ዛጎለ ዜና – ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ” የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ሽማግሌ አመራሮችን ይዞ በቅርቡ ዜናው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደርሳል” ሲሉ የመከላከያ ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ ” ጁንታ” የሚላቸው የትግራይ ህዝብ ነጻ ግንባር ትህነግ አመራሮች ራሳቸውን ቀይረው የመሸጉበት በሕዝብ ጥቆማ መታወቁን ማስታወቁ አይዘነጋም።

ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መደምሰሳቸው፣ መማረካቸውና እጅ መስጠታቸው በተገለጸ የቀናት ልዩነት ውስጥ የትህነግ ተዋጊ ሃይል በቃርሚያ መደምሰሱ ተሰምቷል።ይህ በአንድ ግንባር ነገር ግን ተቆራርጦ የነበረው ሃይል መደምሰሱን ከአዲግራት ጀምሮ ያለው ቀጠና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሰላም መሆኑንን እማኞች ተናግረዋል።

ስለ ዘመቻው የተለያዩ ክፍሎች ግምት አዘል አስተያየት ቢሰጡም፣ ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም ከፍተኛ የጦር አዛዥ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንዳለው ከሆነ ይህ የተንጠባጠበ ሃይል በወታደራዊ ቁንቋ በመከላከያ ሰራዊት “ተጠራርጓል”፤ አካባቢውም ነጻ ሆኗል።

Related stories   አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቶክዮ ኦሎምፒክ ትሳተፉለች!!

እነ ስብሃት ያሉበት የ”ጁንታው አመራር” ከነበረበት ገዳም ነቅሎ የመጨረሻ መዳረሻ ባደረገው የተከዜ አካባቢ ምሽግ ገብቷል።አካባቢው በጠባብ ቀለበት ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት ተከቧል።

ቀደም ባሉት ቀናት የከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መደምሰሳቸውን መንግስት ይፋ እንደሚያደርግ አስቀድሞ ፍንጭ ሰጥቶ የነበረው አርአያ “በሚቀጥሉት ቀናት ወሳኝ የድል ብስራት ዜና እንደምትሰሙ ታማኝ የቅርብ ምንጮች ያደረሱኝን መረጃ በመንተራስ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ” ሲል መረጃውን በማህበራዊ አውዱ አስፍሯል።

በሌላ ዜና የትህነግ ደጋፊዎችና ትህነግን መሰረታቸው ያደረጉ ሚዲያዎች የመከለከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተለቃቅሞ የሚመታበትና የሚጠፋበት ቀን መቅረቡን አሁንም እየገለጹ ነው። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ መንግስት የተማረኩ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላትን የተሃድሶ ትምህርት እየሰጠ እንደሆነና በተሃድሶ የትግራይ ፖሊስን ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ እየተነገረ መስማታቸውን የሚገልጹም አሉ። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት የተማረኩ በብዛት ቢኖሩም ለመገናኛ ብዙሃን ያልታዩት የስነልቦና ትምህርት እየወሰዱና የተነገራቸው ሁሉ ስህተት መሆኑን እንዲረዱ የሚያስችል ስራ እየተሰራ በመሆኑ ነው። ይህ ከገለልተኛ ወገን ወይም ክክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርም ሆን ከፌደራል መንግስት በይፋ አልተነገረም።

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

ከወታደራዊ ዜናው ይልቅ ሰብአዊ ቀውሱ ያሳሰባቸው አብዛኞች እንደሚሉት ” ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ዓለም የትግራይ ተፈናቃዮች እርዳታ እንዲያገኙ የበኩላቸውን ሊያደርጉ ይገባል” እያሉ ነው። የባንክ አገልግሎት ቢጀመርም ገበያ ላይ እህል እጥረት በመኖሩ መሸመት አለመቻሉን የጠቆሙ ችግሩ እንዳይሰፋ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የነዳጅ አቅርቦት ችግር በቅርቡ እንደሚቀረፍ መንግስት ቢያስታውቅም፣ ችግሩ ያስከተለው ማህበራዊ ቀውስ በቀላሉ የሚታይ ባለመሆኑ አጎራባች ክልል በተለይም አማራ ክልል ለትግራይ ሕዝብ ያለውን አጋርነት በማሳየት አጋርነቱን ባስቸኳይ ሊያሳይ እንደሚገባ እየተተቆመ ነው። የጎጃምና አካባቢው እህል ነጋዲዎች ምርታቸውን ወደ ትግራይ እንዲያጋግዙና እንዲነግዱ አማራ ክልል ማበረታታትና በዚያውም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን የማደስ ስራ እንዲጀመሩ የመከሩም አሉ።

Related stories   ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ በዶላር ሳይሆን በብር የኪራይ ውል የምትጠቀምበት ስምምነት ጫፍ እየደረሰ ነው

በሁመራ አንዳንድ አካባቢዎች ስሜታዊ ሆነው በትግራይ ተወላጅና ነዋሪዎች ላይ ያልተገባ ድርጊት የሚፈጽሙ “ኤጀንቶች” ዓላማቸው ሌላ በመሆኑ አማራ ክልልና መንግስት በትብብር ሊያርቁት እንደሚገባ ከስፍራው ታዛቢ ነን ያሉ ለዝግጅት ክፍላችን ጥቆማ ሰጥተዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *