የገንዘብ ዝውውርን”በውጭ አገር ያለን ሃብትም ሆነ የትህነግን ማንኛውንም ነገር ከስብሃት በላይ የሚያውቅ አንዳችም ምድራዊ ፍጡር የለም” ይህን ሰው መያዝ ትህነግ ከነሚስጥሯ እንዳትቀበር ያደርጋል። የትህነግን ሚስጢር ማወቅ ደግሞ ድሉን ሙሉ ያደርገዋል።

ለራሳቸው ሲሉ የሚመረምሩት የሚመከታቸው ተቋማት እንደሚሉት ከኢትዮጵያ በሕገወጥ ወደ ውጭ አገር የወጣው ገንዘብ ከ22 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይጠቁማሉ። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ  ከ2002 እስከ 2009 ባሉት ሰባት ዓመታት አስራ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገንዘብ ተዘርፎ በውጭ አገር ባንኮች መቅመጡን ከነገረን በሁዋላ ነው አሃዙ ያደገው። ከድንጋጤ ይልቅ እንደ ኩራትም የተነገረው። ከዚህ አንጻር የአቶ ስብሃት ነጋና አባዲ ዘሙ መያዝ ቁም ነገሩ እጅግ የገዘፈ እንደሆነ እየተሰማ ነው።

የትህነግ ሃብቱ ሚስጢር የመሆኑ ጉዳይ ለትግራይ ተወላጆችም ነው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ትህነግን ከሚመሩት ውስጥም እጅግ ጥቂቶቹ ካልሆኑ በስተቀር በይፋ አያውቁትም። ኤፈርትን ሲመሩ የነበሩ በፖለቲካ ልዩነትና በኩርፊያ ሲኮበልሉ ስለ ኤፈርት አይተነስፉም።

ስዬ አብረሃም እግር ተወርች ተብለው፣ ሌባ በሚል ተቀፍድደው ሲፈቱ ስለመሩት ድርጅት ያሉት ነገር የለም። እንደውም አስቀድመው ” ስለ ኤፈርት እንዳይጠየቁ ተነጋግረው ነው ቃለ ምልልስ የሚያደርጉት” ሲሉ የድርድር ቃለ ምልልስ ማድረጋቸውን በግርምት ሲናገሩ የነበሩ አሉ። የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልታን ሃላፊ የነበሩት አቶ በላይ አሜሪካ ጥገኝነት ሲጠይቁ ሲመሩት ስለነበረው ኤፈርት አልተነፈሱም።

ስብሃት ነጋ አንዴ የግላቸው እንደሆነ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአፍሪካ በሃብቱ አንደኛ ደረጃ የደረሰው ኤፈርት የተሰኘው የንግድ ተቋም፣ እዚህ ደረጃ ሲደርስ የሚታወቀው ለትርፍ ባልተቋቋመ ድርጅት ስም መሆኑ የድርጅቱን ደምና ነፍስ ምንነት ያስረዳል።

አዜብ መስፍን ባላቸውን ታኮ አድርገው የመሩት ኤፈርት፣ የሃብቱና ሃብቱ የት፣ በእነማን ስም፣ በየትኛው አገርና ባንክ፣ እንዳለ በግልጽ አለመታወቁ በተለይ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት መከራከሪያ ሆኖ ቆይቷል። ብበድርጅት ውስጥ ሳይቀር ጉምጉምታ የሚሰማበት ሃቅ ነው። ዛሬ ስለ ኤፈርት እውቅና ያላቸው ስብሃት ነጋና አባዲ ዘሙ መያዛቸው ትርጉም እንዳለው የሚጠቁሙ፣ የሁለቱን አንጋፋዎች መያዝ ለሚያቃልሉ ” አይቼሽ ነው ባይኔ” የሚለውን ዘፈን እየዘፈኑላቸው ነው።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

“ትህነግ / ኤፈርት የ40 ዓመት እቅዱን በ25 ዓመት ከእቅድ በላይ አሳክቶታል የሚል እምነት ስላለኝ አጠቃላይ ሀብቱ ከ600 ቢሊዮን እስከ አንድ ትሪሊዮን ብር ሊደርስ ይችላል ብዬ እገምታለሁ” ሲል ከወር በፊት አስተያየታቸውን በመንግስት ሚዲያ የሰጡ ይህ ሃብት በትክክል ለህዝብ እንዲውል መደረግ እንዳለበት፣ ነገር ግን ኤፈርት በምዕራብ አፍሪካ ሆቴልና ማዕድን፣ በዱባይና አውሮፓ አገራት በቋሚ ንብረቶች፣ እንዲሁም በአክሲዮን ሽርካ አሜሪካን አገር ያደረጀው ሃብት ለትግራይ ህዝብ ህልም ከመሆን ሊያልፍ እንደሚገባው ጠቁመው ነበር።

ይህ አስተያየት ሲሰጥ መቀለ ሆነው ” እንዴት እዚህ እንደመጣሁ አልገባኝም” የሚል አስተያየት ሲሰጡ የነበሩት ስብሃት ይሰሙ ነበር። የሚገርመው ግን የትግራይ ተወላጅ የሆን የሚዲያ ሰዎችም ሆኑ ምሁራን ” እንዴት ነው ነገሩ” ሲሉ አልተሰሙም።

ዛሬ በትግራይ ያለው ሁኔታ ባይሰክንም፣ ትግራይ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ግልጽነት የጎደለው ቢሆንም፣ ለጋሾች ትግራይ ለመግባት ያሰፈሰፉበት ምክንያት ራሱን የቻለ ከደግነት ያለፈ ቁማር እንዳለበት ቢታመንም፣ በርካታ ባስቸኳይ መጽዳት ያለባቸው ነገሮች ቢኖሩም፣ የኤፈርት ጉዳይ እየተጠናና የገንዘብ ዝውውሩ እየተመረመረ መሆኑንን ዛጎል ሰምታለች።

እንደ መረጃው ከሆነ ስብሃት ነጋ ሁሉንም ጉዳይ ግልጽ ለማድረግ ተስማምተዋል። ገና ከትግራይ ሳይነቀስቀሱ ብዙ ጉዳዮችን ይፋ አድርገዋል። ትህነግ የድርጅት ሃብት የምሚለውን ሁሉ በትሬውም ሆነ በዓይነት ወክሎ የሚያንቀሳቅሰው በግለሰቦች አማካይነት ነው። ውክልናው ደግሞ ህጋዊ መሰረት የለውም።

የቀድሞ ታጋይ የነበሩና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሃብታሞች ምንጫቸው የትህነግ ሃብትን እንዲያንቀሳቅሱ ? በግለሰብ ስም የድርጅት/ ተደርጎ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። እንደውም ከሌሎች ብሄር አባላት የሆኑም በተመሳሳይ ለትህነግ ሃብት የሚሰበስቡ አሉ። ዛሬ ሁሉም የያዙትን ሃብትና ንብረት በግል ይዘው “ትህነግ ወግድ” የሚሉበት አጋጣሚ መፈጠሩ ነው ስብሃት ሁሉንም መረጃ መስጠት የጀመሩት ይላሉ የመረጃው ሰዎች።

መንም እንኳ በፍርድ ቤት ወንጀል እንዳልሰሩ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ቢናገሩም በቀሪው እድሜያቸው የትግራይ ሕዝብ ሃብቱ እንዳይበላና ግለሰቦች ዘንድ እንዳይቀር ስብሃት መረጃውን እያቀበሉ መሆኑ ታውቋል።

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

በዚሁም በውጭ አገር የሚገኝ ገንዘብ በየትኞቹ ባንኮች እንደሚገኙ፣ በማን ስም እንደሚገኙ፣ ስብሃት የሚያውቁትን ሁሉ ይፋ አድርገዋል። እያንዳዳቸው 260 ሺህ ብር የወር ኪራይ የሚከፈልባቸው አራት ሱቆች በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያና ዕዛው ቦሌ አራት የሚታወቁ በዶላር የሚከራዩ ቪላዎች ያላቸው አቶ አባዲ ዘሙ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቀኝ እንደመሆናቸው እስካሁን ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም፤ ውሎ አድሮ በድርድር የትግራይ ህዝብ በስሙ የተሰበሰበውን ሃብቱን እንዳይዘረፍ የስብሃትን አቋም እንደሚከተሉ እምነት መኖሩ ታውቋል።

ኤፌደራል አቃቤ ህግ ከገር በህገወጥ የሸሸን ሃብት ለማስመለስ አሃብቱ ከተቀመጠባቸው አገራት ጋር ግንኙነት መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚሁም ጥረቱ በጎ ምላሽ ማግኘቱም ተገልጾ ነበር። እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ አገሪቱ የተዘረፈቸውን ሃብት የማስመለሱ ስራ አሁን ደጋፊ መረጃዎች በማግኘቱ አንድ እርምጃ ከፍ ይላል።

በውጭ አገር የትህነግ ምዕራፎች እነ ዶክተር ደብረጽዮን ወደ ጦርነት ለመግባት መወሰናቸው አግባብ እንዳልሆነ በጎንዮሽ እየተከራከሩ ነው። መሆን ነበረበት ያሉትን ጨምሮ በተከታታይ እናትማለን። አምብሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ አንዱና በስማቸው ከፍተኛ የትህነግ ሃብት የሚያንቀሳቅሱ መሆናቸው ይታወቃል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ዳያስፖራ የክልሉ ተወላጅ፣ በቅርቡ አስደማሚ ሃብት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች በገሃድ ብቅ ብቅ እንደሚሉ፣ አብዛኞቹም በምዕራብ አፍሪካ ማዕድንና ሆቴል ዘርፍ የተጀመረውን ንግድ የግላቸው እንደሚያደርጉት ግምታቸውን ሰጥተዋል።

ትህነግም ይሁን ኤፈርት በምዕራብ አፍሪካ በማዕድን ዘርፍ አንድም አይነት ንግድ እንዳለው በይፋ አስታውቆ አያውቅም። ስብሃት ነጋ በቢልዮን ዶላር ሃብት ያለውን ድርጅት ከአፍሪካ አንደኛ እንደሆነ ሲናገሩ ግን የትግራይ ሕዝብ ነው የሚባለውን ጉዳይ አለባብሰውት ነበር።


 • “የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው”አንዳርጋቸው ፅጌ
  ”የአውሮፓ ህብረት ነፃ ፉክክር፤ ነፃ ሚዲያ እና ነፃ የምርጫ ቦርድ ባልነበረበት ይታዘብ የነበረው ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ተቆርቋሪ ሆኖ አልነበረም ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው”  ፖለቲከኛና የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አስታወቁ። ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው ለህብረቱ ሀገራት የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ስላለው መሆኑንContinue Reading
 • የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ
  የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎችን ሲታዘብ ቆይቶ አሁን ከታዛቢነት ለመውጣት የወሰነበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊያሳውቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ምርጫ ጉዳይ ላይ ላለመታዘብ ያሳለፈውContinue Reading
 • ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
  ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ያሰቡት ሊሳካላቸው አይችልም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚያሴሩ አካላት ያሰቡት በፍጹም ሊሳካላቸው እንደማይችል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪና የምርጫ ጉዳይ ደህንነትና ጸጥታ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ። ምርጫውን ለማደናቀፍ የዐመፅ ፍላጎት ያላቸው አካላት አቅደው እየሠሩ ቢሆንም የዚህ ምርጫ ዋነኛ ባለድርሻ በሆነው በኅብረተሰቡ፣ በፌዴራልናContinue Reading
 • የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ
  ሚያዝያ 30/2013 (ዋልታ) – በቻይና መንግሥት በሚተዳደረው ሲኖፋርም ኩባንያ የተመረተው የኮቪድ-19 ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን ሰጠ። ድርጅቱ አርብ ዕለት የሲኖፋርም ክትባትን “ደህንነት፣ ውጤታማነት እና ጥራት” ማረጋገጡን ገልጿል፡፡ የክትባቱ ፈቃድ ማግኘት የጤና ሠራተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ለመከላከል የሚያስፈልገውን የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት የማፋጠን አቅም እንዳለውምContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *