በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አምቼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሰረቀው ገመድ ጠልፎ የጣለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ቡድን ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አሰፋ፣ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ/ም ምሽት ላይ ወደ ግንባታው ስፍራው ሰራተኛ መስሎ የገባው ተጠርጣሪው ለሊቱን የህንፃው የምድር ወለል ውስጥ ሆኖ ያሳልፍና ከንጋቱ 12 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ገደማ ለህንፃው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ከተቀመጠ ገመድ ላይ 40 ሜትር ያህል ቆርጦ በመውሰድ በወገቡ ጠምጥሞ በላዩ ላይ ጃኬት በመደረብ ከግቢው መውጣቱን ገልጸዋል፡፡
የግንባታ ስራው የሚከናወነው 24 ሰዓት ሙሉ በመሆኑ የጥበቃ ሰራተኞችም ሰራተኛ መስሎ የገባው ተጠርጣሪ ላይ ሲወጣም ትኩረት እንዳላደረጉ የገለፁት ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን ግለሰቡ ገመዱን ሰርቆ በመንገድ ላይ ሲጓዝ አረማመዱን ተመልክተው ጥርጣሬ ያደረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለማረጋገጥ ሲያስቆሙት ለማምለጥ ሲሮጥ፤ ሰርቆ በወገቡ ላይ የጠመጠመውየኤሌክትሪክ ገመድ ጠልፎ እንደጣለውና በህብረተሰቡ ትብብር ተይዞ ወደ ፖሊስ እንደቀረበ ተናግረዋል፡፡
የጥበቃ ሰራተኞች ተገቢውን የፍተሻ ተግባር ቢያከናውኑ መሰል ወንጀሎችን መከላከል እንደሚቻል ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አሰፋ ማሳሰባቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
(ኢ ፕ ድ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *