የሻሸመኔ ከተማ ሰላምና ጸጥታ እንዳስታወቀው በሞተር የታገዘ ከባድ ዝርፊያን ሲፈጽሙ የነበሩና ራሳቸወንን ሬንጀርስ ሲሉ የሚጠሩ የማፊያ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁንን ጠቅሶ ኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው  ይህ የማፊያ ቡድን ከከተማዋ ወጣ ብሎ ባሉ የጨረቃ ቤቶች ራሱን መሽጎ የነበረ ነው።
አሁን ደግሞ ራሳቸውን የበለጠ በማደራጀት በጦር መሳሪያ በመታገዝ ተመሳሳይ ቁልፎችን በማስቀረጽ የግለሰብ ቤቶችን ሲበርብሩ ፤ባለሶስት እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችን በመስረቅ በአጎራባች ክልሉች ጨምሮ እስከ ጠረፍ በመውሰድ ሲሽጡ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡
የከተማዋ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመምከርም ባደረገው እልህ አስጨራሽ ጥረት ከ35 የቡድኑ አባላት ውስጥም 33ቱ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
በከተማዋ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ከባድ የንጥቂያና የዝርፊያ ወንጀሎች መበራከታቸውን ተናግረው በስርቆት ያገኙትንም ባጃጆችና ሞተር ሳይክሎች ወደ አጎራባች ክልሎች እስከ ጠረፍ ድረስ በመውሰድ ሲሸጡ እንደነበር ሃላፊው ተናግረዋል።
ይህንን ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ከከተማዋ ወጣ ካሉ የገጠር ከተሞች የመጡ እንጂ የከተማዋ ወጣቶች እንዳልሆኑ የሚናገሩት አቶ ስንታየሁ አሁን ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ብለዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ በሰላም የመንቀሳቀስ ችግር እንዳለባቸው ሲናገሩ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ከፖሊስ መዋቅሩ ጋር በተደረገው የተቀናጀ ጥረት 33ቱን ይዘናል ብለዋል አቶ ስንታየሁ።
በያይኔአበባ ሻምበል

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *