“Our true nationality is mankind.”H.G.

” አሜሪካ ስለ ዴሞክራሲ፣ ጸጥታና ደህንነት የማውራት ሞራል የላትም፤ የአገራችን ሚዲያዎች ያሳዝናል”

የአገር ቤት ሚዲያዎች በማህበራዊ ገጻቸው ያስተጋቡት ዜና እንደ ዜጋ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነው አቶ ይገረም ሃይሌ ለዛጎል አስታወቁ። “አሜሪካ ስለ ዴሞክራሲ፣ ጸጥታና ደህንነት የማውራት ሞራል የላትም” ሲሉ ሰሞንኛ ዜናዎችን አስመልክተው ተችተዋል።
ዛሬ ከአዲስ አበባ ይልቅ አሜሪካ ጭንቀት ውስጥ እንደሆነች ያስታወቁት አስተያየት ሰጪ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ይልቅ መግለጫውን ተቀብለው ሳያጣሩ አገራቸው ላይ ሟርት የሚበትኑ ሚዲያዎች አስገራሚ ናቸው።
ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዋሽንግቶን ማነጋገራቸውን ያወሱት አስተያየት ሰጪ አዲስ አበባ በተባለው ደረጃ አስጊ ነገር እንደሌለባት ማረጋገጣቸውን፣ ችግሩ አለበት እተባለው ቦታ ዘመዶቻቸው ሄደው እውነቱን እንዳረጋገጡ አመልክተዋል። ” እኔ በግል ይህንን ካደረኩ ሚዲያዎች የተደፋባቸውን ተንኮል ያዘለ ዜና ከሚያራግቡ ለምን ሃቁን አያጣሩም? ይህ ወንጀልም ነው። ከዛም በላይ አገሬ የሚሏትን ምድር ምስል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ጭቃ መቀባትና ኤምባሲው መግለጫውን ያወጣበትን ዓላማ ማሳካት ነው” ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ያወጣውን መግለጫ ማየታቸውን ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ፣ ዛሬ አሜሪካ ምድር አንድ ግቢ 20 ሺህ ወታደር ተመድቦ እየተጠበቀና፣ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር መላወሻ ባሳጠበት ወቅት አንድ ሰው ተዘረፈ ተብሎ መግለጫ ማውጣት ከሞራል አንጻር ሲታይ ለኤምባሲው ሃፍረት መሆኑንን ነው ያመከቱት።
የዓለም ታላቅ አገር በአንድ ነውጠኛ የምትናድና ቤተመንግስቷ ሳይቀር የዱርዬ አክራሪዎች መፈንጫ በመሆኑ ዓለም ሲሳለቅ አንድ ሰው ተሰረቀ ብሎ የጸጥታና የሰላም ችግር እንዳለ አድርጎ ማራገብ አሳፋሪ እንደሆነ የዲሲው ነዋሪ ይናጋራሉ። አያይዘውም ይህን ሁሉ የሚያዩ የአጋራችን ” ዜጎች” ሳያጣሩ ሞራል አልባዎች የሚያሰራጩትን መረጃ ማሰራጨታቸው ደግሞ እንደ አገር ማሰብ ማቆማችንን አመላካች ነው ብለዋል።
አሜሪካ ዜጎቿ ወደ እንጦጦ ፓርክ እና ጉለሌ የእጸዋት ማዕከል እንዳይሄዱ የሚያስጠነቅቅ መረጃ ስታሰራጭ ዜጎቿ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል ስጋት መሆኑንን ነው። የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በትዊተር ይህንን ሲያሰራጭ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋ እና ጥቃት ይፈጸማል በሚል ነበር። በመሆኑም አሜሪካውያን እና ሌሎች ዜጎች ወደ እንጦጦ ፓርክ፣ የካ ተራራ፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል እና ሌሎች የተራራ መውጣት እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ ነው በጥሪው ተላልፎ የነበረው።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ይህን በመቃወም ፖሊስ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሚከተለውን ብሏል።
ወንጀል በስፋት እየተፈፀመ ስለሆነ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ተጠቀሱት ስፍራዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና የከተማችን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

Related stories   አየር ሃይል " ትዕግስትም ልክ አለው" ሲል ለሱዳን ምክረ ሃሳብ ሰጠ

ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ስድስት ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ቢወሰዱባቸውም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ስፍራው በጣም ሰፊ እና ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ መሆኑን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስለ አካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ከኮሚሽኑ በቂ መረጃ ሳይጠይቁ በስማ በለው ያገኙትን መረጃ መነሻ በመድረግ የከተማችን ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ በተለይ ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ መንቀሳቀስ ስጋት እንደሆነ አድርገው መዘገባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብሏል፡፡
በቅርቡ የተከበረው የገና በዓል በሰላም መከበሩንና ከ12ሺ በላይ ሰዎች የታደሙበት ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁ የከተማዋን ሰላማዊነት ማሳያ ስለመሆኑ ኮሚሽኑ አስታውሶ በተጠቀሱት ስፍራዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ ሰዎች በጋራም ሆነ በግል ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

0Shares
0