“Our true nationality is mankind.”H.G.

አዲስ አበባ ማዘግጃ ቤት ለበዓል የተከዘነ ርችት ፈነዳ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማዘጋጃ ቤት ለበዓላት ማክበሪያ ተብሎ በመጋዘን የተቀመጠ መጠነኛ ርችት በድንገት ፈንድቶ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስተዳደሩ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ከባፈለው ዓመት ጀምሮ አጠቃላይ የህንጻ እድሳት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ለተለያዩ በዓላት ማክበሪያ ተብሎ በመጋዘን የተቀመጠ መጠነኛ ርችት በድንገት ፈንድቶ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች ፣የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በቦታው ተገኝተው ሰራተኛው ወደ መደበኛ ስራው መመለስ እንደሚችል ያሳወቁ ሲሆን÷ የከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የህንጻው እድሳት ስራም እንደቀጠለ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ አስታውቋል።

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0