አስተያየት – ልጅ ግሩም ( ፒኤችዲ) ፊስ ቡክ የተወሰደ
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን በኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል በአሜሪካ ታዛቢነት የተካሄደውን እና ኢትዮጵያ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነትን የተቃወመችበትን ውይይት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸው የሚታወስ ነው።እኚህ ሰው ግብጽ ሲንጎዳጎዱ ቆይተው ወደ ሱዳን አምርተዋል።የግብጽ ቆይታቸውን አስመልክቶ ” የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ከህዳሴ ግድብ ጋር ተይይዞ ሀገራቱ ያሏቸውን ልዩነቶች በፍትሃዊነት እንዲፈቱ አሳስበዋል ” ሲል በካይሮ የአሜሪካ ኤምባሲ በመግለጫው አስታውሷል።

ከአለቃቸው ትራምፕ ጋር ሊሰናበቱ በቋፍ ያሉት የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ወደ ካይሮ፣ ብሎም ወደ ሱዳን የሚያመሩበት ጉዳይ በይፋ እንዲህ ነው ተብሎ ባይገለጽም፣የህዳሴው ግድብ ጉዳይና የቀጣናው ነገር ዋናው ጉዳይ እንደሆነ ታምኗል። ለሁሉም ግን ልጅ ግሩም በፌስ ቡክ ገጹ ” በመጨረሻ ኢትዮጵያ ብቻዋን ቀረች” ሲል የሚከተለውን አስፍሯል።

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር Steven Mnuchin ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከመብረራቸው በፊት ትናንት ካይሮ ጎራ ብለው ከግብጽ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያይተዋል።
የግብጽ ፕሬዚዳንት አል-ሲሲ ባለፈው ዓመት በሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ አሜሪካ ያደረገችውን ጥረትና ኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በማድነቅ አሜሪካን በሕዳሴ ግድብ ላይ ለመደራደሪያ ያቀረበችው ረቂቅ ስምምነት ለረጅም ዓመታት የዘለቀውን አለመግባባት ለመፍታት የሚያስችል ነው ብለዋል።

የግብጽ ፕሬዚዳንት ለአሜሪካኑ የገንዘብ ሚኒስቴር ሕዳሴ ግድብ በቀጠናው ላይ ስለሚያደርሰው ቀውሶችና ሌሎች የጋራ ጉዳዮችን አስረድተዋል። ከውይይቱ በኋላም የአሜሪካን የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ወደ ካርቱም ገብተዋል።

Related stories   ኢትዮጵያን የምታለቅሰው በ"መሪዎቿና በውድ ልጆቿ" ነውና !! ጆሮ ያለው ይስማ!!

የአሜሪካ መንግስት ሱዳን ሽብር ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ከሰረዘቻት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሱዳን መንግስት አመታዊ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወስናለች።

የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትሩ Mr. Mnuchin ግብጽንና ሱዳንን ከጎበኙ በኋላ ዛሬ ወደ ዋሽንግተን ይመለሳሉ። ባለፈው እሁድ በአፍሪካ ሕብረት በተመራው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ግብፅ ድርድሩ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር መሪነት ባለፈው አመት በየካቲት ወር ላይ በቀረበው ረቂቅ ስምምነት ካልሆነ አልደራደርም በማለት ከድርድሩ ወጥታለች።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ አሜሪካ ባቀረበችው ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት ላይ ሳትገኝ የቀረች ሲሆን ሱዳን በቦታው ላይ ተገኝታ በወቅቱ በአሜሪካ ሽብር ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር በመሆኗ ስምምነቱን ላይ አልፈረመችም ነበረ።

Related stories   ኢትዮጵያን የምታለቅሰው በ"መሪዎቿና በውድ ልጆቿ" ነውና !! ጆሮ ያለው ይስማ!!

አሁን ሱዳን ከሽብርተኝነት ውንጀላ ነፃ ስለሆነች አሜሪካ ባቀረበችው ስምምነት ላይ እንድትፈርም ግፊት እየተደረገባት ነው። ዋሽንግተን የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ ፕሮጄክት ላይ ጫና ለማድረግ ሱዳንና ግብጽን እየደገፈች አጋር ወዳጆች በማድረግ ላይ ነች። ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር ላይ እየፈጸመች ያለው ጥቃት በካይሮ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን የዋሽንግተን ረጅም እጅ እንዳለበት አያጠራጥርም። በዚህ ሁሉ ጫና እና መገለል ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መጨረስ ከቻለች ከአድዋ የማይተናነስ ታላቅ ታሪካዊ ድል ይሆናል።

የልጅ ግሩም የፊስቡካቸው ሊንክ https://www.facebook.com/A.Aethiopia

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *