የድምፀ ወያኔ የኦሮምኛ ቋንቋ አዘጋጅ የነበሩ ጋዜጠኞች ህዝብን ይቅርታ መጠየቃቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የጁንታው ቡድን ልሳን የነበረው ድምፀ ወያኔ በቴሌቪዥን ጣቢያው ከወራት በፊት በኦሮሚኛ ቋንቋ ስርጭት በመጀመር የውሸት ዘገባዎችንና በጋዜጠኞች መርሆ ፀያፍ የሆኑ በሀገር ህልውና ላይ ጫና የሚፈጥሩ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷል ።
በኦሮምኛ ቋንቋ ሲሰሩ ከነበሩ 4 ጋዜጠኞች ሶስቱ ግርማ ጉዲሳ፣ ካሊድ አብዱልፈታና ሙስጠፋ ቃሊዩ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በፍቃዳቸው በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሚዲያና ወንጀል ምርመራ ቢሮ የነበረውን ነገር ማስረዳታቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
ጋዜጠኞቹ እንዳስረዱትም የቅጥር ማስታወቂያው የወጣው በትግራይ ቲቪ በኦሮሚኛ ቋንቋ ስርጭት ስለሚጀምር በሚል ሲሆን በፈተናው ወቅትም የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ገፅታ የሚገነቡ ዝግጅቶች ላይ ያተኮረ ስራ እንደሚሰሩ እንደተነገራቸው ለኮሚሽኑ አብራርተዋል፡፡
“ወደ መቐለ ከተጓዝን በኋላ ግን ድምጸ ወያኔ ተመድበን ብሄር ብሄረሰብን በመንግስት ላይ ማሳመፅ እና የእርስ በእርስ ብጥብጥ መፍጠር ላይ ያተኮረ ፅሁፍ እየተሰጣቸው በግዴታ” ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል ።
በዘገባቸውም በኮቪድ ምክንያት የተራዘመውን ሀገራዊ ምርጫ መቃወም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰላም የኖቬል ሽልማት አግባብ አይደለም ብሎ ለማሰረዝ መጣር፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴና ተግባር ሁሉ በተቃራኒ መልኩ በመጥፎ ጎን ትንታኔ መስጠት ላይ በማተኮር በኦሮሚኛ ቋንቋ እንዲያቀርቡ ይገደዱ እንደነበር አስረድተዋል።
በክልሉ በነበረው ህግን የማስከበር ዘመቻ ጣቢያው ከመቐለ ከተማ ቁሳቁሱን ጭኖ ጋዜጠኖችንም በማስገደድ ወደማያውቁት ቦታ በመውሰድ በደረሱበት ሁሉ ስርጭት ለመጀመር እየተሞከረ ባለበት ወቅት ከመከላከያ ሰራዊት የሚደርስበት ጥቃት በማየሉ የጁንታው ቡድን ሲሸሽ ጋዜጠኞቹ ረጅም የእግር ጉዞ በማድረግ እና መቐለ በመግባት በፍቃዳቸው ይህንን መረጃ ሰጥተዋል ብሏል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ።
ጋዜጠኞቹም “በቡድኑ ጋር በመሆን ለሰራነው መጥፎ ስራ ህዝብ ይቅርታ ያድርግልን” ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡(ኢ ፕ ድ)

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *