ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጭካኔ ኩያሳ ሲሰራና ጥላቻ አናት ላይ ሲቀነዝር …

የተናቀው እረኛ፣ የተዘበተበት እረኛ፣ ዋራንቲ የተቆረጠበት እረኛ … ሁሉን ችሎ ድራጎኑንን አፈር ከደነበት። በሳምንታት ውስጥ የድራጎኑንን ገላ አነተበው። “ ዋ ትረግጣትና” በተባለው አገሩ ፎለለ፤ “ አትታበዩ” ሲል ድሉ ታላቅ ቢሆንም እንደማያስኮፍስ መከረ። ይህን የዘመን ክስተት ዛሬም የሚያጣጥሉ አሉ… ጥላቻ መርዝ ነው። ቅንቅን ነው። ቱሃን ነው። ከቱሃንም “የሚጋለብ” ትልቅ ቱሃን፣ የሚጋለብ ቱሃን … ያበደው ሳቀ። የሚጋለብ ቱሃን አይቶ አያውቅም። ጥላቻ ከልክ አልፎ ልብህ ላይ ቅንዝር ሲጫወት ቱሃን ፈረስ ይሆናል። ጥላቻ ልቡናን ሲወስብ ግን ሚስጢርህን በራስህ አንደበት እንደ ድሮ የቁጩ ሳትገረፍ ታፈርጣለህ። ዛሬ የሆነው ይህ ነው። ተመስገን … ድልን ለማጣጣል ራስን በጥላቻ ተሰርሮ ማጋለጥ

ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታውቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደ ውጭ ተመለሰ፡፡ ከሃኪሙ ቢሮ ወጣ !

ብዙ የተቆረጡ አንገቶች ኮሪደሩ መግቢያ ላይ ተደርድረዋል፡፡ አንገቶቹ በላስቲክ ተደርገው ተቋጥረዋል፡፡ እያንዳንዱ ቁራጭ ጭንቅላት ባለቤት አለው፡፡ ባለቤቱ ብቻ ነው ቁራጭ አንገቱን የሚያውቀው፡፡ ብዙ የተቆረጠ ጭንቅላት፡፡ አስናቀ እሱ ያመጣውን ጭንቅላት ቁራጭ ዘነጋው፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አስናቀ ዛሬ በሕይወት የለም፡፡ አስናቀ እጅግ ቆንጆ የቀይዳማ፣ ተሞላቆ ያደገ፣ ለቤቱ አንድ ወንድ፣ ሁሉም የቤተሰቡ አካላት አይን አይኑንን የሚያዩት፣ በኮሚክነቱ ፈቃድ የተጠው ልጅ፤ ምን ያደርጋል ነበር፡፡ አስናቀ ሳያድግ ራሱን ጠላ ቤት ቀርቅሮ እንደ ቦለተ ሞተ፡፡

ያበደው አስናቀን በደንብ ስለሚያውቀው እንባውን አቀረረ፡፡ አስኔ መኖር እየቻለ አምቡላ በላው፡፡ እንደምን ከረማቹህ፡፡ ዛሬ ወሬው ሁሉ ስለ ተቆረጠ አንገት ነው፡፡ “ታጋይ ለአጋሩ ሲል ቀድሞ ተሰዋ፤ ታጋይ ለትግሉ ሲል ዋጋ ከፈለ” የሚለው ትርክት “ ሲያልቅ ታጋይ የባልደረባ ታጋይን አንገቱን ቆረጦ ፈረጠጠ” ወደሚለው ተቀየረ፡፡ ስማ ጆሮ ያለህ፣ አንገት ያለህ ዞረህ እይ፤ አይናማ ተመልከት፣ ጭንቅላት ያላህ አስብ …. ተራረዱ፣ ተሞሻለቁ፣ ብለህ አትገልፍጥ፡፡ ያገርህ ፖለቲካ መተራረድ እንጂ ሌላ አያውቅም!!

አስናቀ ከሃኪሙ ቢሮ ወጣ ያለው የተቆረጠ አንገት ሊያመጣ ነበር፡፡ ብዙ አነገቶች ተደርድረዋል፡፡ አስናቀ የሱን መለየት አልቻለም፡፡ ያበደው የዛሬ መረጃ ባይኖረውም አስናቀን ውሻ በነከሰው ጊዜ፣ ውሻው ባለቤት ከሌለው አስገድሎ አንገቱን ባማስቆረጥ ፓስተር መሄድ ግድ ነው፡፡ምክንያቱም የማታውቀውን ውሻ አስረህ አትነዳም።

አስናቀን የነከሰው ጅላጅል ውሻ የሰፈሩ ጸሐይ ሟቂዎች ተከፍሏቸው አንቀው ገደሉትና አንገቱን ቆርጠው ለአስናቀ አስረከቡት፡፡ አስኔ አንገቱን ይዞ ፓስተር ሄደ፡፡ ፓስተር ሄዶ እንደሱ አንገት ቆርጠው ከመጡ ሰዎች ተርታ እሱን የነከሰውን ውሻ አንገት ኮለኮለ፡፡ አስናቀ ላስቲኩ ላይ ምልክት አላደረገም ነበርና መለየት አቃተው፡፡ ሲቆይ ሃኪሙ ከቢሮው ወጣ ብሎ መቆየቱን ነገረው፡፡

አስኔ መለየት እንዳቃተው ገለጸ፡፡ አስከትሎም “ዶክቶር እንደ በግ ቀንድ የለው፣ ላት የለው በምን ልለየው” አለና ቆርጦ ያመጣውን አንገት መለየት እንደማይችል አረጋገጠ።… ጨዋታው ወዲህ ነው። አንገት ቆረጣ። ደብዛ ለማጥፋት!!

ስብሃት ነጋ ሳይቆረጡ ተያዙ። ሲያዙ የመከላከያ አባላት ፊት ሆነው ፈገግ እያሉ ሲያወሩ ጥምባሆውን ለመለኮስ እንኳን ጊዜ አላገኙም። እናም ደስ ብሏቸዋል። ዛሬ ተላጭተው፣ ያማረ በልተው፣ የሚቀማመሰውን ቀምሰው በትዝታ ወደ ሁውላ …

ያበደው በትዝታ ወደ ሁዋላ ሲመለስ ለወትሮው ምራቁ ይደለድላል። ይቆጣል። በዛው አናቱ ይግልና ያናጨዋል። ዛሬ ግን አዲስ ስሜት። የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሚል ምስል ያለበት ዘንዶ አርቷል። ባለ ሞገስ ዘንዶ። ያልፈረሰው የኢትዮጵያ ምልክት አየር ሃይል።

ደስታው ግን አፍታ አልቆየም ድንገት ተቆናጠረና “ ቆይ ለምን? ለምን? ለምን? እኮ ለምን? ” እያለ ዘለለ። እነ ስብሃት ለምን እንደዚህ መሆንን መረጡ? እንዴት ቢያስቡ እንዲህ ሆኑ? ስብሃትና እህታቸው በዚህ ዕድሜ ዋሻ ለምን መረጡ? ዋሻ ውስጥ ስንት ጊዜ ሊኖር? ያበደው መልስ አጣ …

አምባ ገነኖች እንዲህ ናቸው። ሳዳም እንዲያ ፎክሮ ምናምንቴ ስርቻ ውስጥ ተያዘ። ራሱን እንኳን ለማጥፋት አላሰበም። አምባገነኖች ማስገደል እንጂ መሞትን አይደፍሯትም። ሞሶሎኒ የሞተው ሚስቱን ይዞ ሲኮበልል ተይዞ በገዛ ነው። ሂትለርም ራሱን አላጠፋም።

ቦሰና ተቆጣች። አንዳንዶች ስብሃትን እያዩ ሲገለፍጡ አልተደሰትችም። ስብሃት በበቂ ችሎት እንዲዳኝ ትወዳለች። መያዙንም የአምካ ቁጣ ነዶበት እንደሆነ ታምናለች። “ ግን “ ትላለች “ ግን እድሜያቸው ደስታውን ጎዶሎ ያደርገዋል” ባይ ናት። ቦሰና መከላከያ ሲቸፈቸፍ አንብታ፣ ስብሃት ሲያዝ አዝና … ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። የሚረዷትን ፖለቲከኞች የተራበች አገር …

ድሉ የጎረበጣቸው አሉ። ድሉን ለማሳነስ የደከሙ ጥቂቶች ከላይም ከታችም የታመሙ፣ ወይም ታመናል ብለው ያምታቱ ድሉን ሊያሳንሱ መሞከራቸው ለቦሰናም ግልጽ ነበር። አይችልም፣ አይሆንለትም፣ ደካማ፣ ልፍስፍስ፣ አቅመ ቢስ የተባለው መሪ መራና ድል አቀጣጠለ። ዛሬም ደካማ እየተባለ ነው …

ቦሰና “ መጥኔ” አለች። ይቅርታ መጠየቅ ባይቻል ድሉን ማድነቅ ይከብዳል? የበርካቶች ጥያቄ ነው። ያበደው ጥያቄውን አጎላው። አዎ ጥላቻ መጥፎ ነው። ጥላቻ ሲጀመር መሪው ቃል “ እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” ነበር፤ እረኛው ሌላ እረኛ ነበረውና ጸና!!

የተናቀው እረኛ፣ የተዘበተበት እረኛ፣ ዋራንቲ የተቆረጠበት እረኛ … ሁሉን ችሎ ድራጎኑንን አፈር ከደነበት። በሳምንታት ውስጥ የድራጎኑንን ገላ አነተበው። “ ዋ ትረግጣትና” በተባለው አገሩ ፎለለ፤ “ አትታበዩ” ሲል ድሉ ታላቅ ቢሆንም እንደማያስኮፍስ መከረ። ይህን የዘመን ክስተት ዛሬም የሚያጣጥሉ አሉ።

ሲያጣጥሉ ግ፤እ ታሪካቸውን ነው የሚያወሩት፣ ጥላቻቸው ማስተዋላቸውን ስለጋረደው የባንዳነት ዘመናቸውን “ ከስብሃት ጋር ተቀምጬ” እያሉ ይተርካሉ። “ የእኛ ልጅ አለን” እያሉ ያፏጫሉ። የፓርቲ ስም እየለዩ ተደጓሚውን ከሚነቀፈው ሳያስቡት አንገዋለው ያሳያሉ… ጥላቻ ልቡና ሲዘጋ ማሳያው ይህ ነው!!

ጥላቻ መርዝ ነው። ቅንቅን ነው። ቱሃን ነው። ከቱሃንም “የሚጋለብ” ትልቅ ቱሃን፣ የሚጋለብ ቱሃን … ያበደው ሳቀ። የሚጋለብ ቱሃን አይቶ አያውቅም። ጥላቻ ከልክ አልፎ ልብህ ላይ ቅንዝር ሲጫወት ቱሃን ፈረስ ይሆናል። ጥላቻ ልቡናን ሲወስብ ግን ሚስጢርህን ታፈርጣለህ። ዛሬ የሆነው ይህ ነው።

ጥላቻህ ላይ አበል ሲደረብበት በጀነራል ብርሃኑ ጁላ ብቃት ትነዳለህ። የኢትዮጵያ ወታደር መሆኑንን ባንዲራ ለብሶ ሲናገር በግድ ” ኦሮሞ ነህ” ትለዋለህ። ዛሬ ጀነራሎቻችን፣ መኮንኖቻችን፣ ወታደሮቻችን ሚሊሻዎቻችን፣ ልዩ ሃይላት ተጋምደው ድራጎኑኑ ሲጥሉ የማይታይህ ጥላቻ የህሊናህን መሃል ስለሰረረው ነው። የተሰረረ ማንነት፤ ያበደው ተፋ። ሲናደድ የለድለደ ምራቅ ያገኘው ነገር ላይ ይለድፋል።

ኢትዮጵያ ምን ትሁንልህ? ምን ታድርግህ? ያበደው ጮክ ብሎ እየተየቀ ቁልቁል በሸራተን ጥግ ሮጠ። መድረሻውን አያውቀውም። ሸራተን … ሌላው ቶራ ቦራ !! ዋናው ቶራ ቦራ ተናደ። ቦሰና ” ይሄ ቤት” ትላለች። አዎ ስም የሌለው ክልል። ስም የሌለው መንግስት። ስም የሌለው ፕላኔት። ኢትዮጵያ የምትጋለብበት መርከብ !!

ያበደው እንደሮጠ ሃዲድ ገባ። ቦሰና የለችም። ደጎል ጋደም ብሏል። በክራት ስለምታ አደረሰ። ለሚገባቸው ተስፋ እየለመለመ ነው። ጥላቻው ከመሰረቱ ተንዷል። የፍልፈሎቹ ዘመቻ አስጊ አይደለም። ኢትዮጵያ አምላክ አላት። ኢትዮጵያ ትግራይም ጭምር ናት። ጀነራሉ ” ፈጣሪ ረድቶናል” አሉ!! በጥላቻ የምትቃጠሉ አቁሙ። ጨዋታውን ቀይሩ። ወይም ከልፍለፈ ወደ ሰርቶ መኖር ተቀየሩ!! ቸር ያሰማን!! ሰላም ይብዛላቹህ፤ አስኔ ጓዴ አፈር ይቅለልህ!! የጥላቻ ብላቴናዎች ስብሃት ይለቀቅ ይሉ ይሆናል!! ማን ያውቃል!! የበላን ያብላል!!