጣቸው ገልጸው ማንነታቸውን እችሎት አደባባይ በተናዘዙበት አንደበታቸው በርቱካንን በሚያንቋሽሹበት ፍጥነታቸው ሌላ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል።

” ወህኒ ቤት ሄጄ ነበር” አሉ ” ቴዲ” እያሉ ደጋግመው ለሚያቆላምጡት ጠያቂያቸው፣ አስከትለው እነ ጃዋር መሀመድን፣ በቀለ ገርባን፣ ስንታየሁንና እስክንድር ነጋን ለመጎብኘት ወህኒ ቤት መሄዳቸውን ገለጹ።ሊጠይቋቸው የሄዱትን ሰዎች ሲያገኙ በነጻነት ያለ ፍርሃት ማነጋገራቸውን፣ማንም በቅርብ ሆኖ የሚያዳምጥ ሰላይ ወይም ፖሊስ አጠገባቸው እንዳልነበር በበጎ አነሱ።

Related stories   “በአጣዬ እና አካባቢው በተፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ” ኮማንድ ፖስቱ

ልቡ የታወረው የትህነግ ቁልፍ ሰው የርዕዮቱ ጠያቂ ” የሚነገረውን ብቻ” ብሎ ስለ ወህኒ ጉብኝቱ መስመር አስምሮ ጠየቀ። ወይም አቅጣጫ አሳየ። አቶ ልደቱም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በምንም ዓይነት የፖለቲካ ሂሳብ ከጃዋር ጋር የጋራ ነጥብ እንደማይኖረው፣ ይልቁኑም ጸረ ኢትዮጵያ እንደሆነ ከሚገልጸው የጃዋር አስተሳሰብ ጋር ምን እንዳገናኛቸው ሳይጠየቅ ጃዋርን መጎብኘቱን አብራራ። ጠያቂው እንዳለው ሁሉንም መናገር እንደማያስፈልግ ጠቁሞ ወደ እስክንድር ጉዳይ አመራ።

1997 የቅንጅት ማዕበል ዘመን አንዱና ዋናው የፓርላማ አንገባም ዘመቻ መሪ እስክንድር መሆኑን መቼም የሚዘነጋ የለም። በወቅቱ እስኬው ” ፓርላማ ትገቡ እንደሁ ዋ!” በሚል ሚኒሊክ ጋዜጣ ግንባር ላይ በካርቱን የተደገፈ ዜና ለጥፎ የትህነግን አገዛዝ ሲፋለጥ፣ ልደቱ ሽጉጥ ይታተቅ እንደነበር በነገረን ማግስት እስክንድር ጋር ሄዶ ምን አወራ?

ጃዋርና እስክንድር ጋዜጣ እንደሚቀያየሩ፣ መጽሃፍ እንደሚዋዋሱ፣ አብረው ለመታሰር ጠይቀው መከልከላቸውን ጠቁመው፣ ከዚህ በላይ በዚህ መድረክ መናገሩ አስፈላጊ እንዳልሆነ ጠቁመው ወደ ዋናው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የማማትና የመቀጥቀጥ አውዳቸው አቀኑ። ድብደባው ቁጥር ሁለት፣ ሶስት፣ አራት … ይኑረው በይፋ ባይነገርም በተመጋጋቢነት ግን ሌሎች ተቀብለውት የሚያላምጡት እንደሚሆን እሙን ነው።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

ጎልጉል ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ እንዴትና ለምን ገጠሙ? በሚል ንዑስ ርዕስ ስር “ጃዋር እስር ቤት ሆኖ “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” ሲል እርግጥም ሰሚን ያስደነግጣል። ጃዋርና የአንድነት ኃይሎች ምን አገናኛቸው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ጃዋር ብልጽግና ፓርቲ መቋቋሙ እጅግ እንዳንገበገበው ሲናገር አንድነትን በመቃወም መሆኑን በራሱ አገላለጽ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች በተደጋጋሚ አረጋግጧል። የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ገብቶ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳልነበረው ባንደበቱ በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ጃዋር፣ በድንገት ኦፌኮን ሲቀላቀል ፍላጎቱን የሚያሳካበት ካርታና ስልት ማዘጋጀቱ አይገርምም። ፖለቲካ ውስጥ ሲገባ ዓላማው ሥልጣን ነውና “የአንድነት ኃይሎች” ከሚላቸው ጋር ድር አደራ” ሲል ልደቱ አያሌው እንዴት ኦኤም ኤን ቢሮ ግብቶ ከጃዋር ጋር እሳት እንደሞቀ መጠቆሙን ማስታወስ አግባብ ይሆንል።

ጎልጉል አክሎም በአንድ ወቅት “አስክንድር ነጋ ምን እንደሚፈልግ አውቃለሁ” ሲል እንዳጫወታቸው፣ ይሁን እንጂ ዝርዝር ጉዳዩን እንዳላብራራላቸው የሚናገሩት ሰው፣ ጃዋርን እስር ቤት ሊጠይቁት ሄደው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” ሲላቸው በርካታ ጉዳዮች ተሳስመውላቸዋል። ኢትዮጵያዊ እምነት ካላቸው የኦሮሞ ተወላጆች ድጋፍ የሌለው ጃዋር፣ እነዚህንና ቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀልብ ለመሳብ ሲል በገሃድ ወጥቶ “ኢትዮጵያ” ብሎ ቢሰብክ ጽንፍ የያዙትና ጽንፍ ያስረገጣቸው ይነሱበታል። በመሆኑም በገሃድ “ኦሮሞ ፈርስት” እያለ በጓሮ ከአንድነት ኃይሉ ጋር ገጠመ። ተናብበውም መሥራት ጀመሩ። ምርጫ ላይ እንዴት እንደሚያሸንፍ አብሯቸው ሰጥቶ በመቀበል መርህ ዶለተ። ይህ መስመር አሁን የሚወተረተሩትንና ቀደም ሲል የተገፉትን ፖለቲከኞች ያጡትን ምኞት አጋለ። እናም አንድ ሆነው ዕቅዳቸውን ለመተግበር መነሳታቸውን ያትታል። ያብራራል። ሙሉውን ሊንኩን እዚህ ላይ ተጭነው ይንብቡ ጃዋር የአንድነት ሃይሎች ከዱኝ ይላል

Related stories   በሳሊቫኪርና በሪክ ማቻር መካከል እያገረሸ ያለውን ቅራኔ እየተባባሰ በመምጣቱ በደቡብ ሱዳን አዲስ ግጭት እንዳያገረሽ ተሰግቷል

ጽሁፉ በጥቅሉ ” መንግስት የለም” በሚል ስሌት የተነደፈው ድራማ ውስጥ ልደቱ አያሌው ያላቸውን ሚና ይሳያል። እናም 360 ዲግሪ የሚዞረውን ጽንፍ በማስተዋል፣ በመመጋገብ ማብቂያቸውን ” ጊዚያዊ መንግስት” ያደረጉ ሃይሎች “ቢያዩዋቸው ቢያዩዋቸው ሁሉም አንድ ናቸው ” እንዲሉ የትህነግ ዓላማ አራማጆች ሆነው እናገኛቸዋለን። ርዕዮት ሚዲያም የስሌቱና የስትራቴጂው መጥመቂያ የህሊና መታወሪያ ቤት ነው። የምናደምጠውም ከመታወር አናመልጥም። የታወርነውም ኪሳችንን እያወለቅን ነው። እነ ልደቱ አያሌው ሱዳን 40 ኪሎ ሜትር ድንበር ወራ ዝም መባሉ አግባብ አይደለም በሚል ጥይት እንዲተኮስና ቀውስ ውስጥ ትህነግ አፈር ልሶ እንዲነሳ እየወተወተ እንደሆነ አንዘንጋ።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *