ዛጎል ዜና – ስዩም ምስፍን ከመቀሌ ብዙም በማይርቅ ስፍራ መከበቡን መረጃዎች እያመለከቱ ሲሆን ይህ መረጃ ይፋ ከመሆኑ በፊት ስዩም መስፍን የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አራት ቀን በፊት አገር ለቆ እንደወጣ በሱዳን በኩል መውጣቱን የሚናገሩ አሉ፡፡
እጅግ የተቀራረበ ወይም ቀጥተኛ የሆነ መረጃ በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም እንዳለው ስዩም የተከበበው ከመቀሌ ድንበር 18 ኪ/ሜትር ርቀት ወይም ከመቀሌ እምብርት በግምት ከ 35 እስከ 40 ኪ/ሜትር በምትገኘው ገርአልታ ተብሎ በሚጠራውና ስፍራ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ህዝብ ክራባት ለብሶ ግብር በሚከፍልበት ቴሌቪዥን፣ ልጆቹን የገበረበትን የባድሜን ጦርነት “በፍርድ ቤት ተከራክረን አሸነፍን” በሚልነጭ ውሸት በማቅረብ ወንጀል የፈሸመው ስዩም እጅ በመስጠት ወይም በመደምሰስ መካከል እንደሚገኝ ነው የተጠቆመው፡፡
በህዝብ ጥቆማ ያሉበትን አካባቢ እንዳወቀ ከቀናት በፊት ይፋ ያደረገው የመከላከያ ሰራዊት አመራር ስዩም መስፍን ተደብቆ እንደሚገኝ ቦታ ከታወቀ በሁዋላ ስፍራውን በቅርብ ረቀት ከቦ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ከትግራይ የተገኘው ጥቆማ እንደሚያመከተው ስዩም ምንም ሳይሆን እጁን ለመያዝ ኦፕሬሽኑ ተጀምሯል፡፡ ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ጠዋት ድረስ ኦፐሬሽኑ እንደሚጠናቀቅ አርኣያ እማኞቹን ጠቅሶ ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተከዜ ከታየዘው ስብሃት ነጋና ሚስቱ ኮ/ል ፀአዱ እንዲሁም የጁንታው አባላት በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች በመከላከያ ኮማንድ ሃይል እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታውቋል፡፡
በተቃራኒው ሥዩም መስፍን አገር ለቆ የወጣው የመከላከያ ሰራዊት ላይ እርምጃ ከመወሰዱ አራት ቀን በፊት መሆኑንን፣ ይህም የሆነው በሱዳን በኩል እንደሆነ፣ እሱ ወደ ሱዳን ማምራቱ ሲታወቅ አቶ ገዱና ደመቀ ተከታትለው ካርቱም ሄደው እንደነበር የሚናገሩ ዜናውን አያምኑም፡፡ እነሡ እንደሚሉት ስዩም መቀለን የለቀቀው አስቀድሞ ነው፡፡
በሁለቱም ወገን ያለው ዜና በመንግስት በኩል ማረጋገጫ አልተሰጠበትም፡፡ ስዩም መስፍን መቀለ ሆኖ አስገራሚና ምን አልባትም በአዝናኝነታቸው ወደፊት የሚታወሱ ትንተናዎችን በድምጸ ወያኔ በኩል እየሰጡ ሰሚውን ትን ሲያሰኙ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *